ትላንትና ያለምንም ክስ ድፍን 80 ቀን የሞላቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ጓደኞቻቸን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ ያካሄደውን ምርመራ መጨረሱን ፓሊስበጓሮ በኩል በ”ፍርድ ቤት” በመቅረብ አሳውቋል፡፡ ቅዳሜ እለት 28 ቀናት የምርመራ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ”ፍርድ ቤት” ከመሄዳቸው ከቀናትአስቀድሞ ከነበሩበት የጨለማ ክፍል እስር በተለምዶው ሸራተን ወደሚባለው ቦታ የተዘዋወሩት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላለፉት ጥቂት ቀናትበወዳጅ እና ጓደኛም ጭምር መታየት ችለዋል፡፡
ቅዳሜ በመቶዎች ተሰብስበው የሚጠበቁበት ችሎት ላይ ፓሊስ ብቻውን በመገኘት እና ጠበቃውን ባላካተተ ከዳኛ ጋር የተደረገ ንግግር የፓሊስየምርመራ ፋይሉን በማጠናቀቁ ወደ አቃቤ ህግ ማስተላለፉን እና ክሱም በከፍተኛው “ፍርድ ቤት” አንደሚታይ በማመልከት የጊዜ ቀጠሮ ፋይሉአንዲዘጋ ጠይቋል፡፡ ታሳሪዎችም ሆነ የህግ ጠበቃቸው ባልተገኙበት ፍርድ ቤቱ የፓሊስን ጥያቄ ተከትሎ ፋይሉ የተዘጋ ሲሆን ከሰአታት ጥበቃበኋላ በመዝገብ ቤት በኩል ጠበቃቸውና ወዳጆች ፋይሉ መዘጋቱን ለማወቅ ችለዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ትላንት ሰኞ ይቀርባሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት ሌሎች ሶስት የዞን 9 ጦማርያንም ፓሊስም ሳይቀርቡ ፓሊስ በጻፈው የሶስትመስመር ደብዳቤ ምርመራ መጨረሱን አና ለአቃቤ ህግ ማስተላለፉን አሳውቋል፡፡ በመሆኑም የጓደኞቻችን ሆኑ ፓሊስ ባልተገኙበት የትላንትናውሂደትን አስከትሎ የጓደኞቻቸን ጠበቃ አቶ አምሃ መኮንን ክሱን በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ለደንበኞቻቸው አንደሚሰጥ እነደሚጠብቁና እሳቸውባሉበት መከናወን እነዳለበት ገልጸዋል፡፡ የፓሊስን አሰራር የወንጀል ስነስርአት ህግን ያልጠበቀ ድብብቆሽ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ጓደኞቻችን ቀድሞ የነበሩት የእስር ቦታ በቀን ሁለት ጊዜ ለ15 ደቂቃ ወደውጪ ለመናፈስ ከመውጣት ባሻገር ምንም ከውጪው አለም ጋርየመገናኘት እድል ሳይኖራቸው ከሁለት ወራት ከግማሽ በላይ ካሳለፉበት ጊዜ በመገላገል ሊጠየቁ ወደሚችሉበት ቦታ መዘዋወራቸውን ተከትሎበጠንካራ ሞራል አና አካላዊ ደህንነት ላይ አንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል፡፡ በቦታው ለጎበኙዋቸው ወዳጆች አንደተናገሩትም ሁሉም ራሳቸው ላይጥፋተኝነትን የሚመሰክር ቃል ላይ የፈረሙ ሲሆን ጦማሪ አቤል ዋበላ ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆኑ እስካሁን ሌሎች ሊጎበኘት የማይችሉት ቦታላይ አንደቆየ ታውቋል፡፡
የተከሰሱት አና ምርመራ እየተካሄደባቸው ያለው በጻፏቸው ጽሁፎች አይደለም የሚል ክርክር ሲያቀርብ የነበረው ፓሊስም ፣ ጽሁፎቻቸውንማስረጃ አድርጎ እነዳስፈረማቸው ገልጸውልናል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የሪፓርተር ጋዜጣ ሁለት ዜናዎችን በማጋራቱ ብቻመስረጃ ተብሎበት አንዲፈርም የተገደደ ሲሆን ዜናው የመከላከያ የብሄር ተዋእጾን አና አዲሱን የይቅርታ አዋጅን የሚመለከት ሲሆን ጦማሪበፍቃዱ ስለለውጥ የሚለው በዞን9 ላይ የተጻፉ ተከታታይ ጽሁፎቹ እነዲሁም ጦማሪ ዘላለም ክብረት ህግ መንገድ ወይስ ምርኩዝ እና ሳንሱርድሮና ዘንድሮ የሚሉት ጽሁፎች ይገኙበታል ፡፡
የዞን 9 ጦማርያን በጠንካራ አካላዊና መንፈሳዊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሲሆን አላአግባብ እስሩን ተከትሎ በተለያየ መልኩ አጋርነታችሁን ላሳያችሁየዞን 9 ነዋሪያን እና የሰብአዊ መብት ጠበቆች ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በምርመራ ወቅት በተደጋጋሚ የተፈጸመባቸው የመብትጥሰትም ሃሳባቸውን መግለጻቸው ትክክል መሆኑን ያረጋገጠላቸው መሆኑን አስታውሰው መጪውን የህግ ሂደት ለመከታተል እና ለታሪክለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ዞን 9 ጦማርያን ስብስብ በምንም ድብቅ ህገ ወጥ ድርጊት ውስጥ ተሳትፈን አንደማናውቅ እና ጦማሪ ጓደኞቻችን አንዲፈቱ መጠየቃችንንእንደማናቆም እያስታወስን መጪውን የህግ ሂደት በሚገባ ለመዘገብ እና የፍትህ ስርአቱን ለመፈተሽ ዝግጁ መሆናችንን በድጋሚ አንገልጻለን፡፡
የጦማሪ በፍቃዱና ዘላለም ጽሁፎች ሊንክ ከስር ይገኛል፡፡
#Ethiopia #FreeZone9bloggers #FreeEdom #FreeTesfalem #FreeAsemamaw #FreeAllPoliticalPrisoners
አዘጋጅ Zone 9
0 comments:
Post a Comment