Tuesday 8 July 2014

አንዳርጋቸው ጽጌ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ መሆኑ ተረጋገጠ

Andargachew Tsige
Andargachew Tsige
(ኢ.ኤም.ኤፍ) የግንቦት ሰባት ዋና ጸሃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ አበባ ውስጥ በ እስር ላይ መሆናቸው ተረጋገጠ። ይህ የተረጋገጠው የ እንግሊዝ አለም አቀፍ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ጀስቲን ግሪኒንግ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ በጎበኙበት ወቅት ነው። በአንድ በኩል የሰናአ ፖሊሶች አቶ አንዳርጋቸውን ወደ ኢትዮጵያ አሳልፍው መስጠታቸው ብዙዎችን ቢያናድድም፤ ቢያንስ በመጨረሻ አቶ አንዳርጋቸው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆናቸው መታወቁ ለቤተሰቡም ሆነ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ኢትዮጵያውን ትንሽም ቢሆን እፎይታ አስገኝቷል። “ካሁን በኋላ የውጭ ሰዎች ሊጎበኟቸው ስለሚመጡ፤ ቢያንስ በአቶ አንዳርጋቸው ሊኖር የሚችለው ድብደባ ሊቆም ይችላል።” የሚል አስተያየት ተሰንዝሯል።
ከጥቂት ቀናት በፊት የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ እና ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፤ “የመንን እኛ ስጡን ብለን አልጠይቅም፤ እኛም አልተረከብንም” ማለታቸው ይታወሳል

0 comments:

Post a Comment