Wednesday 11 May 2016

የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሃገሩን ጥሎ ተሰደደ


Muluken-tesefaw-hiber-radio

በአገር ቤት የሚታተመው የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሙሉቀን ተስፋው በሚደርስበት ተደጋጋሚ ጫና ባለፈው ሳምንት ከአገር ወጥቶ የተሰደደ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በስዊድን ጥገኝነት መጠየቁ ታውቋል። ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በቀለም ቀንድ ዋና አዘጋጅነቱ ብቻ ሳይሆን ከቀለም ቀንድ በፊትም ይሰራባቸው በነበሩ የፕሬስ ውጤቶች ላይ የሚሰራቸውን ዘገባዎችና የሚያወጣቸውን ጽሑፎች ተከትሎ ተደጋጋሚ ጫና ይደርስበት እንደነበር ለማወቅ ተችላል።

የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በቅርቡ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ በወልቃይት ሕዝብ የሚፈጽመውን የሰብኣዊ መብት ረገጣ ቦታው ድረስ ሄዶ ያጠናቀረውን ዘገባ ተከትሎ፣በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ መሰረት በማድረግ የቀረቡ ተከታታይ ዘገባዎች በወጡ ቁጥር ተደጋጋሚ ማስፈራሪያና ዛቻ ይደርስበት ስለነበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ጫና እየበዛ መምታት ለስደት እንደዳረገው ያገኘነው መረጃ ይገልጻል።

<< የክፉ ሰው ሽንት>> በሚል ርእስ በ2014 መጽሐፍ ጽፎ ለንባብ ያበቃው ጋዜጠኛ ሙሉቀን በአሁኑ ወቅትም በቀጣዩ ሰኔ ወር የሚወጣ ሁለተና መጽሐፉን ጽፎ መጨረሱም ታውቋል። ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በአሁኑ ወቅት ከሚሰራበት የቀለም ቀንድ ዋና አዘጋጅነት በተጨማሪ ቀድሞ በኢትዮ ምሕዳር ጋዜጣ በተሌአዩ ጊዜያት በአገር ቤት ያለውን የሰብኣዊ መብት ረገጣ የሚአጋልጡ ሰፊ ዘገባዎችን ችምር ሲአቀርብ መቆቱ ይታወሳል። ከዚህ ቀደም በሙያው ሳቢያ በ2013 ታስሮ ከፍተኛ ድብደባና እንግልት ደርሶበት እንደነበር በጊዜው ኣለም አቀፍ የሰብዓዊ መብትና የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪዎች የሆኑት አምንስቲ፣ሲፒጄና ፔን ኢንተርናሽናል ሪፖርት ማውታታቸው አይዘነጋም።

0 comments:

Post a Comment