Sunday, 1 June 2014

የማለዳ ወግ … ካርል ሓይሰን ለሰብዕና የተጉ ብጹዕ ነበሩ !



የማለዳ ወግ … ካርል ሓይሰን ለሰብዕና የተጉ ብጹዕ ነበሩ ! ነፍሳቸውን ይማር
ሰብዕናን መሰረት አድርገው በመላ አለም በበጎ የረድኤት እና ምግባረ ሰናይ ድርጅቶችን የመሰረቱ ብጹአን እንብዛም ባልበረከቱባት ምድር አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ በሰብአዊ ስራቸው መንፈሳዊ ቅናት ሰሜታችን የሚያጎኑ አልጠፉም። …ግን አይበረክቱም
ከቀረው አለም ምልከታ ትናንትም ሆነ ዛሬ በእኛ ሃገር ለእኛ ስለሆነውና የሚሆነውን አድርገው ስላለፉት የእኔ ብጹዕ ካርልሓይንስ Karlheinz Böhm ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ሃዘን ጋር ስለዚህ ታላቅ ሰው ጥቂት ማለት ወደድኩ ። ሰብአዊነትን በተግባር ስላሳዩን የሩቅ ሃገር ሰዎች ስናነሳ በቀዳሚነት ከሚነሱት መካከል አንዱ የተከበሩት ካርልሓይንስ Karlheinz Böhm “የሰዎች ለሰዎች ” ምግባረ ሰናይ ድርጅት መስራችነት በቀዳሚነት ይነሳሉ ።
ባለ ጥምር ዜጋው የፊልም ተዋናኝ ካርልሐይንስ በያዝነው ሳምንት መጨረሻ በ86 ዓመታቸዉ ለዚህ አለም እንደተለዩን ሰማን :) የተከበሩት ካርል ሓይሰን ማን ናቸው? ለሚለው ሰፊ ትንታኔ ለመስጠት ሳይሆን የተከበሩት ካርልን ክብር ለማዘከር ፣ በስራቸው መንፈሳዊ ቅናት አድሮብን መንገዳችን እንድንመረምር ብሎም እንማርበት ዘንድ በማለዳ ወጌ ላፍታ የእኔን ብጹዕ የታላቁን ሰው ቅንጭብ ዝክረ ታሪክ በጨረፍታ መቃኘት ወደድኩ …
ካርል ሓይሰን ለኦስትርያዊው አለም አቀፍ ታዋቂ የሙዚቃ ባለሙያ world-famous conductor አባታቸው እና ለጀርመናዊት እናታቸው ብቸኛ ልጅ ነበሩ። ካርልሓይሰን በጎልማሳ እድሜያቸው በፊልም ተዋናኝነት ከ45 ባላነሱ ፊልሞች በመተወን ከፍ ያለ እውቅና ነበራቸው። ሰአሊ የመሆን ህልማቸው ተጨናግፎ በጎልማሳ እድሜያቸው የፊልም ተዋኝ በመሆን በአውሮፖና አሜሪካ በበርካታ ፊልም ዝናን ያተረፉት ካርልሓይሰን እጎአ በ1981 “ሰዎች ለሰዎቸ ” የተባለውን ግብረ ሰናይ ድርጅት በእኛዋ ኢትዮጵያ መስርተዋል። ካርል በእኛው ሃገር ፣ በእኛው ምድር ፣ የእኛን እንባ ከመጥረግ አልፈው ሶስት ሆስፒታልን ከመቶ ያላነሱ የጤና ተቋማትን መስርተው ለአመታት የህክምና እርዳታን ያደረጉ ታላቅ ሰውም ነበሩ። ይህ ብቻ አይደለም… እኛ በአንድ አብረን ለእኛ ሳንሆን በምንንገዳገድበት የታሪክ አጋጣሚ ከሶስት መቶ ስልሳ ትምሕርት ቤቶችን አቋቁመው የእኛኑ ወገን የመማር ህልም እውን በማድረግ አቅማቸው በፈቀደውን ሁሉ ማድረግ የቻሉ ታላቅ ሰውም ነበሩ ። በዚህ መልካም ምግባራቸውም ከአምስት ያላነሱ የተለያዩ አለም አቀፍ አለም አቀፍ የክብር ሽልማትን አግኝተዋል። ካገኟቸው ሽለማቶች መካከልም እአአ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል የክብር ዜግነትን ፣ ከBalzan Prize ተብሎ ከሚጠራው አለም አቀፍ ድርጅት በስብእና በሰው ልጆች መካከል በመከባበር ላይ የተመሰረተ ፍቅርን በማስፋፋታቸው የተበረከተላቸው የክብር ሽልማት እና እጎአ በ2011 ለካርልና ለኢትዮጵያዊቷ ባለቤታቸው ለወ/ሮ አልማዝ በማህበረሰብ እድገትና ሰብዕናን መሰረት አድርገው ለሰሩት በጎ ምግባር Essl Social Prize በተባለው ድርጅት የተበረከተላቸው የክብር ሽልማትን ይጠቀሳል።
እጎአ ማርቸ 16 , 1928 የተወለዱት ካርል ኃይንሰን የትዉልዳቸዉ ሃገራቸው ጀርመን ዳርምሽታት ከተማ ሲሆን ቅስም ሰባሪው ህልፈታቸው የተሰማው እጎአ ሜይ 26, 2014 ኦስትርያ 29 ጎርዲግ ከተማ ዉስጥ ነበር። አኩሪ ስራን ሰርተው የተለዩን ካርል የሰባት ልጆች አባት እንደ ነበሩ ዝክረ ታሪካቸው ያሰረዳል ።
የካርል ግብረ ሰናይ ድርጅት መሰናክሉን ሁሉ አልፎ በሃዘን ችግር ቋፍ ያለው “ሰዎች ለሰዎች” ድርጅት የመስራች አባቱ መለየት ጉዳቱ የከበደ ነው። የድርጅቱ ተረካቢዎች ድርጅቱ እንደ ትናንት ዛሬም ለወገን አጋርነቱን በማሳየት ይቀጥል ብለን መልካሙን ሁሉ እንመኝ ። ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ የድርጅቱ ሃላፊነት በኢትዮጵያዊት ባለቤታቸዉ በወ/ሮ አልማዝ ብቻ የተጣለ አይደለም ባይ ነኝ ። ይህን መሰሉን ድርጅት አቅም በፈቀደ መጠን የመደገፍ ሃላፊነት በመንግስት ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና በሁሉም ዜጋ ላይ የተጣለ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል ባይ ነኝ ። በዋናነት ግን የካርልን አላማ መሰረት አድርው ባለቤታቸው ይህ ፋና ወጊ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ለወገን ደራሽነቱን እንደሚያስቀጥሉት ተስፋ አናድርግ !
አርግጥ ነው ፣ የተከሩት ካርል ሓይሰን ለሰብዕና ሳንተጋ የተጉ ብጹዕ ነበሩ እላለሁ !
ነፍስ ይማር :)
ለመላ ቤተሰቡ መጽናናትን እመኛለሁ!
ነቢዩ ሲራክ

0 comments:

Post a Comment