Saturday 24 August 2013

ዜና ከባሌ ሮቤ – አራት የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ለውይይት ተጠርተው ታገተው ተለቀቁ

የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን አባላት የሚደርስባቸውን ጫና ተቋቁመው በባሌ ሮቤ የተሳካ ቅስቀሳ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት
“የህዝቡ አቀባበል መንግስት የሚያደርስብንን ጫና ተቋቁመን ስራችንን እንድናከናውን ረድቶናል”
ብለዋል፡፡
በባሌ ሮቤ ከንቲባ ጽ/ቤት አራት የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ለውይይት ተጠርተው ታግተው የነበሩ ሲሆን እነዚሁ የአንድነት ፓርቲ ተወካዮችና የቅስቀሳ ብድን አባላት አሁን የተለቀቁ ቢሆንም በሁለት መኪኖች የተጀመረውን ቅስቀሳ ፖሊሶችና ደህንነቶች በማወክ ላይ እንደሚገኙ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመላክቷል፡፡
በተያያዘ ዜና ታግተው የነበሩትን የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ጉዳይ ለመከታተል ወደ ከንቲባው ጽ/ቤት ያመራው የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ባልደረባ ያሬድ አማረ በጥበቃ ሰራተኞች ተዋክቦ እንዲወጣ የተደረገ ሲሆን እሱን በኮንትራት አሳፍሮ የወሰደው የባጃጅ ሹፌር ግን እስከአሁን በህገወጥ መንገድ ታስሮ ያገኛል፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ536940_705669206116210_1304109982_n

0 comments:

Post a Comment