
(ዘ-ሐበሻ) አማራ ነኝ ስላሉ ብቻ እስር ቤት የገቡት እና የአማራው ተጋድሎ ግንባር ቀደም መሪ ተደርገው
የሚወሰዱት ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት የአሸባሪነት ክስ ሊመሰርት መሆኑን የሚያሳይ
ደብዳቤ ወጣ::
በሶሻል ሚድያዎች የተሰራጨው ይኸው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ለአማራ ክልል ፍርድ ቤት የተጻፈ ደብዳቤ ይልና
ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ በተጠረጠሩበት የሽብር ፈጠራ ወንጀል የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሰብ 28 ቀን ቀጠሮ
ይሰጠኝ ይላል:: ከደብዳቤው መረዳት እንደተቻለው “ትግሬ አይደለሁም አማራ ነኝ” ያሉት ኮለኔሉ በአሸባሪነት
ይከሰሳሉ::
ይህን ተከትሎ በተለይ በአማራ ጉዳይ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው አክቲቭስት አቻምየለህ ታምሩ በኮለኔል ደመቀ ዘውዱ የሽብር...