Sunday 22 May 2016

በስዊድን፤ በዴንማርክ፤ በፊላንድ፤ በእንግሊዝ እና በሌሎችም የአውሮጳ ሀገራት የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ኖርዌይ ያመራሉ!!!


በኖርዌይ የተሰናዳው ሰሜን አውሮጳ አቀፉ የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሕዝባዊ ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል! አርበኛው ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በጉጉት እየተጠበቁ ነው! 

በመጭው ጁን 4 በኖርዌይ ኦስሎ የሚካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰሜን አውሮጳ አቀፍ ህዝባዊ ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ኢትዮጵያውያን ተጋባዥ እንግዳ የሆኑትን የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፍ. ብርሀኑ ነጋን በጉጉት እየጠበቁ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን ከስዊድን፤ ከዴንማርክ፤ ከፊላንድ፤ ከእንግሊዝ እና ከሌሎችም የአውሮጳ ሀገራት ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው ኦስሎ ድረስ በመምጣት በዝግጅቱ እንደሚታደሙ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል። የመግቢያ ትኬቶች ከ 98 % በላይ የተሸጡ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ከዝግጅቱ ቀን ቀድመው የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለኮሚቴው እየሰጡ እንዲሁም ቃል እየገቡ የነፃነት ትግሉ ደጀንነታቸው እያረጋገጡ ነው። በዝግጅቱ እለት የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታው በስፋት እንደሚካሄድም ይጠበቃል።

አዘጋጅ ኮሚቴው በዝግጅቱ መታደም ለማይችሉ እንዲሁም ለዓለማቀፍ ረጅዎች የባንክ አካውንት አመቻችቶ ይፋ አድርጓል። ስለዚህ የነፃነት ትግሉን በገንዘብ ለመደገፍ የምትሹ ኢትዮጵያውያን የሚከተለውን የባንክ አካውንት መጠቀም ትችላላችሁ!

Iban number - NO6815037614421
Swift code – DNBANOKKXXX
Account no. – 15037614421

ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕወሓት አገዛዝ ከተደቀነባት የመበታተን አደጋ ለማዳን በረሀ በዱር በገደሉ እየተዋደቁ የሚገኙ የነፃነት አርበኞቻችን የእኛን እርዳታና ድጋፍ በፅኑ ይሻሉ! ስለዚህ በቻልነው ሀቅም ሁሉ የነፃነት ትግሉን ለመደገፍ እንዲሁም ለአርበኞቻችን ያለንን አጋርነት ለማረጋገጥ እንዘጋጅ! ቀኑ እየደረሰ ነው!

አንድነት ሀይል ነው!
ከአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ወደ ፊት!

0 comments:

Post a Comment