Thursday 22 September 2016

በጎንደር ከተማ በተለያዩ ቦታዎች ቃጠሎ ሊያደርሱ ነበር የተባሉ ሰዎች ተያዙ

ላለፉት 4 ቀናት የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ በምትገኘው ጎንደር ከተማ ትናንትና ዛሬ የገበያ ቦታዎችን፣ የንግድ ድርጅቶችን እንዲሁም መስሪያ ቤቶችን ሊያቃጥሉ ነበር የተባሉ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ግለሰቦቹ በህወሃት የተላኩ መሆናቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ከትግራይ ክልል እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት የይለፍ ወረቀት እንዳላቸው የአይን እማኞች ተናግረዋል።
የአንዲት ሴትና የአንድ ወንድ ወጣት መያዛቸውን ተከትሎ ህዝቡ ተቃውሞውን ገልጿል።

በከተማው የተሰማሩት ወታደሮች ድረሰው ሁለቱንም ወጣቶች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰደዋቸዋል። እስካሁን ባለን መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል መንግስት ስልጠና ወስደው ግማሾቹ እብድ በመምሰል በጎንደርና በተለያዩ የአማራ ክልል ውስጥ የሽብር ተገባር ሊፈፅሙ ሲሉ ከነ እቃቸው ዘጠኝ የሚሆኑት በጎንደር ህዝብና ሚኒሻ ትብብር ተይዘዋል።




0 comments:

Post a Comment