Monday 30 May 2016

ጋዜጠኛ ውብሸት ምግብ ከበላ 24 ሰዓት አልፎታል

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ‬ የ14 አመት እስር ተፈርዶበት በዝዋይ ማረሚያ ቤት ይገኛል። ውብሸት ትናንት ግንቦት 20/2008 ዓ.ም የታሰረበት ክፍል ሲፈተሽ ጽሁፍ ተገኝቶብሃል በሚል በቅጣት ጨለማ ቤት እንዳስገቡት ባለቤቱ ወ/ሮ ብርሃኔ ተስፋየ ገልጻለች።

ውብሸት ዛሬም ጨለማ ክፍል እንደታሰረ ነው። ይህን በመቃወም ውብሸት የርሃብ አድማ ማድረጉንና የሄደለትን ምግብ መመለሱን ለማወቅ ተችሎአል። ዛሬ ውብሸትን ለማየት የሄዱ ሰዎች “ማየት አትችሉም” ተብለው ተመልሰዋል። ጋዜጠኛ ውብሸት ምግብ ከበላ 24 ሰዓት አልፎታል።

#FreeWubeshetTaye


0 comments:

Post a Comment