Wednesday 17 August 2016

በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በደቡብ ኮሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሃገር ቤት እየተደረገ ያለውን ሕዝባዊ ትግል በመደገፍና በሰላም ጥያቄውን ላቀረበው ህዝብ ምላሹን ጥይት ያደረገውን የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በመቃወም በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊትለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ::

ኢትዮጵያውያኑ የኢትዮጵያ ባንዲራንና የኦሮሞን ሕዝብ የትግል ባንዲራ በመያዝ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ድሉን ተጎናጽፎ በሃገራችን ዘረኛው ስርዓት እስኪወገድ ድረስ ከሕዝቡ ጎን ነን ሲሉ ቃል ገብተዋል:: በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይም የታሰሩ እንዲፈቱ; የወልቃይትና የሌሎች ሕዝቦች ጥያቄዎች እንዲመለሱ በወያኔ ሕወሐት ኢምባሲ ፊትለፊት ጮኸታቸውን አሰምተዋል::


0 comments:

Post a Comment