Tuesday 10 May 2016

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በብሎገር ዘላለም ወርቃአገኘሁ ላይ አምስት አመት ከአራት ወር የእስር ቅጣት በየነ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዘላለም ወርቃአገኘሁ ላይ አምስት አመት ከአራት ወር የእስር ቅጣት በየነ። ዘላለም እና ጓደኞቹ ከሀገር ውጪ የሚሰጥ የኢንተርኔት ደህንነት ስልጠና ለመውሰድ ማመልከታቸውን ተከትሎ "ለሽብር ተግባር ተሰናድተዋል" ተብለው ከሁለት አመት በፊት ለእስር ተዳርገዋል።

ወጣቶቹ የተከሰሱበት ስልጠና ፈፅሞ ያልተካሄደ ሲሆን አላማውም ከየትኛውም የፖለቲካ ቡድን ጋር የተያያዘ አልነበረም። ዘላለም ለደ ብርሀን ድረ ገፅ ተባባሪ ጦማሪ ሲሆን ከመታሰሩ አስቀድሞ በትምህርት ላይ ነበር። ሌሎቹ ታሳሪዎች ከሳምንታት በፊት ከእስር በነፃ ተሰናብተዋል።

0 comments:

Post a Comment