እስካሁን ድረስ በገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማጣራት መሰረት ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ
ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውንና ከ10 ሽህ በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች በእስርቤት ሰቆቃ ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመባቸው
እንደሚገኙ ሂውማን ራይትስ ወች ለተ መ ድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በሪፓርቱ ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት
በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች በፋጣኝ ሁኔታ በገለልተኛ አካል ማጣራት እንዲያደርግ ሲል
ጥሪውን አቅርቧል። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በኦሮሚያ ክልል እስካሁን ድረስ በቀጠለው ግድያ፣ የጅምላ እስራት፣
አካላዊ ጥቃት፣ ከትውልድ ቦታ ማፈና
ቀልን የመሳሰሉ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈጽመዋል።
ሂውማን ራይትስ ወች በኢትዮጵያ የመንግስት ታጣቂዎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ ሰለባ በሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ግድያ
ላይ የተሳተፉት ተለይተው በሕግ እንዲጠየቁ ሊደረግ እንደሚገባና ገለልተኛ የምርመራ አጣሪ ቡድን ይቋቋም ዘንድ
የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት እንዲተባበሩ ድርጅቱ ግፊቱን እንዲያደርግ አሳስብዋል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በባንግላዲሽ፣ ታይላንድና በየመን በሳኡዲ መራሹ ጦር የተፈፀመው እልቂት በገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን እንዲመረመር ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ለምክር ቤቱ ጠይቋል።
ለዝርዝሩ የሚቀጥለዉን ሊንክ ይጫኑ
Human Rights situations that require the Council's attention
0 comments:
Post a Comment