Monday 30 June 2014

“እንደ ከሳሾቼ 100 ሺ የማከራየው ቤት የለኝም” ሲሉ አቶ ገብረውሃድ ተናገሩ


መንግስት በሙስና ወንጀል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ እና የሕግ ማስከበር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት የሰጡ ሲሆን፣ አቶ ገብረውሃድ “በኢትዮጵያቴሌቪዥን 16 ቤት አለው ተብሎ በካሜራ ተቀርፆ መነገሩ የሚያሳዝ ንመሆኑን ፣ እርሳቸው በአዲስአበባ ውስጥ አንዲት ጐጆ እንደሌላቸውና ቢኖራቸው ኖሮ ልጆቻቸው መጠለያ እንደማያጡ ተናግረዋል።
‹‹እንደከሳሾቼ 100,000 የማከራየውቤትየለኝም፤›› በማለት ንጽህናቸውን ለማስረዳት የሞከሩት አቶ አቶ ገብረውሃድ፣ ከሳሾቼ ያሉዋቸውን ሰዎች በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።
ሪፖርተር እንደዘገበው አቶ ገብረውሃድ መሬት መቀበላቸውን ነገር ግን ቤትለመሥራት አቅም ስለሌላቸውም እንዳልሠሩበት ዘግቧል።
ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መላኩ ፋንታ በበኩላቸው ” ልንመሰገንበት በሚገባ ስራ ወንጀለኞች መባላችን ያሳዝናል ” ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ክደዋል።
“አቶ መላኩ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ከ3.2 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ንብረትና ገንዘብ አፍርተዋል”በሚል ለቀረበባቸው ክስ፣እንደማንኛውም ሰው 175 ካሬሜትር ቦታ ላይ ቤት መሥራታቸውን፣ይህ ደግሞ ለእሳቸው ብቻ ተነጥሎ ወንጀል ሊሆን እንደማይችል ገልጸው፣ ዓቃቤ ሕግ የቤቱን ግምት አሳስቶ ማቅረቡንም ተናግረዋል።
ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ምስክሮቹን ከሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ አቅርቦ እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል።
Source: Ethsat

0 comments:

Post a Comment