Tuesday, 24 June 2014

ለጋሽ አገራት በኢትዮጵያ ስላለው የህዝብ መፈናቀል ምርመራ እንደሚያካሂዱ አስታወቁ

ሰኔ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት በጋራ እንዳስታወቁት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ እየታየ ያለውን የህዝብ መፈናቀል ለማጣራት አንድ መርማሪ ቡድን ወደ አካባቢው ይልካሉ።
ለስኳር ልማት በሚል ምክንያት መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ የቦዲና ክዌጎ ጎሳ አባላትን ማፈናቀሉን ዜናውን ይፋ ያደረገው ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል አስታውቋል።
አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን እንዲሁም የአለም ባንክን ያካተተው የለጋሾች ቡድን፣ የሚፈናቀሉና ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚሰፍሩ ሰዎች በቅድሚያ ፍላጎታቸው መጠየቅ አለበት የሚል መመሪያ አለው።
ለጋሽ አገራት እርምጃውን ለመውሰድ የተነሳሱት በእየ አገራቱ የሚገኙ በርካታ የፓርላማ አባላት ጥያቄ እያነሱ በመምጣታቸው ነው።
Source: Ethsat

0 comments:

Post a Comment