Monday 9 June 2014

ቅድመ ውህደቱን ለማወክ ከተዘጋጁት መሃል አንደኛው ታገተ (ፎቶ እና የመታወቂያ መረጃ ይዘናል)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የመኢአድ እና የአንድነት ፓርቲዎች በመዋሃድ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክረው ለመቀጠል፤ የቅድመ ውህደት ፊርማ አድርገዋል።
የቅድመ ውህደት የፊርማ ስርዓት ሲፈጸም በጽ/ቤቱ የተገኙ አባላት
የቅድመ ውህደት የፊርማ ስርዓት ሲፈጸም በጽ/ቤቱ የተገኙ አባላት

ይህ የስምምነት ፊርማ በተደረገበት ወቅት አንዳንድ ወጣቶች “የመኢአድ አባል ነን፤ ውህደቱን እንቃወማለን” በማለት ረብሻ ለመፍጠር ሞክረው ነበር። ድንጋይ በመወርወርም አጸያፊ ተግባራቸውን አሳይተዋል። እነዚህ ወጣቶች ግን የመኢአድ አባላት ሳይሆኑ ኢህ አዴግ የላካቸው ካድሬዎች መሆናቸው፤ ከተያዙ በኋላ ኪሳቸው ሲበረበር የተገኘባቸው መረጃ ማንነታቸውን አጋልጧል። የታገተው ካድሬ ሲናገር የነበረውና ኪሱ ሲበረበር የተገኘበት መረጃ ማንነቱን ስላጋለጠበት አፍሮ አንገቱን ደፍቷል። ለተጨማሪ ዝርዝር በስፍራው የነበረው ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን የላከውን ዘገባ እናስቀድም፤ እንዲህ ብሏል።
ውህደቱ ለማደናቀፍ ቢሞከርም ወያኔ ሳይሳካለን በሰላም መፈረሙ ታውቋል።
ዛሬ በመኢአድ ጽ/ቤት አንድነትና መኢአድ የቅድመ ውህደት ስምምነታቸውን በወረቀት ላይ ከማስፈራቸው ቀደም ብሎ ወደ ግቢው እንግባ የሚሉ የተወሰኑ ሰዎች ግርግር ለመፍጠር ሞክረው ሳይሳካላቸው ሲቀር የግቢውን በር በድንጋይ መደብደብ በመጀመራቸው የተወሰኑት በፖሊስ ተይዘዋል፡፡
ድንጋይ በመወርወር ውህደቱን ለማደናቀፍ ከሞከሩ ሰዎች መካከል የአንዱን ማንነት ለማጣራት በተደረገ ሙከራ ከኪሱ ውስጥ ለኢህአዴግ የወር መዋጮ የከፈለበት ደረሰኝ ተገኝቶበታል፡፡የመኢአድ አባል ነኝ ሲል የነበረው ወጣት ደረሰኙ ከተገኘበት በኋላ በሀፍረት ተሸማቅቆ አንገቱን አቀርቅሯል፡፡
ከረብሻ ፈጣሪዎቹ መካከል አንደኛው ተይዞ ኪሱ ሲፈተሽ ለኢህ አዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈለበት ደረሰኝ ኪሱ ውስጥ ተገኘ፤ እሱም አንገቱን ደፋ።
ከረብሻ ፈጣሪዎቹ መካከል አንደኛው ተይዞ ኪሱ ሲፈተሽ ለኢህ አዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈለበት ደረሰኝ ኪሱ ውስጥ ተገኘ፤ እሱም አንገቱን ደፋ።
የረብሸኛው መታወቂያ ወረቀት
የረብሸኛው መታወቂያ ወረቀት
በተመሳሳይ መልኩ የውህደቱንና የረብሻውን ጉዳይ የዘገበው ምኒልክ ሳልሳዊ ደግሞ በበኩሉ የሚከተለውን ዘገባ አቅርቧል።
መኢአድ እና አንድነት የውህደት ፊርማ ተፈራርመዋል። የአንድነት የሂሳብ ክፍል ሰራተኛን ሲፈነክቱ አንድ የመኢአድ አመራር ጥርሱን በድንጋይ አውልቀውታል።
በዛሬው እለት ከጠዋቱ አራት ሰአት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው የመኢአድ ጽ/ቤት ውስጥ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች ዲፕሎማቶች ጋዜጠኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ እና የአንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ (አንድነት) የውህደት ፊርማቸውን በደመቀ ስነስር ስት መፈራረማቸውን በስፍራው የተገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ውህደቱን ለማደናቀፍ የተወጠነው ሴራ በሁለት መልኩ ቢሆንም አንደኛው የቀድሞ መኢአድ አባላትን በማደራጀት አስርጎ ለማስገባት የተድረገው ሙከራ የመግቢያ ካርድ ባለመያዛቸው እንዲሁም ከድርጅት የተባረሩ መሆናችው ተነግሯቸው በሰላም የተሸኙ ሲሆን ሁለተኛ ብድን የመጀመርያዎቹን አለመሳካት ትክትሎ የተላከ የካድሬዎች ቡድን በር በመገንጠል ለመግባት ሲሞክር አንደኛው ሲያዝ ሌላው የቡድኑ አባላት ከቦታው ሮጠው ማምለጣቸውታውቋል።
በአከባቢው የተመደቡ ፖሊሶች እንዲይዙት ቢጠየቁም ሄዳችሁ የክስ ፋይል ክፈቱና እንይዝላቹሃልን የሚል መልስ ቢሰጡም ማንነቱ እና አድራሽው የማይታወቅ ሰው እንዴት ይከሰሳል ወንጀል ሲሰራ እጅ ከፍንጅ መያዝ ሲገባቸው በንዝህላልነት እና በአደርባይነት መንፈሳቸው ከፍትህ ጋር አብረው ተቀብረዋል።
በወቅቱ ብጥብጥ ለመፍጠር ሞክረው አልሳካ ያላችው ካድሬዎች ቢያመልጡም ከተያዘው አንደኛው ኪስ ውስጥ የኢሕ አዲግ አባልነት ክፍያ ደረሰኝ እንዲሁም መታወቂያ የተገኘበት ሲሆን ለረብሻው የተላኩት ሶስቱን የትግርይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ ፎቶግራፋቸው የተያዘ ሲሆን ድንጋይ በመወርውር አከባቢውን በጥብጠውታል። በፎቶግራፋቸው የምታዩት የአቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ መኪና ተደግፎ የቆምውና አመራሮቹን በድንጋይ የፈነከተው እንዲሁም መኢአድ ግቢ ውስጥ የተያዘው ካድሬ ምስሎቻቸውን ይመልከቱ።
የአቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ መኪና ተደግፎ የቆምው የወያኔ ባለጌ ወጣት
የአቶ ግርማ ሰይፉ ማሩ መኪና ተደግፎ የቆምው የወያኔ ባለጌ ወጣት

መኢአድ ግቢ ውስጥ የተያዘው ካድሬ
መኢአድ ግቢ ውስጥ የታገተው ካድሬ


0 comments:

Post a Comment