አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በነገው እለት ሰኔ 15/2006ዓ.ም የሚያካሂደውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ ከ30 በላይ የፓርቲው አባላት በፖሊስ መታሰራቸውን ተከትሎ የሀዋሳ ከተማ ባለስልጣናትና የከተማው ፍትህ መምሪያ ሐላፊ በተገኙበት የተካሄው ስብሰባ መታሰር አልነበረባቸውም፤አሁንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው በሚሉና ማሰራችን ትክክል ነው ከተለቀቁ ነገ ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም በሚል ለሁለት ተከፍለው ሲሟገቱ ማምሸታቸውንና በመጨረሻም አቶ መንድሙ ወታንጎ የተባሉት የደህንነት ሀላፊ በተዓምር መፈታት የለባቸውም መፍታት እንኳን ካለብን የሰልፉ ሰዓት ካለፈ ከ6፡00 በኋላ ነው በማለታቸው በእስር ቤት እንዲያድሩ መወሰኑን ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለፃ ከሆነ ወረቀቶች የተበተኑ በመሆኑ ህዝብ ሊመጣ ስለሚችልከፍተኛ ቁጥጥር እንዲደረግ በደህንነት ሃላፊው መታዘዙን አያይዘው ገልፀዋል፡፡
0 comments:
Post a Comment