ዛሬ ሀምሌ 7 ቀን2006 ዓ.ም የፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ፍብሔር ችሎት ሀምሌ 6 ቀን2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የማዕከላዊወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ተክላይ መብራቱ ታሳሪዎቹን ይዘው እንዲቀርቡ ቢያዝም ኃላፊው ታሳሪዎቹን ሳይዙ ቀረቡ፡፡
ችሎቱ በ3፡30 ተሰይሞ ተከሳሽ ክሱ እንደደረሳቸው ዳኛው ጠየቁ፡፡ ክሱ በንባብ ከተሰማ በኋላ የጽሑፍ ምላሽ እንዳላቸው ሲጠየቁ፣ በጽሑፍ መልስ አላመጣሁምበቃል መልስ እሰጣለሁ በማለት ምላሻቸውን ከዚህ እንደሚከተለው በቃል ሰጥተዋል፡፡
ተከሳሾቹ በሰኔ 30 ቀን2006 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወጣ የመያዣ ትዕዛዝ ሐምሌ 1 ቀን2006 ዓ.ም እንደተያዙና ሐምሌ 2 ቀን2006 ዓ.ም ፍቤት ቀርበው ቀጠሮ እንደጠየቁባቸውና በህጉ መሰረት መብታቸው ተጠብቆ እንዳለ ገልጸው ጠበቆቹ ከደንበኞቻቸው ጋር ረቡዕ እና ዓርብ መገናኘት እንደሚችሉየመጡበት ቀን ግን መገናኘት በማይቻልበት ቀን በመሆኑ ነው ያልተገኙት በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡
የከሳሽ ጠበቆች አቶ ተማም አባቡልጉ እና አቶ ገበየሁ ይርዳው በበኩላቸው ይህ በቃል የተሰጠው ምላሽ በሰነድ ያልተደገፈ ማስረጃ የሌለው በመሆኑ የተከበረው ፍቤት ውድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃለን፡፡ ወደ ማዕከላዊ በመሄድ ደንበኞቻችንን ለማናገር እስረኞች አስተዳደር ብናናግርም የፀረ ሽብር ኃላፊውን አናግሩ የሚልምላሽ ነው የተሰጠን ኃላፊውን ማናገር አልቻልንም በቀጠሮ መጥተን እናናግራቸው ብንልም በቀጠሮ ሊያገናኙን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ የኛ ጠበቃ ጓደኞችደንበኞቻቸውን ሲያናግሩ አይተናል እኛ ደንበኞቻችንን እንዳናናግር ተደርገናል፣ አድልዎ ተደርጎብናል፡፡ ምንም እንኳ ሀገሪቷ በወታደራዊ ዕዝ ሥር ብትሆን እንኳ የእስረኞች የእኩልነት መብት አይገፈፍም፡፡
ሌላው የፀረ ሽብር ኃላፊው እንዳመኑት በሳምንት ሁለት ቀን ረቡዕና ዓርብ ብቻ ከእስረኞች ጋር መገናኘት ይችላሉ ያሉትየህግ ጥሰት ነው፣ ለምን በሥራ ቀናቶች ሁሉ መጠየቅ አለባቸው ይህ ህገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ ታሳሪዎቹን ፖሊስ ይዞ እንዲቀርብ ያዘዘ ቢሆንም የፍቤቱን ትዕዛዝ አክብሮ ታሳሪዎቹን አላቀረበም፡፡ በአቤቱታችን መሰረት ደንበኞቻችን ህጉ ተጠብቆ በህጉ መሰረት ያልተያዙ በመሆኑ አሁኑኑ ከእስር እንዲለቀቁልን፤ ይህ የማይሆን ከሆነ በዋስትና እንዲለቀቁልን ክቡር ፍቤቱን እንጠይቃለን፡፡ የእስር ቦታቸው ተቀይሮ ወደ ተሻለ ጣቢያ ተዛውረው በጠበቃ፣በወዳጅ ዘመዶቻቻ እንዲጎበኙ እንዲደረግ ክቡር ፍ/ቤት እንጠይቃለን፡፡ በማለት የከሳሽ ጠበቆች ለፍ/ቤቱ አስረድተዋል፡፡
በመጨረሻም ፍቤቱ የመያዣ ትዕዛዝና ፍቤት ያቀረቡበትን ሰነድ የማዕከላዊ የፀረ ሽብር ዲቪዚዮን ኃላፊ ተክላይ መብራህቱ ሐምሌ 10 ቀን2006 ዓ.ም ከጠዋቱበ 4፡00 ሰዓት ይዘው እንዲቀርቡ አዟል፡፡
የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከሥራ ሰዓት ውጪ ማታና ጠዋት ታሳሪዎችን እንደሚያቀርቡ መዘገቧ ይታወሳል፡፡
Source: Andenatethiopia2012
0 comments:
Post a Comment