Friday 11 July 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑት ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሳይነገራቸው ነው ተባለ

አቡጊዳ 



ኢትዮጵያ ሪቪው ምንጮቹን ጠቅሶ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የታፈኑት፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሳያወቁት ፣ በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የሕወሃት ደህንነት ጽ/ቤት እና በአቶ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ዉሳኔ እንደሆነ ዘገበ። ሁለቱ የሕወሃት ባለስልጣናት፣ የሆነውን ነገር ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ለመንገር እንኳን ደንታ እንደልነበራቸው ኢትዮጵያ ሪቪው፣ እነ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን እንደ አለቃቸው ሳይሆን እንደ «አህያቸው» እንደሚመለከቷቸው በዘገባው አስፍሯል።
«ያለ እንግሊዞች ትብብር፣ የየመን ደህንነቶች የእንግሊዝ ፓስፖርት ያለው ሰው፣ ያለ እንግሊዞች አዎንታ የመያዙ እድል በጣም ትንሽ ነው» ሲልም የእንግሊዝ ደህንነት በጉዳዩ ላይ እጁ ሊኖርበት እንደሚችል ኢትዮጵያ ሪቪዉ አክሎ ገልጿል።
የእንግሊዞች እጅ እንዳለበት በኢትዮጵያ ሪቪዉ የቀረበው ግምት እንደተጠበቀ፣ በተለያዩ መድረኮች ሌሎች ግምቶችም እየተሰጡ ነው። የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ወይንም አስመራ ባለው የግንቦት ሰባት መዋቅር ዉስጥ ያሉ አመራሮች፣ የአቶ አንዳርጋቸውን የጉዞ መረጃ አስቀድመው ለሕወሃት ደህንነቶች በመስጠታቸው፣ አቶ አንዳርጋቸው ሊያዙ እንደቻሉም የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም።
«አቶ አንዳርጋቸውን ማን አስያዛቸው ? » ለሚለው ጥያቄ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለበት መልኩ የግንቦት ሰባት ድርጅት፣ ምላሽ መስጠት እንዳለበትም ብዙዎች ይናገራሉ።

0 comments:

Post a Comment