የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜዎቹ ግጭቶች ስለጠፋው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት
እንዲሁም ዜጎች ለእስር ለተዳረጉበት ሁኔታ በልዩ ትኩረት እከታተላለሁ አለ…ለጠፋው የሰዎች ሕይወትም ከልብ ማዘኑን
በኢትዮጵያ የህብረቱ አምባሳደር ተናግረዋል፡፡
በአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ አምባሳደሯ ቻንታን ሀብርቻት የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ቢውል ምርጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም አለመግባባቶች ሲፈጠሩ መንግስት ራሱን ከዜጎች ጋር ለመነጋገር ማዘጋጀት ነበረበት መፍትሄውም ኃይልን ከመጠቀም ይልቅ ጥያቄዎቻችሁ ምንድን ናቸው፣ ምን ላድርግ ማለት ነበረበት ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳን መንግስት ጥያቄዎችን ለማዳመጥ ጆሮውን ክፍት ማድረግ እንደነበረበት አክለው ጠቁመዋል፡፡መንግስት በቅርብ ጊዜ አደርገዋለሁ ብሎ ቃል የገባው ምን ላይ እንዳደረሰው እና የሚያደርገውን ለውጥ እንጠብቃለን ብለዋል፡፡
በስደተኞች ጉዳይም ሁለት አይነት እቅዶችን ማስቀመጣቸው ጠቅሰዋል፡፡በአምባሳደሯ የቅርብ ጊዜ እና የረጅም ጊዜ እቅድ ተብለው ከተቀመጡት መካከል ወደ አውሮፓ መዳረሻቸውን አድርገው በስደት የሚሞቱ አፍሪካውያንም በሜዲትራንያን ባህር ከመስጠም መታደግ የአጭር ጊዜ ዕቅድ ሲሆን የረጅም ጊዜ እቅዳቸው ደግሞ እስከ መንደር ድረስ በመዝለቅ የስራ ዕድል በመፍጠር ወደ ስደት እንዳያማትሩ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ለዚህም ከአፍሪካ 5 አገሮች የተመረጡ ሲሆን ኒጀር፣ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያና ማሊን ተከትላ ኢትዮጵያም ተቀምጣለች፡፡ ህብረቱ ጋዜጠኞችን ዛሬ በደሳለኝ ሆቴል ጠርቶ ስለ ሰላምና ፀጥታና ስደትን ስለመቆጣጠር ሽብርተኝነትን ስለመከላከል፣ ስለኢንቨስትመንትና የአየር ንብረት ለውጥ እየሰራ ስላለው ስራ እና ስለወደፊት እቁዱም መግለጫ ሰጥቷል፡፡

0 comments:
Post a Comment