Thursday 3 July 2014

ወያኔ ክድጡ ወደ ማጡ - ትርፍ አልባ ከባድ የፖለቲካ ኪሳራ

ወያኔ የህዝብን ጥላቻ እያሳደገ እንጂ የህዝብን ልብ እየገዛ አይደለም።

የወያኔው ስርአት በየጎረቤት አገሩ እየተልከሰከሰ ባለስልጣናትን እና የደህንነት አካላትን በገንዘብ በመደለል እና ለማይዘልቁበት የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ በመስጠት ስልጣኑ ሊረዝምለት ያለውን ሁሉ ለዜጎች ሰቆቃ በመፍጠር ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ስደተኞችን እና የተቃዋሚ አመራሮችን አፍኖ በመውሰድ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል በመፈጸም ላይ ነው።
ከዚህ ቀደም በኬንያ እና በጅቡቲ ከከፍተኛ የኦነግ እና የኦብነግ አመራሮች ጀምሮ እስከ ተራ አባላት ድረስ እንዲሁም በሱዳን የቅንጅት እና የኢሕአፓ እና የከፋኝ ግንባር የአርበኞች ግንባር አባላትን በተለያዩ ጊዜያት አፍኖ በመውሰድ የግድያ የእስር እና የማንገላታት እና የቶርች ሰቆቃ በመፈጸም ታሪክ ይቅር የማይለው ከባድ ወንጀል ፈጽሟል።
ይህ አልበቃ ያለው ወያኔ ይህን ሰሞን ደግሞ በየመን የጸጥታ ሃይሎችን እና ባለስልጣናትን በገንዘብ በመደለል የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል መሪ እና የድርጅቱ ጸሃፊ የሆነውን አንዳርጋቸው ጽጌን በማሳፈን ያለበት ቦታ እንዳይታወቅ እስክማድረግ ድረስ ዘልቋል። ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ከወያኔ ጋር በመተባበር የፈጸሙት የየመን ባለስልጣናት ነገን ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ማወቅ ይኖርባቸዋል። ግለሰቡን ለወያኔ አስረክበው በመስጠት በግለሰቡ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልትና ድብደባ በጉዳዩ ላይ እጁን ያስገባ ሁሉ የሚጠየቅበት ጉዳይ ነው። ወያኔ ካለበት ከፍተኛ የሃገር ውስጥ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አጣብቂኝ ለመውጣት መጣር በሚገባው ሰአት ሌላ ከፍተኛ ሊወጣበት የማይችል ማጥ ውስጥ መዘፈቁን ማወቅ አለበት ።
አንድ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ እጅ ገብቶ መከራውን ቢያይም ለሕዝቦች ነጻነት እና መብት እስከሆነ ድረስ ሚሊዮን አንዳርጋቸዎች መፈጠራቸው የማይቀር ሃቅ ነው። ወያኔ ደርግ እንደወደቀ ሁሉ ተንከባሎ መውደቁ የማይቀር እና እስከዘላለም ድረስ ላይነሳ እንደሚቀበር ሊያውቀው የሚገባ ጉዳይ ነው። አንዳርጋቸውን በቶርች እና በግርፋት ማሰቃየት ከተጠያቂነት እንዳማያድን ማወቅ አለባችሁ ዛሬ የሃገሪቱ ሃብቶች ለየመኖች ቢሰጣቸውም ነጋ ሊነጠቁ እንደሚችሉ ማወቅ አለባችሁ ለጊዜያዊ የስልጣን ፍጆታ ዘልቂ የሃገር ጥቅምን አንድ ግለሰብን ለማሰቃየት ማዋል እያንዳንዱ የወያኔ ባለስልጣን የሚጠየቅበት ጉዳይ ነው፡፤ ማንም ከዚህ የሚያመልጥ የለም ። አሁንም ወያኔም ይሁን የመን አንዳርጋቸው ጽጌን የመልቀቅ ግዴታ አለባቸው።

0 comments:

Post a Comment