በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ከህዳር ወር 2006 ዓ.ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞና የመብት ጥያቄ
ምክንያት በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰደው እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰልፈኞች ተገድለዋል፤ በሺዎች
ታስረዋል፤ ተሰደዋል፣ ሲያልፍም የገቡበት ያልታወቁ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህ እውነታ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት
ተሟጋች ድርጅቶች በተሰሩ ሪፖርቶች ገሃድ የወጣ ድርጅታችን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጅክትም ሲዘግበው የነበረ
የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክትም በህዝባዊው ተቃውሞ የተነሳ
መንግስት ግድያ የፈጸመባቸውን ዜጎች ዝርዝር በጥናት ላይ ተመስርቶ ይፋ አድርጓል፡፡ በተቃውሞው ሂደት መንግስት
በወሰደው የኃይል እርምጃ ህይወታቸውን ካጡት ዜጎች በተጨማሪ በርካቶች አደባባይ ወጥተው የመብት ጥያቄያቸውን
በማሰማታቸው ወደእስር ቤት ተግዘዋል፡፡ እስረኞቹ በክልልና በፌደራል እስር ቤቶች ታጉረው ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት በፌደራል መንግስቱ በሚተዳደሩ እስር ቤቶች የሚገኙትንና ክሳቸው ሽብር
የሆኑትን ሰዎች ዝርዝር ከዚህ ቀጥሎ ይፋ አድርጓል፡፡ ዝርዝሩ ከሽብር ውጭ ባለ ወንጀል የተከሰሱትንና ለእስር
ተዳርገው ክስ ያልተመሰረተባቸውን እስረኞች አይጨምርም፡፡ በዝርዝሩ ላይ የተካተቱት ተከሳሾች ከህዳር 2006 ዓ.ም
ጀምሮ ከተነሳው የኦሮሞ ህዝብ የመብት ጥያቄ እንቅስቃሴ ወዲህ ክስ የተመሰረተባቸው ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ ሳይመሰረትባቸው በፌደራል ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ (ማዕከላዊ) በእስር ላይ የሚገኙ
ተጠርጣሪዎች እንዳሉ አብረዋቸው ታስረው ቆይተው ክስ ከተመሰረተባቸውና ቀጥሎ ስማቸው ከተዘረዘሩት ሰዎች ለመገንዘብ
ቢቻልም፣ ሙሉ ስማቸውና ቁጥራቸው በውል ባለመታወቁ ለጊዜው እዚህ ዝርዝር ውስጥ አልተካተቱም፡፡ በዘጠኝ መዝገቦች
የተከፈተው የሽብር ክስ ተከሳሾች ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡
በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ (እነ በቀለ ገርባ)
1. በቀለ ገርባ
2. ደጄኔ ጣፋ
3. አዲሱ ቡላላ
4. ጉርሜሳ አያኖ
5. አብደታ ነጋሳ
6. ገላና ነገረ
7. ጭምሳ አብዲሳ
8. ጌቱ ግርማ
9. ፍራኦል ቶላ
10. ጌታቸው ደረጄ
11. በየነ ሩዶ
12. ተስፋዬ ሊበን
13. አሸብር ደሳለኝ
14. ደረጄ መርጋ
15. የሱፍ አለማየሁ
16. ሂካ ተክሉ
17. ገመቹ ሸንቆ
18. መገርሳ አስፋው
19. ለሚ ኤዴቶ
20. አብዲ ታምራት
21. አብደላ ከመሳ
22. ሀራኮኖ ቆንጮራ፣ ናቸው፡፡
በእነ ደስታ ዲንቃ መዝገብ
23. ደስታ ዲንቃ
24. ለማ ባይ ጉተማ
25. ዋዩ ቤካ
26. አብደታ ባትሪ
ያለ አባሪ ክስ የቀረበበት
27. ዮናታን ተስፋዬ
በእነ ሐብታሙ ሚልኬሳ የክስ መዝገብ
28. ሐብታሙ ሚልኬሳ ጫሊ
29. ረዳት ሳጅን ጫላ ፍቃድ አብደታ
30. ጌትነት ለሚ ኃይሎሴ
31. በከልቻ ቁፋ ቤኛ
32. ለሜሳ አብቹ ዱሬሳ
33. መኮነን ገቢሳ ገደፉ
34. ፀጋዬ ጋዲሳ ኡባ
35. አቦንሳ አኩማ ሆንዳራ
36. ረዳት ሳጅን ቤኩማ ታደሰ ፊንዳ
37. ዲንሳ ፋፋ ድርባ
38. አልኩ አቦና መኩሪያ
39. እሸቱ ደባ ነገዎ
40. ታደሰ ነገኦ ገመዳ
41. ኡምኔሳ በዳሳ ሚዴቅሳ
42. ሮቢሌ አብዲሳ ክቲላ
43. በቀለ ተሬሳ ረጋሳ
44. ነገሰ በርሲሳ ደበሌ
45. ካሳሁን ሙሊሳ ሙለታ
46. አብዲ ታሪኩ ዴረሳ
47. ደጀኔ ፋይሳ ጠፋ
48. ታሪኩ ቦኪ ደበላ
49. አብዲሳ ቦካ ቱጅባ
50. እምሩ ነገዎ ጀማ
51. መልካሙ ታደለ ቢዬ
52. ረዳት ሳጅን ተስፋዬ አባተ ደምሴ
53. ተካልኝ ቡለቾ ገመዳ
54. ረ/ሳጅን ኩምሲሳ ዱጉማ ሚልኬሳ
55. ክንፈ መኮነን ተሰማ
56. ኪንስታብል ገመቹ ታሪኩ እጅጉ
57. ቶሎሳ በዳዳ ደበሬ
58. ሺፈራው ግርማ ሰንበታ
59. ቢኒያም ጫላ ገረሱ
60. ስንታየሁ መኮንን ገዳ
በእነ ኦላና ከበደ መዝገብ
61. ኦላና ከበደ
62. ወልዴ ሞቱማ
63. መገርሳ ፍቃዱ
64. አርገምሲሳ ሌንጂሳ
65. ም/ሳጅን መሰረት አቦማ
66. አብዲሳ ኢፋ
67. ዋርደር ተመስገን
68. ተካልኝ መርዶሳ
69. ቦኪ እሸቱ
70. ብርሃኑ ቦኪ
71. ማሙሽ ቦኪ
72. ፍቃዱ አዱኛ
73. መኮንን ዘውዴ
74. ወርቁ ጉርሙ
75. ገረሙ አዱኛ
76. ደረጄ ታዬ
77. ጃለታ ሰንዳፋ
78. ላቀው ሮቢ
79. እንግዳ ቁሲ
80. ቶሽሌ ተስፋ
81. ታደለ ዓለሙ
በእነ አበበ ኡርጌሳ መዝገብ
82. አበበ ኡርጌሳ
83. መገርሳ ወርቁ
84. አዱኛ ኬሶ
85. ቢሉሱማ ዳመና
86. ሌንጂሳ አለማየሁ (መከላከል ሳያስፈልገው በፍርድ ቤት ነጻ ተብሎ የተፈታ)
87. ተሻለ በቀለ (ከሽብር ክስ ወደ ወንጀል ህጉ ተቀይሮለት ተከላከል የተባለና በዋስ የተፈታ)
በእነ ተሾመ ረጋሳ መዝገብ
88. ተሾመ ረጋሳ
89. ጫላ ዲያስ
90. ኦብሱማን ኡማ
91. ኒሞና ለሜሳ
92. ከበደ ጨመዳ
93. ምረቱ ጉሉማ
94. ዴቢሳ በየነ
95. ጌታሁን ደስታ
96. መንግስቱ ጉዲሳ
97. ተሰማ ሁንዴ
98. ቦንሳ (ኦብሳ) ኃይሉ
99. አሸብር ኦንቾ
100. ጃራ ኤቢሳ
101. ፋፋ ሬፋንራፋ
102. አጥናፉ ቢራሳ
103. አብዲ ታደሰ
በእነ ሀብታሙ ሀጫሉ መዝገብ
104. ሀብታሙ ሀጫሉ
106. ቶኩማ ሙሌሳ
107. ደጋጋ ብርሃኑ
108. ዮሐንስ ኡርጌሳ
109. ዴብሳ በሊና
110. አብዱርህማን አደም
111. ዮሴፍ ዲዳ
112. ተስፋዬ በቀለ
113. ዴቢሳ ኤታንሳ
114. ናኦል ሻሚሮ
115. ለታ አህመድ
በእነ ቀጀላ ገላና የክስ መዝገብ
116. ቀጀላ ገላና
117. ሰብኬበ በቀለ
118. አብደታ ወላንሳ (ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በደረሰበት ድብደባ (ቶርች) ምክንያት ታሞ ቂሊንጦ እስር ቤት የሞተ)
119. ኡርጌሳ ደመና
በእነ አሚን ዬዮ ሙመድ መዝገብ
120. አሚን ዬዮ ሙመድ
121. አብዱ የሱፍ አቡዱ ኡመር
122. አብድልዋሴ ኢብራሂም አብደላ
123. አብድልቃድር መሃመድ ኢብራሂም
124. ሸምሰዲን አህመድ ኡመድ
125.መሃመድ አልዩ ኡመር አህመድ
126. መሃመድ ሶፍያን ሀመዴ
127. አበዲ መሃመድ አደም
128. ጀማል ቶፊቅ አሜቶ
129. ፋሮምሳ ሃሚሶ ጊዞ
130. ሃሩን አዪቦ መሀመድ
131. ናስር አሚን ኢብራሂም ኡመር
132. ጀማል አልዩ መሃመድ ብተቤ
133. አህመድ ከሊፍ አሚን
134. ከልፍ መሃመድ አደም
135. ብሩ ገለቱ ጋሪ
136. ያሲን መሃመድ አደም
(በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት የተዘጋጀ)
በቀለ ገርባ
0 comments:
Post a Comment