Sunday 22 June 2014

አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ አመራሮችንና አባላትን በማሰር ከተማዋን በፀጥታ ኃይሎች በመውረር ተደናቀፈ

በዛሬው ዕለት በአዋሳ ከተማ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በሀዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ከ30 በላይ በፖሊስ የታሰሩ ሲሆን የሲአን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ ለምን ይታሰራሉ ብለው በመጠየቃቸው እሳቸውንም አስረው ከምሽቱ 3፡30 ለቀዋቸዋል፡፡ በቅስቀሳው ወቅት ወረቀቶች የተበተኑ በመሆኑ ህዝብ በነቂስ ሊወጣ እንደሚችል ስጋት ያደረባቸው የደህዴን ካድሬዎች ትላንት ማታ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ተጨማሪ 7 የአንድነት የሀዋሳ አመራሮችና አባሎች በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡ የደቡብ ክልል የደህዴን ካድሬዎች ከተለቀቁ ነገ ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም በሚል ለሁለት ተከፍለው ሲሟገቱ ማምሸታቸውንና አቶ መንድሙ ወታንጎ የተባሉት የደህንነት ኃላፊ መፈታት የለባቸውም መፍታት እንኳን ካለብን የሰልፉ ሰዓት ካለፈ በኋላ ነው በማለታቸው በእስር ቤት እንዲያድሩ መወሰኑና በዛሬውም ዕለት የሀዋሳ ከተማ በፀጥታ ኃይሎችከፍተኛ ጥበቃ ሥር መሆኗን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልፀዋል፡፡
10269554_656125667805704_1964284731181619666_n
10403063_655210891230515_1638818640015330651_n
10407259_656125577805713_222556347364704833_n
10488127_656125691139035_1357107079390830511_n
10488248_656125737805697_5478378998562656693_n

0 comments:

Post a Comment