Monday 1 August 2016

በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ሕዝባዊው ተቃውሞ ቀጠለ * በበዴሳ ሰልፈኞች እስር ቤት ሰብረው እስረኞችን አስለቀቁ – በአወዳይ በአጋዚ የተገደሉት ቁጥር 6 ደረሰ

በምስራቅ እና ም ዕራብ ሐረርጌ የህዝብ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው:: ትናንት በአወዳይ ከተማ የአጋዚ ሰራዊት በሕዝብ ላይ ተኮሱ 26 ሰዎች ማቁሰሉና የገደላቸውም ንጹሃን ዜጎች ቁጥር ወደ 6 ማደጉ ተዘግቧል::

በዛሬው ዕለት በአወዳይ አጋዚ አፈሳ የጀመረ ቢሆንም ሕዝባዊው ተቃውሞ በምስራቅ ሐረርጌ ዳዳር ከተማና በማሳላ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል:: ሕዝቡ አንገዛም እስከማለት የደረሰ ሲሆን በሶቃ ከተማና በሌሎችም እየተቃወመ ነው:: በምዕራብ ሐረርጌም እንዲሁ በተለይም በበዴሳ ከተማ የአጋዚ ጦር በንጹሃን ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥይት አዝንቧል:: በዚህም ሳቢያ ህፃናት ሳይቀር እንደቆሰሉና በየአደባባዩም ደም እንደሚታይ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

በቆቦ ከተማ በኩል ያለው የሃረር መንገድ መዘጋቱ ሲታወቅ በበዴሳ ከተማ ጥይት የተተኮሰበት ህዝብ ቁጣውን ለመግለጽ እስር ቤት ሰብሮ በመግባት እስረኞችን ማስለቀቁ ተሰምቷል:: በበዴሳ ከተማም በአጋዚ የቆሰሉት ወገኖች ብዛት ከ10 በላይ ሲሆን 2 ሰዎች መሞታቸውም ታውቋል::

በመሰላ ከተማ እና በበበዴሳ ከተማ የቆሰሉ ወጣቶችና ህጻናት በጭሮ ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ::




0 comments:

Post a Comment