Friday 30 September 2016

ሕወሓት “ትግሬ አይደለሁም; አማራ ነኝ” ባሉት ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ በአሸባሪነት ክስ ሊመሰርት መሆኑን የሚያሳይ ደብዳቤ ወጣ

(ዘ-ሐበሻ) አማራ ነኝ ስላሉ ብቻ እስር ቤት የገቡት እና የአማራው ተጋድሎ ግንባር ቀደም መሪ ተደርገው የሚወሰዱት ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የአሸባሪነት ክስ ሊመሰርት መሆኑን የሚያሳይ ደብዳቤ ወጣ::

በሶሻል ሚድያዎች የተሰራጨው ይኸው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ለአማራ ክልል ፍርድ ቤት የተጻፈ ደብዳቤ ይልና ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ በተጠረጠሩበት የሽብር ፈጠራ ወንጀል የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ 28 ቀን ቀጠሮ ይሰጠኝ ይላል:: ከደብዳቤው መረዳት እንደተቻለው “ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ” ያሉት ኮለኔሉ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ::

ይህን ተከትሎ በተለይ በአማራ ጉዳይ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው አክቲቭስት አቻምየለህ ታምሩ በኮለኔል ደመቀ ዘውዱ የሽብር ክስ ዙሪያ የሚከተለውን አስተያየት በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል:-
“ፋሽስት ወያኔ እነኮሎኔል ደመቀን “በሽብር ፈጠራ» ክስ ሊመሰርት ነው። በቤተ ወያኔ አማራ ነኝ ማለት በአሸባሪነት የሚያስቀስፍ ወንጀል ስንል ከመሬት ተነስተን አይደለም። የነኮሎኔል ደመቀ ወንጀል አማራ መሆናቸው ብቻ ነው። እነኮሎኔል አማራነታቸውን በአደባባይ በመግለጻቸው ከኦሳማ ቢን ላድን እኩል በአሸባሪነት ክስ ሊመሰረትባቸው ነው። ይህ የወያኔ ልግጫ ዛሬ አማራው እያደረገው ያለውን ትግል የበለጠ በሞትና ህይወት መካከል የሚደረግ ፍልሚያ፤ ላለመሞት ሲል ሊገድለው ከሚመጣ ጨካኝ አውሬ ለመዳን የሚያደርገውን ተጋድሎን ተገቢ ብቻ ሳይሆን ህጋዊም ያደርገዋል።”

0 comments:

Post a Comment