Friday 9 August 2013

በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ እናወግዛለን! ENTC press release

Ethiopian National Transitional Council
P.O.Box 9929
Alexandria, VA 22304
Tel: 1-571-335-4637
Tel: +44-7958-487-420
Email: contact@etntc.org
Website: www.etntc.org

ነሐሴ 2 2005

               በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ እናወግዛለን! 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት የወያኔ/ኢህአዴግ ስርአት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በምአራብ አርሲ በኮፈሌ
ከተማ በንጹህ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ህጻናት ላይ ያደረሰውን ኢሰብአዊ ጭፍጨፋ በታላቅ ሀዘን ተመልክተናል።
ይህንን የጭካኔ ተግባር ድርጅታችን በጥብቅ በማውገዝ ለሟች ቤተሰቦች ሀዘናችንን እየገለጽን፤ መጽናናትን እንዲሰጥልን
እንጸልያለን። ከሟች ወገኖቻችን በተጨማሪ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች እንደተዘገበው በሺህ የሚቆጠሩት ንጹሃን ዜጎች
ታፈሰው ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል። በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞችም ከፍተኛ ድብደባና እስር በኢድ አልፈጥርም በአል
እየቀጠለ ይገኛል ።
ሙስሊም ወገኖቻችን አምባገነኑ የወያኔ/ኢህአዴግ ስርአት በሃይማኖታቸው ጣልቃ በመግባት የሚያካሂደውን ግልጽ ወረራ
በመቃወም ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ማሰማት ከጀመሩ አመት አስቆጠሩ። ተቃውሞው የእግር እሳት የሆነበት ይህ
አስከፊ ስርአት ቢገድልም፤ ቢያስርም፤ ቢያስፈራራም ትግላቸውን ሊገታው ግን በፍጹም አልቻለም። በቅርቡ በደሴ ከተማ
በሼክ ይማም ኑሩ ላይ የተካሄደው የመግደል ወንጀልም የስርአቱ እጅ እንዳለበት ምስክሮች ይናገራሉ። ዘረኛው ወያኔ አራሱ
የለየለት ሽብርተኛ ሆኖ ድምጻችን ይሰማ፤ ፍትህ ይስፈን የሚሉ ዜጎችን ከሽብርተኞች ጋር ለማዛመድ የሚያደርገውን ዘመቻ
ኢትዮጵያውያን የተለመደው የወያኔ ድራማ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ክርስተያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንም ይህንኑ
በመገንዘብና በወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሳትፈቱ የምታደርጉትን ድጋፍና አንድነት ልትቀጥሉ ይገባል ።
ይህ የጭካኔ ዘመቻ በጀሌዎቻቸው እይተካሄደ በሚገኝበተ ሰአት የህውሃት አመራር አባላት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በመጓዝ
ከጠባብ ዘረኛ አባላቶቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ጋር ሳምንት የፈጀ አስረሽ ምቺው ደስታ ላይ ሰንብተዋል። ከድሃ
አትዮጵያውያን ወገኖቻችን ድሞዝ በግፍ ከሚነጠቀው ገንዘብ ላይ፤ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠር ዶላር በማፍሰስ በየሆቴሉ
በውስኪ ሲራጩ ከርመዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክርቤት ይህንን የዘቀጠ ስርአት በተባበረ ሃይል አሽቀንጥሮ ጥሎ በምትኩ ሁሉን አቀፍ
ሕዝባዊ የሽግግር መንግስት ከመመስረት ውጭ ምንም አይነት መፍትሄ እንደሌለው ያምናል። ከዚህ አላማ ባነሰ ደርጃ
በተለያዩ ወቅታዊ ሂደቶች የሚነሱ ጥያቄዎችን ስርአቱ ለማስተናገድ ምንም አይነት ፈቃደኛነት የሌለው መሆኑን በግልጽ
በማስመስከሩ፤ የተሸራረፉ መብቶች ይገኛሉ በሚል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ዘላቂ መፍትሄ ይሆናሉ ብለን አናምንም። በመሆኑም
መላው የሙስሊም ህብረተሰብና እንዲሁም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በዚህ ስር ነቀል አላማ ዙሪያ እንዲሰባሰቡ ጥሪያችንን
እናቀርባለን።
ኢድ ሙባረክ ለሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን!
አንድነታችን ሃይል ነው!
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት አመራር

0 comments:

Post a Comment