Sunday 18 May 2014

ፖሊስ በሶስቱ የዞን 9 ጦማርያን ላይ ሊያቀርብ ያሰበው የአሸባሪነት ክስ ውድቅ ሆነ


(ኢ.ኤም.ኤፍ)ሃሳባቸውን በድረ ገጽ ላይ የሚገልጹ ዘጠኝ ወጣት ጦማርያን ተይዘው በ እስር ላይ መሆናቸው ይታወሳል። ዘጠኙ ጦማርያን ወይም የድረ ገጽ ጸሃፊዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበት ድረ ገጽ ዞን ዘጠኝ በመባል ይታወቃል። እራሳቸውንም ዞን 9 ብለው ነው የሚጠሩት። እናም ከዘጠኙ መካከል ስድስቱ በትላንቱ እለት አራዳ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። ፖሊስ “ምርመራዬን አልጨረስኩም፤ ተጨማሪ ቀን ይሰጠኝ” በማለቱ ትላንት የተሰየሙት ዳኛ በጠዋቱም ሆነ በከሰአቱ ችሎት፤ የፖሊስን ጥያቄ ተቀብለው ተጨማሪ ቀን ሰጥተው ወጣቶቹም በእስር ቤት እንዲቆዩ ማዘዛቸው የሚታወቅ ነው። የትላንቱ ዳኛ ዛሬ አልነበሩም። የዛሬው ችሎት ዳኛ ሴት ናቸው። እነሱ ጋር ነበር 3ቱ ጦማርያን ዛሬ የቀረቡት።
በፎቶው ላይ አቤል፣ ማህሌት እና በፍቃዱ ይታያሉ። ከመታሰራቸው በፊት በሰላሙ ግዜ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው። (የፎቶ ምንጭ፡ ዞን ዘጠኝ ብሎገር)
በፎቶው ላይ አቤል፣ ማህሌት እና በፍቃዱ ይታያሉ። ከመታሰራቸው በፊት በሰላሙ ግዜ የተነሱት ፎቶግራፍ ነው። (የፎቶ ምንጭ፡ ዞን ዘጠኝ ብሎገር)

ዛሬ እሁድ የቀረቡት ማህሌትፋንታሁን፣በፍቃዱሃይሉእና አቤል ዋበላ ናቸው። በዚሁ የአራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ችሎት ሲቀርቡ፤ ዳኛው ከትላንቱ የተለየ ነገር እንደማያረጉ ና ፖሊስ የጠየቀውን ያስፈጽማሉ ተብሎ ነበር የተጠበቀው። ሆኖም የተጠበቀው ነገር አልሆነም። ዳኛዋ የፖሊስን ጥያቄ አልተቀበሉም፤ ብስራት ወልደሚካኤል ከአዲስ አበባ የላከውን የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ እናስነብባቹህ። እንዲህ ይላል…

ፖሊስ ሊመሰረት ያሰበው የሽብርተኝነት ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደረገ
ዛሬ እሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. አራዳ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በፍቃዱኃይሉ፣ አቤልዋበላ እና ማህሌትፋንታሁን ከረፋዱ 4፡20 ቀርበውነበር፡፡ይዟቸው የመጣውና እስካሁንም መደበኛ ክስ ያልመሰረተው የማዕከላዊ ፖሊስ ምርመራዬን አልጨረስኩም፣ጉዳዩ ከሽብር ጋር ስለሚያያዝ ተጨማሪየ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ቢጠይቅም ፍርድቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ፍርድቤቱም ከዚህበፊት ለ24 ቀናት አስራችሁ ያቀረባችሁት ከሽብር ጋር የተያያዘ ባለመሆኑ እና ሌላ አዲስሂደት ስለሌለ ከዚህበፊት ያላቀረባችሁትን ከሽብርጋር የተያያዘ የሚለውን ጭብጥ አልቀበልም፣ ተጨማሪ የ28 ቀናት የምርመራ ጊዜየ ተጠየቀውም ተገቢ አይደለም ካለ በኋላ የ14 ቀናትተጨማሪ ጊዜ በመስጠት ለእሁድ ግንቦት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋትተለዋጭ ቀነቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ፍርድቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የሚውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
ትናንት ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. የነበረውየ 6ቱ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ፖሊስ ጉዳዩን ከሽብር ጋር አያይዞተ ጨማሪ የ28 ቀናት የጠየቀውተፈቅዶለት ለሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋትተለዋጭ ቀነቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል፡፡ትናንት የነበረው የ6 ቱን ጉዳይ የተመለከተው ዳኛ ወንድ ሲሆን የዛሬውን ጉዳይ የተመለከተችው ዳኛ ሴትመሆኗተጠቁሟል፡፡
በቀጣይ የምናገኛቸውን ተጨማሪ ዘገባዎች ይዘን እንቀርባለን። ተከታተሉን።

0 comments:

Post a Comment