August 3, 2013
መንግስት አንድነት ፓርቲ በመቀሌ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በኃይል አደናቀፈ፡፡ የመቀሌ ከተማ አስተዳደር በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የአንድነት አመራሮችን በህገወጥ ሁኔታ በማሰር፣ከመቀሌ ለቅቀው እንዲወጡ በማስጠንቀቅ እንዲሁም ቅስቀሳ ሲደረግባቸው የነበሩ ቁሳቁሶችን በአደባባይ በመንጠቅ በመቀሌ በቂ ቅስቀሳ እንዳይደረግ በማድረግ ሰላማዊ ሰልፉን በኃይል አደናቅፏል፡፡ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ኮማንድ ፖስት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ መንግስት በመቀሌ የወሰደውን ህገወጥ እርምጃ በመገምገም በነገው እለት የተጠራውን ሳላማዊ ሰልፍ እንዲተላለፍ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ በቅርቡም በመቀሌ ከተማ በተጠናከረ ሁኔታ ዳግም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ በመወሰን ሰልፉ የሚያደርግበትን ቀን በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ግብረኃይል ጀግናው የመቀሌ አዋሪ የመንግስትን ህገወጥ እርምጃ በማውገዝ ለአንድነት ፓርቲ አመራሮች ያሳየውን አጋርነት በማድነቅ በመቀሌ ከተማ በቅርቡ የሚጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ በንቃት እንዲጠባበቅ ጥሪን አስተላልፏል፡፡
0 comments:
Post a Comment