Wednesday, 21 May 2014

የአንድነት ፓርቲ በደጀን፤በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ የምክር ቤቶች ምስረታ አካሄደ – በያሬድ አማረ

                                            UDJ-SEAL
በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር አባል ፤የውህደት ጉዳዮች ፀሀፊና የፋይናንስ ክፍል ሀላፊ በሆኑት በአቶ ፀጋዬ አላምረው የተመራው ከፍተኛ ልኡካን ቡድን ከባለፈው ሳምንት ሀሙስ ማለትም ከግንቦት 7ቀን 2006ዓ. ም ጀምሮ በሰሜን ቀጠና የሚገኙ የፓርቲውን አደረጃጀት መዋቅሮች በመገምገም ላይ ሲሆን በተለይ በመኢአድና በአንድነት ፓርቲዎች የውህደት ጉዳይ በደጀን በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ የመኢአድ አባላት በቀረበ ጥያቄ መነሻነት በውህደቱ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ መሰጠቱንና ከተናጥል ውይይቱ በኋላ የሁለቱ ፓርቲዎች አባላትን በጋራ በመሰብሰብ ስለወደፊት የሰላማዊ ትግል አቅጣጫ ስልት ዙሪያ መመሪያ የተሰጠ ከመሆኑም በላይ በደጀን፤በደብረማርቆስና በባህር ዳር ከተማ በእያንዳንዱ ከተማ 15 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያሉት የምክር ቤት ምስረታ መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተያያዘ ሁኔታም በቻግኒ ፤ዳንግላ እና አዴት ከሚገኙ ከመኢአድና አንድነት ፓርቲ አባላት ጋር ተመሳሳይ ሰፊ ውይይት የተደረገ መሆኑንና በአዲስ መልክ የስራ አስፈፃሚ አባላት መዋቀሩን እንዲሁም በአዴት ላይ ጽ/ቤት መከፈቱን በቦታው የሚገኘው ልኡካን ቡድን አስታውቋል፡፡ ቡድኑ በቀጣይ ቀናትም የፓርቲውን አደረጃጀት መዋቅር እየገመገመ ተመሳሳይ የማጠናከር ስራውን በሌሎች ቦታዎችም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

0 comments:

Post a Comment