Wednesday 18 May 2016

“የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው” – እየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት)

ከእየሩሳሌም ተስፋው (ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት)

(እየሩሳሌም ተስፋው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ስትሆን፣ በነብርሃኑ ተክለያሬድ መዝገብ ‹ግንቦት 7›ን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ ተይዘዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸው አሁን የመከላከያ ምስክር ለማስደመጥ በቀጠሮ ላይ ናቸው፡፡ እየሩሳሌም ተስፋው ይህንን ደብዳቤ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በግንቦት 7፣ 2008 እንዲታተም ያወጣችው ቢሆንም፤ በተለያዩ እንቅፋቶች በዕለቱ ለሕዝብ ሳይደርስላት ቀርቷል፡፡) 

ነገር ግን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለሕዝብ ድምፅ ሥልጣን ላይ የወጣ ፓርቲ አይደለምና በየዕለቱ የሚፈጠረው ኮሽታ ስለሚያስበረግገው እንዲሁም ንፁኃንን ለማሰር እና ለመግደል ምክንያት ይፈልግ ነበርና ይህ ሕዝባዊ ኃይል እንደተመሠረተ “ሽብርተኛ” ስለፈረጀው መስራቾቹን እንዲሁም ወደሃገር እንዲገቡ የማይፈልጋቸውን ተቃዋሚዎች በዚህ አጋጣሚ “አሸባሪዎች” ሲል ፈረጃቸው፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል ያላቸውን ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሲቪክ ማኅበራት አመራሮች፣ ጦማሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ለም ብለው ጥያቄ እሚያነሱ ዜጎችን ግንቦት 7 በማለት በየወኅኒው እያሰራቸው ይገኛል፡፡

እንግዲህ ይህ ሕዝባዊ ኃይል ከላይ እንደገለጽኩላችሁ አሸባሪ ሊያሰኘው የሚችል ዓላማ፣ ራዕይም ሆነ ተልዕኮ የለውም፡፡ ለሠላማዊ መንገድ የተነጠቀውን መብቱን በሁለገብ ትግል ለማስከበር ዓልሞ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ብቻውን ሕወሓት/ኢሕአዴግ ከወንበሩ እንደማያነቃንቀው እስካሁን የታዩት ሙከራዎች በቂ ናቸው ለዚህም ነው በዚህ ሰዐት ብዙ ወጣቶች ይህን ሕዝባዊ ኃይል በቆራጥነት እየተቀላቀሉት የሚገኙት፡፡

ሕወሓት/ኢሕአዴግ ባወጣው የፀረ-ሽብር ዐዋጅ (በነገራችን ላይ ይህን የፀረ-ሽብር ዐዋጅ ልብ ብላችሁ ካያችሁት ሕወሓት/ኢሕአዴግ ለራሱ ያወጣው ይመስላል፡፡ ለምሳሌ ሽብር በሌለበት ሽብር መንዛት አሸባሪነት ነው ይላል፡፡ ታዲያ በአገር ሠላም፣ በጠራራ ፀሐይ ቦንብ አፈነዱ እያለ documentary የሚሠራ ሕወሓት እንጂ ግንቦት 7 ነው እንዴ? በተረፈ ሁሉንም አንቀፆች ተመለከቷቸው ከግንቦት 7 ይልቅ ለሕወሓት ይቀርባሉና ገና ጫካ እያሉ የሕዝብን ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ በገዛ ሕዝባቸው (በሓውዜን) ላይ የጀመሩት እልቂት በደርግ ማሳበብ፣ አሁንም ከ25 ዓመት በኋላ ሳይቀነስ ሳይጨመር እንዳለ ነው፡፡ አሸባሪ ማነው? እንግዲህ ይህ ሁሉ የተፈፀመው በዚህች ዕለት ነው፡፡ “ግንቦት 7” ይህቺ ቀን የትናንት አሰቃቂ ትዝታችን የዛሬ ክሳችን የነገ ተስፋችን ናት፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተማረ ዜጋ አይገኝም፡፡ ሁሉም ነጻነትን ይናፍቃል፡፡ ነጻ ለመውጣት ግን ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ይፈራል፡፡ የሆነ አካል መጥቶ ነጻ እንዲያወጣው ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን አይችልም፡፡ ነጻ ለመውጣት መጀመሪያ ራስን ከታሰሩበት የፍርሓት እስር ነጻ በማውጣት ትግሉን መቀላቀል ነው፡፡ ድርጅታችን ግንቦት 7 ለነጻነት፣ ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የተቋቋመ ነጻ አውጪ ድርጅት እንጂ አሸባሪ አይደለም፡፡ ስለዚህ በድፍረት እናገራለሁ፡፡ እኔ ግንቦት 7 ነኝ፤ እናንተስ? ሁሌም እንደምለው የታሰረው አካሌ እንጂ ልቤ ቀይ ባሕርን ተሸግሮ ከጓዶቼ ጋር በኤርትራ በረሃ ነው፡፡ ይህቺ ቀን ለብዙዎች ሞት፣ አካል መጉደል፣ እስራት አብቅታለች፡፡ መራራውን ሳያልፉ ጣፋጭ፤ ሳይሞቱ ትንሳኤ የለምና ባለፈው ከመፀፀት ባለፈ እልህ አስይዞን ይህንን ዘረኛና አምባገነን የሽፍታ ቡድን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መንግለን ለመጣል እንዘጋጅ፡፡ ከላይ እንዳልኩት የትላንት ጥቁር ጠባሳ፣ የዛሬ ግርፋትና እስራት፣ የነገ ተስፋ ናትና እንኳን ለዚች ቀን አደረሳችሁ፡፡ ይህች ቀን፣ የነጻነት እንዲሁም የድል ቀናችን እንደምትሆን አልጠራጠርም፡፡ ግንቦት 20 በግንቦት 7 እንደመስሰዋለን!!

የነጻነት ታጋዩ ጀግናው አንዳርጋቸው ፅጌ አንድ ጊቢ ብንኖርም መገናኘት አልቻልንም፡፡ እንኳን አካልህን ወሬህንም በስንት ስቃይ ነው፡፡ እምሰማው ያንተ መታፈን ወያኔ እንደጠበቀው ትግሉን አላሽመደመደውም፡፡ እንደውም፣ ይበልጥ አጦዘው ለኛ ከቤት መውጣት ምክንያት አንተ ነህ፡፡ እኛ የአንተ ፍሬዎች ነን፡፡ ዛሬ ታፍነህ ቀንና ሌሊቱን መለየት የማትችልበት ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም የነጻነት ቀን ቀርባለችና እስከዛው ዕድሜህን ያርዝምልን፡፡

0 comments:

Post a Comment