Sunday 8 June 2014

አንድነትና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ፊርማ ፈረሙ ( ዱርዬዎች ረብሸው ነበር)

ዛሬ ሰኔ አንድ ቀን 2006 ዓ፣ም አገር ቤት ከሚንቀሳቀሱ አንጋፋዎቹ ድርጅቶች መካከል የሚገኙት የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲዎች የቅድመ ዉህደት ፊርማ ፈርመዋል። በስምምነቱ ወቅት ዱርዬዎች ድንጋይ በመወርወር የነበረዉን ፕሮግራም ለማስተጓጎል ሞከረው ነበር። የቅድመ ዉህደቱን ስምምነት ወቅት አቶ አበባዉ መሃሪ የመኢአድ ሊቀመንበር ንግግር ሰጀምሪ ነበር የድንጋይ እሩምታ በጽ/ቤቱ ላይ የዘነበው። ከስብሰባው አዳራሽ የወጡትን የመኢአድና አንድነት ሰዎች ዱርዬዎችን አብ አረው ለመያዝ ሲሆን፣ አንዱ ዱርዬ ለመያዝ ችለዋል።eprdf_member
የተያዘዉ ድርዬ የኢሕአዴግ ወርሃዊ መዋጮ ከፋይ ካድሬ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ዱርዬዎቹ የወረወሩት ድንጋይ የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊ የሆኑት የፈነከተ እንደሆነ የደረሰን ዘገባ ያለለከታል። የአዲስ አበባ ፖሊሲ አስቀድሞ ጥበቃ እንዲያደርግ ተነግሮት የነበረ ቢሆን፣ በወቅቱ ምንም አይነት ጥበቃል አላሰማሩም።
ፓርቲዎቹ ጠቅላላ ጉባዔ ጠርተው በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ ዉህደቱን እንደሚያጠቃልሉም ተናግረዋል።

0 comments:

Post a Comment