አቃቤ ህግ
በክሱ ሜሮን አለማየሁ ድንጋይ እንደወረወረች ቢጠቅስም፣ የአቃቤ ህግ ምስክሮች ስትወረውር አላየንም ብለው፡፡
በተጨማሪም አቃቤ ህግ ሜሮን ከ200-300 የሚሆኑ ሰዎችን በመምራት ሁከትና ብጥብጥ እንደፈጠረች ጭብጥ ቢያስይዝም
ምስክሮቹ አቃቤ ህግ እንዳለው ሳይሆን ሜሮን አለማየሁን ከ20-30 ከሚሆኑ ሰዎች ጋር እንዳዩዋት መስክረዋል፡፡
በተመሳሳይ አቃቤ ህግ ሜሮን አለማየሁ ብጥብጡን የፈጠረችው መስቀል አደባባይ ላይ ነው ሲል ምስክሮቹ አቃቤ ህግ
ባለው ሰዓት ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ በሚወስደው መንገድ እንዳዩዋት መስክረዋል፡፡
አቃቤ ህግ ሜሮን አለማየሁ ብጥብጡን የፈጠረችው ከ3 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ባለው ጊዜ ነው ያለ ሲሆን የሜሮን አለማየሁ የመከላከያ ምስክሮች ከ3፡20 እስከ 5 ሰዓት ከእሷ ጋር አምባሳደር አካባቢ እንደነበሩ አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ፍርድ ቤቱ ምስክሮቹ ከ3፡20 በፊት የት እንደነበረች አላስረዱም እንዲሁም ካፌ ውስጥ የጠጡትን ለስላሳ አልገለጹም በሚል ምስክርነቱን ውድቅ አድርጌዋለሁ ብሏል፡፡

0 comments:
Post a Comment