Tuesday 2 August 2016

በባህርዳር እና በመላው የኦሮሚያ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

“ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ማሳወቅ በቂ ነው” የሚለው የሰማያዊ ፓርቲ መልዕክት ነሀሴ 01 ቀን 2008 ዓ ም በባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰላማዊ ሰልፍ መጠራቱን ይገልጻል።

በባህር ዳር ከተማ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ የማሳወቂያ ደብዳቤ ገቢ ተደረጓል፡፡ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 01 ቀን 2008 ዓ/ም በባህር ዳር ከተማ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ ከሀሙስ ሐምሌ 21 ቀን 2008 ዓ/ም ጀምሮ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተቀብሎ ምላሽ እንዲሰጠን በተደጋጋሚ ጊዜ ጠይቀን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባይሆንም ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን 2008 ዓ/ም ለባህርዳር አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት፣ ለመምሪያ ፖሊስ እና ለፀጥታ ዘርፍ አስፈርመን አስገብተናል፡፡በመሆኑም ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ማሳወቅ በቂ በመሆኑ ሰልፉ እሁድ ነሀሴ 01 ቀን 2008 ዓ ም በባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ስለሚካሄድ የባህር ዳር ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፉ እንድትሳተፉ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በተመሳሳይ በኦሮሞ አክቲቪስትቶች እየተላለፈ ያለው መልዕክት እንደሚያመለክተው በመላው የኦሮሚያ ከተሞች የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 30፣ 2008 ዓ.ም ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ተጠርተዋል።

በኦሮምያ ሲደረግ በነበረው ተቃውሞ የሞቱ ወገኖቻችን እየቀበርን፡ የቆሶሉትን እያስታመምንና የታሰሩትንም እየጠየቅን እጅግ በጣም መራራ ወራትን አሳልፈን ዛሬ ዜጠነኛ ዋራችን ላይ እንገኛለን! በሰላማዊ እንቅስቃሴ የማያምን ከጅምሩም በጠመንጃ አፈሙዝ የተወለደዉን ክፉ የወያኔ መንግስት አሁንም ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለመፋለም የፊታችን ቅዳሜ (ሐምሌ 30፣ 2008 ዓ.ም) በኦሮሚያ ከተሞች በሙሉ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ሲለተጠራ ሁላችንም በምንኖርበት ከተሞች ዉስጥ በነቂስ ወጥተን ተቃዉሞአችንን እንድናሰማ ጥሪ ተላልፏል!

ድል ለሰፊው ህዝብ!

0 comments:

Post a Comment