Sunday, 25 May 2014

የኦሮሚያ ፖሊስ አስራት አብርሃን ሰወረ

                                                   10325409_641028839315387_2062526112924134023_n
የአራት ፓርቲዎች መድረክ የሆነው መድረክ ትናንት በአዲስ አበባ ላደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቀደም ብለው የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ የነበሩ አስራ ሁለት ሰዎች በቡራዩ ከተማ በፖሊስ መታሰራቸውን የሰሙት የአረና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ሐብታይ ገብረ ሩፋኤልና በቅርቡ አንድነት ፓርቲን የተቀላቀለው ደራሲና ፖለቲከኛ አስራት አብርሃ እስረኞቹን ሊጠይቁ በሄዱበት በወረዳው ከታሰሩ በኋላ ፖሊስ አቶ ሐብታይን ሲለቅ አቶ አስራትን በወረዳው አሳድሯቸው ነበር፡፡
ዛሬ ማለዳ አቶ አስራትንና የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ ወደ ቡራዩ ያመሩት የአቶ አስራት ባለቤትና የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አቶ አስራት በፖሊስ ጣብያው አለመታሰራቸው ተነግሯቸዋል፡፡አቶ ሐብታይ በስፍራው በመገኘት ‹‹አስራት ከእኔ ጋር ታስሮ ነበር››ቢሉም የኦሮሚያ ፖሊስ ‹‹የምትሉትን ሰው እኔ አላሰርኩትም››የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡
በቡራዩ ከተማ ሶስት ፖሊስ ጣብያዎች በመኖራቸው አስራትን ፍለጋ ወደ ፖሊስ ጣብያዎቹ ያመሩት የአንድነት አመራሮች ተመሳሳይ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

Abraha Desta 

ፖለቲከኛ አስራት አብርሃም በደህንነት ሰዎች ከቡራዩ ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ ተወሰደ። ምንም ወንጀል ሳይሰራ በቡራዩ ከተማ ለሰለማዊ ሰልፍ ሲቀሰቅሱ የታሰሩ የመድረክ አባላትን ለመጠየቅ በመሄዱ ምክንያት ታፍኖ ከተወሰደ የሕገወጥ ዓማፂ ቡድን አባል ቢሆን ኑሮስ ምን ያደርጉት ነበር? ደሞ ሰለማዊ ሰዎችን እያፈኑ ከደርግ እንሻላለን ይሉናል! ደርግ ኮ እያፈነ የገደለን ሕገወጥ ዓማፂ ቡድን (ህወሓት) ስለነበረ ነው። በደርግ ግዜ ህወሓት ዓማፂ ሕገወጥ ቡድን ነበር። የህወሓት አባል የሆነ ወይ ህወሓትን የተባበረ ሁሉ እርምጃ ሲወሰድበት ደርግን እንቃወመው ነበር። አሁን ደግሞ ሰለማዊ ሕጋዊ ታጋዮችን እየታፈኑ የሚወሰዱበት ግዜ ላይ ደረስን! አሁን እንደ ህወሓት ያለ ሕገወጥ ድርጅት (ዓማፂ ቡድን) ቢኖር ኑሮስ ምን ያደርጉን ነበር? ወይ ግንቦት 20! It is so!!!

0 comments:

Post a Comment