Wednesday 1 June 2016

እነብርሀኑ ተ/ያሬድ ያለቀጠሮአቸው ተገደው ፍርድ ቤት ቀረቡ

--ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን የመከላኪያ ምስክሮች በምን ጭብጥ የሚሉትን እንዲናገሩ ከምስክሮቹ ቀጠሮ አስቀድሞ እንዲገለፁ ጠይቋል፡፡
--ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ እና ማረሚያ ቤት ህገወጥ ጫናና ወከባ እየፈጠሩብን ይገኛል ብለዋል፡፡

የክስ መዝገባቸው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት በመታየት ላይ የሚገኘው 4 ተከሳሾች ብርሀኑ ተ/ያሬድ እየሩሳሌም ተስፋው-ፍቅረማርያም አስማማው እና አቶ ደሴ ፍርድ ቤቱ እንዲከላከሉ ብይን በመስጠት የመከላከያ ምስክር ለማቅረብ ከግንቦት 30-ሰኔ 8 ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበረ ቢሆንም ዛሬ ግንቦት 23 ቀን 2008ዓም ያለቀጠሮአቸው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርገዋል፡፡

ተከሳሾቹ ዛሬ የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንደሌላቸው ለማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች ቀድመው ከግቢ የገለፁ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ የጥበቃ ሃላፊዎች መቅረብ አለባችሁ በሚል ግዳጅ ወከባና ግፍተራ እንዲቀርቡ መገደዳቸው ለፍ/ቤቱ ሲገልፁ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኃላ የፍርድ ቤቱም ዳኛም “ዛሬ ቀጠሮ ባይኖራችሁም ፍርድ ቤቱ ማጣራት ያለበት ጉዳይ ስላለ ነው የጠራናችሁ”በማለት የተከሳሾቹ መከላከያ ምስክሮች የሚመሰክሩበትን ጭብጥ ተከሳሾቹ ለፍርድ ቤቱ እንዲያስረዱ ተጠይቀዋል፡፡ 

ቀደም ሲል ተከሳሾቹ ካስብት የመከላኪያ ምስክሮች ከ1-10 ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች መሆናቸው ይታወቃል፡፡የምስክሮቹ ጭብጥ ማሳወቅ የሚገባን ምስክረነት በሚሰጥበት ዕለት እንጂ ምስክሮቹ ከመቅረባቸው አስቀድሞ ለፍርድ ቤቱ የማሳወቅ ህጋዊ ግዴታ የሌለባቸው መሆኑን ተከሳሾቹ የገለፁ ሲሆን ፍርድ ቤቱ እየጠየቀ ያለው ቅድመ ሁኔታ ግን ህጋዊ መሰረት የሌለው እና የፍርድ ቤቱም ተኃማኒነት የት ድረስ እንደሆነ ያሳያል፡፡ የፍትህ ስርዓቱ አይን ያወጣ የገዢው ፓርቲ የአፈና መዋቅር ተፅኖ እንዳረፈበት በግልፅ የሚያሳይ ብለውታል፡፡.ተከሳሾቹ አያይዘው እንደገለፁት ለምስክሮች የተዘጋጀው መጥሪያ በፍርድ ቤቱ ዳኛ ተፈርሞ ለምስክሮቻቸው እንዲሰጥ ማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ ተከሳሾች ከደረሳቸው በኃላ በድጋሚ “በፍርድ ቤት ትእዛዝ ነው” በሚል ምክንያት መጥሪያዎቹ የተነጠቁ መሆኑ በማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች በኩልም መከላከያ ምስክሮቻቸው እንዳይቀርቡ እየተደረገ ሲሆን
የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ለምስክርነት ማስጠራታቸውን ተከትሎ እንዲሰርዙ ማስፈራርያና ወከባ እየደረሰባቸው መሆኑ አያይዘው ገልፀዋል፡፡ 


በመጨረሻም ተከሳሾቹ የምስክሮቻቸውን ጭብጥ ለፍርድ ቤቱ እንደማያሳውቁ በአፅኖት የገለፁ ቢሆንም የፍርድ ቤቱ ዳኛ “ከአነጋገራችሁ የምስክሮቹን ጭብጥ ለመረዳት ችለናል በመሆኑም ይህንኑ ጉዳይ መርምረን ለግንቦት 30-2008 ብይን እንሰጥበታለን “ በማለት ለተከሳሾቹ በደፈናው ትህዛዝ በመስጠት ተመልሰዋል።


0 comments:

Post a Comment