ዘመንኑ ያለቀበት ስርዓት፣ መዋቅሩ የፈረሰ ስርዓት፣ ሁለመናው እኩይ በሆነ በሕዝብና ሃገር ጥላቻ የተተበተበ ስርዓት፣ የእድሜ ዘመኑ እያለቀና የማስተዳደርና የመምራት አቅም ማጣት ሲጀምር ለስልጣኑና በስልጣን ዘመኑ የመዘበረውን የሕዝብና የሃገር ሃብት ለማስጠበቅ የውር ድንብሩን ዪዳክራል፡፡
ይህው በመቃብር አፋፍ ላይ ያለው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት በሕዝብና በሃገር ላይ ሲያደርስ የነበረውን እጅግ ዘግናኝ ክህደት ከማንም ኢትዮጲያዊ አህምሮ የሚፋቅ ባይሆንም ስርዓቱ ቤሔራዊ ስሜት(ሃገራዊ ስሜት) በማጣቱ ምክኒያት የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ ችግር የተቃወሙ ንፁሃን ዜጎች ወይም እንደ ዜጋ በሃገራቸው ውስጥ በሰላም የመኖር ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በግፈኞች ተነጥቀው ነፃነታቸውን ለማስመለስ ፍትህ የጠየቁ ሁሉ በአሸባሪው ስርዓት አሸባሪ ተብለው ሲፈረጁ መመልከት የተለመደ ድራማ ነው፡፡
ከአመታት በኋላ ፍርሃታቸውን አሸንፈው የወያኔ መናጆ መሆን ይበቃናል ብለው ህገ-መንግስቱ የሚፈቅድላቸውን መብት ለመጠቀም ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ወያኔን እምቢኝ እያሉ ያሉት በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉት ጥቂት የፖለቲካ ድርጅቶች መብታቸውን ተጠቅመው የሚያደርጉት የሰላማዊ ትግል መርህ የዚህን ዘረኛ ስርዓት ማንነት ፍንትው አድርጎ ያሳየን አጋጣሚ ነው፡፡ ምንም እንኳን የኢትዮጲያ ሕዝብ ስለወያኔ ማንነትና ምንነት የጠለቅ ግንዛቤ ቢኖረውም በዚህ ደረጃ በወረደና በዘቀጠ ማፊያ ቡድን እንደምንመራ ማመን በእጅጉ ይክብዳል፡፡
በሃገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ በመታገል ላይ ባሉት፣ በሰማያዊ ፓርቲ ተጀምሮ በኋላም በአንድነት የቀጠለው ሕዝብን የማደራጀትና የማንቃት ብሎም ሕዝብ ለሚደርስበት የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፍትህ መጓደል፣ የሚደርስበትን የመብት ጥሰትና ብሶቱን የሚያሰማበትና ድምፁን የሚያስተጋባበት መድረክ እንዲያገኝ እያደረጉ ያሉት እንቅስቃሴ ይበል የሚያሰኝ ትልቅ እምርታ ነው፡፡
ይህንን ህዝብ ለትግል በማነፅ የግፍ ቀንበሩን ከጫንቃው ላይ ማውረድ የሕዝብ ወገን ነን ከሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡ የትኛውም የትግል ስልት አይነቱ ይለያይ እንጂ ቁርጠኝነትና መስዋትነት ይፈልጋል ስለዚህም አታጋዮቻችን መገንዘብ ያለባቸው የምንጠይቀው የሕዝብ መብት ወያኔ በችሮታ የሚሰጠን የኛ ያልሆነ ሳይሆን ሰብአዊ ፍጡር በመሆናችን ልናገኝ የሚገባን እውንታችን እንደሆነ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ እናም ለእውነት ዋጋ ለመከፈል ዝግጁነት ያስፈልገናል፡፡ ትግሉ በከረረ ቁጥር ዘረኛው ስርዓት ማጣፊያ ሲያጥረው ከሚሊዮናት አሸባሪዎች ጎራ መፈረጁ አይቀርምና፡፡
በሌላ በኩል የህምነት ነፃነታቸውን በዘረኛው ስርዓት የተነጠቀት ሙስሊም ኢትዮጲያዊያን ላለፉት ሁለት አመታት እጅግ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ ሚሊዮናት በመሆን የመብት ጥያቄያቸውን ሲያሰሙ በሕዝብ ንቀት የታወረው ዘረኛው ቡድን ጥቂት አክራሪያን እያለ ሲፈርጃቸው ሰንብቷል፡፡ የሚገርመው ገዥው የህውሃት ቡድን እንደሚለው ሚሊዮናት አሸባሪ ያልባት ሃገር በሰላም አምሽታ ማንጋቷ ነው፡፡
በሰላማዊ መንገድ መንግስት ከእምነታቸው ላይ እጁን እንዲያነሳ ለጠየቁት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ተገቢውን መልስ መስጠት አሻፈረኝ ያለው ህውሃት ተቃውሞዋቸውን በሃይል ለማፈን የቃላት ማስፈራሪያ የጀመረው ልጁምአ ጸሎት ምህምኑ ሲዘጋጅ ነው፡፡
ከስምንት አምታት በፊት ሟቹ መለስ ዜናዊ እነደዚሁ የደም ግብሩን ለመፈጸም ጅሌዊቼ ሁሉ ተጠሪነታቸው ለሱ እንደሆነ በእሱ ቀጥተኛ ትህዛዝ የፈለጉትን ማድረግ ይችላሉ ብሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎችን በጠራራ ፀሃይ እንደቀጠፈ ሁሉ የእሱ እኩይ እራእይ አስፈፃሚዎች ባለፈው አረብ ማለትም ሐምሌ 26 2005 ዓ.ም በመላው ሃገሪቱ አንድ ወጥ የ”ድምፃችን ይሰማ” የተቃወሞ ድምጽ ልማሰማት የወጣው መርሃ ግብር ተከትሎ የወያኔ ፖሊስ እስከ ግድያ ሊደርስ የሚችል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን የሚያመለክት መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ የህንን ሰይጣናዊ የስርዓቱን ተልኮ ለማኮላሸትና አላስፈላጊ መስዋትነት እነዳይከፈል በማሰብ የድምፃችን ይሰማ አስተባባሪዎች ብልጠት የተሞላበት እርምጃ ወስደው የወያኔን እኩይ ተንኮል ቢያኮላሹትም በንፁሃን ደም ለመታጠብ አሰፍስፈው የነበሩት አምባገነን መሪዎች ቅልብ ጀሌዎቻቸውን አሰማርተው በምእራብ አርሲ ዞን በኮፈሌና አካባቢዋ በስላማዊው ሕዝበ ሙስሊም ላይ የፈፀሙት አረመኔያዊ ተግባር የብዙሃንን ህይወት የቀጠፈና ለአካል ጉዳት የዳረገ መሆኑ ሕዝብ በሃገሩ የመኖር መብቱን የሚያሳጣ አስከፊ ድርጊት ነው፡፡
ህውሃት ጀሊዎቹን አሰማርቶ በንፁሃን ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ ግድያዎችን እንዲሁም እስራትና ግርፋትን ሲፈፅም ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ ማነህ ባለ ሳምንት እንዲሉ ዛሬ የኮፈሌ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ነገ በማን ላይና በየትኛው የሃገራችን ክልል እንደሚደገም አናውቅም ግን ይደገማል፡ ዘረኛው ቡድን የሽብር ስሙን ለኛ ሰጥቶ በተግባር እራሱ ያሸብረናል፡፡
ወያኔ የቆሰለ አውሬ ይመስል ደመ ነብሱን ያልነከሰውና ያላቆሰለው የሕብረተሰብ ክፍል የለም ይህንንም መሰረቱ ለበሰበሰው ህልውናው እድሜ ማራዘሚያ ይፈልገዋል፡፡ ከምቼውም ጊዜ በላይ በደልና ግፍ ያንገሸገሸው ሕዝብ መፍትሄ በመሻት ታግሎ የሚያታግለው ቁርጠኛ ድርጅት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አሁን ያለው ተነሳሽነት ለዘመናት ብሶት መልስ ሊሰጥ የሚችል የትግል እንቅስቃሴ ስለሆነ በተቃዋሚ ጎራ ያለን ድርጅቶች በሕዝብ መሃል ውጅንብር እንዳይፈጠርና የዘረኛው ስርዓት መሳሪያ እንዳንሆን በመጠንቀቅ ልዩነታችንን አቻችለን አሁን የጋመውን የሕዝባዊ ትግል ተነሳሽነት ዳር ልናደርስ ይገባል፡
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!
ሞት ለወያኔ!!
0 comments:
Post a Comment