Wednesday 29 June 2016

አቶ ሀብታሙ አያሌው አስቸኳይ የዉጭ አገር ሕክምና እንዲያገኙ ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ አሳሰበ

ሰማያዊ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ሕዝብ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ሕክምና እንዲያገኙና ከሀገር እንዳይወጡ የተጣለባቸው ማእቀብ በአስቸኳይ እንዲነሳ አሳስቧል። አያይዞም ሰማያዊ ፓርቲ በላከው ደብዳቢ እንዳሳሰበው “አቶ ሀብታሙ አያሌው በፍርድ ቤት ከሀገር እንዳይወጡ የተጣለባቸው እግድ ተነስቶ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ሳይታከሙ ቢቀሩ በግለሰቡ ሕይወት ላይ ለሚደርሰው አደጋ መንግስት (ሕወሃት) ሃላፊነቱን እንደሚወስድ እናሳስባለን ብሏል”።

አቶ ሀብታሙ አያሌው በድንገት እራሳቸውን ስተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን እስካሁን ከሁለት በላይ ሆስፒታሎች ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ በመግለጽ ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች ልከዋቸዋል። አቶ ሀብታሙ አሁንም እራሳቸውን እንደሳቱ ይገኛሉ።

0 comments:

Post a Comment