Saturday 24 August 2013

ዜና ከፍቼ፤ በፍቼ የአንድነት ቢሮ በመንግስት ሃይሎች ተሰበረ:: ወጣቱ ሰባሪዎችን አሳፍሮ አባሯል::

የአንድነት ፓርቲ የቅስቀሳ ቡድን መኪናና በባጃጆችን በመጠቀም የተቀናጀ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የፍቼ ከተማ የኢህአዴግ ካድሬዎችና የመንግስት ሹመኞች ህዝቡ ለነገው ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጣ ቤት ለቤት በመሄድ በማስፈራራት ላይ ቢገኙም ህዝቡ በነገው የተቃውሞ ሰልፍ ብሶቱን ለመግለፅ ተዘጋጅቷል፡፡
ዘግይቶ በደረሰን ዜና በፍቼ ከተማ የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የመንግስት የደህንነት ሀይሎች ሰብረው በመግባት በቢሮው ውስት ያሉትን አባላት ቢያባርሩም የፍቼ ከተማ ወጣቶች፣ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ጽ/ቤታቸውን መልሰው ተቆጣጥረውታል፡፡
አንድነት ፓርቲ በአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት እየተወሰደ ያለውን ህገወጥ እርምጃ አውግዞ የፍቼና የአካባቢው ህብረተሰብ በነገው ዕለት በነቂስ በመውጣት የታፈነ ድምፁን እንዲያሰማ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡#Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ1157736_504506602967612_580379237_n

0 comments:

Post a Comment