Sunday, 31 July 2016

Massive protest held in Gondar city

Tens of thousands marched in Ethiopia’s northwestern city of Gondar on Sunday morning. Residents descended to the city center “piazza” around 9 am. The rally lasted until noontime. In placards and chants, the protesters denounced what they see as putting Amhara people at a disadvantage. Among the slogans in the protest:  “Restore the historic border”, “Wolqait is Amhara”, “Qimant and Amhara are one” and “Return the land given to Sudan”.  ...

Saturday, 30 July 2016

የረሃብ አድማ ላይ ያሉት ብርሃኑ ተ/ያሬድ እና ዮናታን ተስፋዬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

በቂሊንጦ የሚደርስባቸውን በደል በመቃወም ለ9 ቀን የረሃብ አድማ ያደረጉት እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ እና ዮናታን ተስፋዬ ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። እነ ብርሃኑ (ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩስ ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካህሳይ) የቅጣት ማቅለያ እንዲያመጡ ነበር የተቀጠሩት። የተሰጣቸው ቀጠሮ አጭር ስለነበረ እና የእስር ቤቱ አስተደዳደር በሚያደርስባቸው በደል ከቤተሰብ ጋር ባለመገናኘታቸው ማቅለያው ሊደርስላቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል። በተጨማሪም አራተኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ቤተሰቦቹ ሩቅ ሃገር በመሆናቸው ከነሱ ጋር ተነጋግሮ ማቅለያ ለማስገባት ጊዜ ስለሚፈልግ ረጅም ቀጠሮ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ዳኛዋ የተሰጣችሁ ጊዜ በቂ ነው በማለት ከሃምሌ 29 በፊት በቢሮ ማቅለያዎቻቸውን እንዲያስገቡ...

Alarming condition of political prisoners on hunger strike

Political prisoners who were on hunger strike for over a week now have become frail and a wife of one of the prisoners told ESAT that she was worried they were not taken to a hospital. Aselefech Mulatu, wife of Dejene Tafa said the prisoners were instead given intravenous fluid while still in their isolated dark room. Prison administrators have kept nine prisoners of conscience separately from others in a dark room saying they were organizing...

Thursday, 28 July 2016

Wednesday, 27 July 2016

የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ አስቸኳይ ጥሪ እናደርጋለን:: ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ

ከሕገመንግስታዊ አግባብ ዉጭ በዜጎች ላይ የሚወሰዱ የመንግስት እርምጃዎች እንዲቆሙ በፓርቲያችንም ሆነ የትግል ጓዶቻችን በሆኑ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሲሰጡ የቆዩ ጋዜጣዊ መግለጫዎችንና ጋዜጣዊ ኮንፌረንሶች እናስታዉሳለን፡፡ በተለይም የዜጎቻችን ከፊንፊኔ ዙሪያ የማፈናቀል ድርጊት እንዲቆም ሲቀርቡ የቆዩ ተማፅኖዎች የመንግስት ባለሥልጣኖች ጆሮ እንዳልገባ አረጋግጠናል፡፡ በሥልጣን ላይ ያለዉ ሥርአት ደጋፊዎች ጥቂት የማይባሉና ከአንድም በላይ ቤት ሲኖራቸዉ በመኖሪያ ቤት እጦት የሚቸገሩ ዜጎች ቁጥር የትየሌለ መሆኑና እነዚህም ዜጎች ከራሳቸዉና ከልጆቻቸዉ ጉሮሮ ቆጥበዉ የሰሩት መጠለያ፤ ለዚያዉም የክረምቱ ጊዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ ላይ ሲፈርስባቸዉ ማየት ምን ያህል...

Regime forces arresting protesters in West Arsi, Oromo region of Ethiopia

Special Forces of the TPLF regime, locally known as Agazi, were on Tuesday going door to door in towns in West Arsi, Oromo region arresting people suspected of taking part in protests that reignited this week. The Oromo regional administration meanwhile said one woman was killed and five others were injured in the protest that has also resumed in East Hararge. Tensions were high in the West Arsi towns of Dodola, Adaba, and Asasa where there was high presence of federal forces. Security forces killed at least 400 protesters in the last...

Tuesday, 26 July 2016

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ! (የጎንደር ሕብረት መግለጫ)

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በጎንደር የከፈተዉ የዕብሪት ጦርነት የኢትዮጵያን ሕዝብ በባርነት ለመግዛት ያለመዉ ቅጀት ነዉ በቅድሚያ፤ የፍርሃት ጨለማን ደፍረዉ የባንዳ አጋዚ አፋኞችን ዘርረዉ መስዋዕትነት ከፍለዉ ክብር ላላበሱን የጎንደር ኢትዮጵያዊ ሰማዕታት ጀግኖችን ስም እንዘክራለን፦ ጀግና አቶ ሲሳይ ታከለ ጀግና አቶ ሰጠኝ ባብል ከበደ ጀግና አቶ ደሳለኝ ጀግና አቶ ጌታዉ ጎዳናዉ አምዴ ሌሎችም ስማቸዉን ያላገኘናቸው ጀግኖች ሁሉ ስማቸዉ በጎንደር/በኢትዮጵያ የታሪክ የወርቅ መዝገብ እንደሚሰፍር ስንገልጽ ከፍ ባለ ኩራት ነዉ። የዛሬዉ መግለጫችን የሚያተኩረዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ዘረኛ ቡድን የሚያካሂደዉን በጎንደር ክፍለሃገር የተፈጸመዉን አፈና ለመቋቋም የህብረት ተሳትፎ ጥሪያችን ለማስተላለፍ የታሰበ...

Monday, 25 July 2016

በምእራብ አርሲ ህዝባዊ አመጽ እንደገና አገረሸ

የአካባቢው ነዋሪዎች መብታችን ይከበር፣ የታሰሩ ዜጎች በአስቸኳይ ይፈቱ፣ ለአነሳናቸው የፍትህ ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ ይሰጠን፣ በወያኔ መተዳደር አንፈልግም የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በማንሳት ተቃውአቸውን አሰምተዋል። በዳባ፣ ዶዶላ፣ ኢዶ በሚባሉ ከተሞች ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚገኙ መንገዶች ሙሉ በሙሉ በድንጋይ ተዘግተው ውለዋል። በተለይ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ የሚወስደው መንገድ መዘጋት መኪኖች ቀኑን ሙሉ ቆመው እንዲውሉ አድርጓቸዋል።የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው በመሄድና ጥይቶችን በመተኮስ ሰልፎችን ለመበተን የሞከሩ ሲሆን፣ ስለደረሰው ጉዳት ለማወቅ አልተቻለም ...

Saturday, 23 July 2016

በጨለማ ቤት የሚገኙ የህሊና እስረኞች በቂሊንጦ እስር ቤት የረሃብ ኣድማ ላይ ናቸው

በቂሊንጦ እስርቤት "እስረኛ እያሳመፃችሁ ነው" ተብለው ከሌሎች እስረኞች ተለይተው በጨለማ ቤት የሚገኙ የህሊና እስረኞች በቀለ ገርባ፣  ፍቅረማርያም አስማማው፣  ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ አበበ ኡርጌሳ፣ ማስረሻ ታፈረ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ ጉርሜሳ አያና  እና አዲሱ ቡላላ ካለፈው እሮብ ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ ናቸው። እነ አቶ በቀለ ገርባ እና እነ ብርሀኑ ተክለያሬድ ሐምሌ 13 የጀመሩት የረኀብ አድማ 4ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን የፖለቲካ እስረኞቹ ሕይወት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ቤተሰቦቻቸው  ገልጸዋል። ከ9 በላይ የሆኑት እና በቂሊንጦ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በጨለማ ቤት ሆነው ባለ5 ነጥብ ጥሪ አስተላልፈዋል:: ይህን መስዋዕትነት የሚከፍሉት ለሕዝብ...

Two Ethiopians try self-immolation in Cairo

Two Ethiopians tried self-immolation at the headquarters of the UNHCR in Cairo, Egypt after the office refused their request for immigration to a third country. The two Ethiopians came to Egypt escaping from the cruel hands of Ethiopian regime forces cracking down on ongoing uprising in the Oromo region. Police and other Ethiopians at the scene stop the two from killing themselves but video obtained by the Oromo Media Network show one of...

በኢትዮጵያ የሚደረጉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ ተባለ

በኢትዮጵያ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆኑ እና በተለያዩ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በሂደት ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አርብ አሳሰበ። መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገውና በሃገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታዎችን ዙሪያ ሪፖርቱን ያወጣው ፍሪደም ሃውስ፣ መንግስት በብቸኝነት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቁጥጥርን ተግባራዊ ማድረጉ ተቃውሞዎች እንዲቀሰቀሱና እየተባባሱ እንዲሄድ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል። ለወራት በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ወደ አማራና የደቡብ ክልል መዛመቱን ያወሳው ድርጅቱ፣ መንግስት ድርጊቱን ለመቆጣጠር እየወሰደ ያለው እርምጃ በሃገሪቱ ያለውን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አደጋ ውስጥ እንደከተተው...

Thursday, 21 July 2016

People of Borena, south Ethiopia stage protest rally

People in Borena, Oromo region in south Ethiopia held a demonstration on Thursday denouncing the maladministration, corruption and injustice under a tyrannical regime. Students and residents of Yabelo town in Borena have also expressed their outrage that they were being administered by incapable, uneducated and corrupt officials directly appointed by the regime in Addis Ababa. The demonstrators also spoke of lack of infrastructural and educational...

Wednesday, 20 July 2016

እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ተከላከሉ ተባሉ

አርበኞች ግንቦት 7ትን ሊቀላቀሉ ሲሉ መንገድ ላይ ተይዘዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ብርሃኑ ተክለያሬድ ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም የግንባሩ አባል ነው የተባለው ደሴ ካሳይ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኞች ተብለዋል፡፡ 14ኛው ወንጀል ችሎት ውሳኔውን ያስተላለፈው ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮችን ባላቀረቡበት ሁኔታ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችንና የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናትን በመከላከያ ምስክርነት ለማቅረብ አስመዝግበው የነበረ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ምስክሮቻችሁን አቅርባችሁ ማሰማት አትችሉም ብሎአቸዋል። ተከሳሾች በጸረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 652/2001 መሰረት ሃምሌ 22 ቀን 2008 ዓም የፍርድ ውሳኔ እንደሚያገኙ ፍርድ ቤቱ ወስኗል። ...

ለአቶ በረከት በቅርበት የምትሰራው ጋዜጠኛ ሳምራዊት ስንታየሁ ተሰደደች – የመንግስት ጋዜጠኞች ስርዓቱን ጥለው መኮብለሉን ተያይዘውታል

                                                                 ሳምራዊት ስንታየሁ (ዘ-ሐበሻ) በታች በኦሮሚያ በኩል በላይ በጎንደር በሕዝብ አመጽ የተወጠረው የሕዝባዊ...

ኢሕአፓ ለጎንደር ሕዝብ ትግል ሙሉ ድጋፉን ያረጋግጣል

ኢሕአፓ የትግል ታሪክ ውስጥ ጎንደርና የጎንደር ሕዝባ ያላቸው ቦታ ከፍተኛ ነው። የጎንደር ሕዝብ ኢሕአፓንም ሌሎች ሀገር ወዳድ ድርጅቶችንም ደግፎ ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍሏል። . . . የጎንደር የሰማዕት ታሪክ የኢሕአፓ ታሪክ ማዕክል ሆኖም ቆይቷል። ኢሕአፓ በጎንደር እየተካሄደ ያለውን ጸረ ወያኔ ትግል ሙሉ በሙሉ ይደግፋል። . . . ወቅቱ የመራራና የቆራጥ ትግል ወቅት ነው። ወያኔ ሕዝብን በጅምላ በመፍጀት ትግሉ ለማፈን መጣሩ የሚጠበቅ ነው። በግድ ወደ ትግራይ የተጠቃለለው መሬትና ማንነቱ የተካደውም ሕዝብ ቆርጦ መነሳቱ የሚመሰገን ነው። የአፍራሽና የቅጥረኞች አዞ እንባ ረግጦ ትግልን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ትግልን ለሚያውቀው የጎንደር ሕዝብ ሊያስተምር የሚቃጣ ሊኖርም አይችልም። ከጎንደር...

Thursday, 14 July 2016

አርበኞች ግንቦት 7 ለጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ

አርበኞች ግንቦት 7 መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው የጎንደር ህዝብ አጋርነቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በምስልና ድምፅ ከኤርትራ ረቡዕ ዕለት ባስተላለፉት መልዕክት የአማራም ህዝብ ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል። የወልቃይት ህዝብ ማንነቱን በተመለከተ በህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያቀረበው ጥያቄ በህወሃት በኩል የሃይል ምላሽ መሰጠቱ የቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደግጭት ማምራቱን በጥሪያቸው ያስታወሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በጎንደር የታየው ህዝባዊ ዕምቢተኝነት በስርዓቱ ሰለባ ለሆኑትና ለውጥ ለሚሹ ሁሉ መነቃቃትን የፈጠረ እንደሆነ አመልክተዋል። “ከተባበርን አንጸናለን፣ ከተከፋፈልን...

Wednesday, 13 July 2016

The Revolt in Gondar, Ethiopia continued for the second day

In one of the deadliest days in the town of Gondar, northern Ethiopia, six residents and four members of regime forces were killed on Tuesday.Deadliest days in the town of Gondar, northern Ethiopia. The killings began when TPLF forces from Tigray came to the town of Gondar in the wee hours of the morning on Tuesday and apprehended four members of a committee that spearheads the political demands by the people of Wolkait and Tegede as regards their...

በጎንደር ህዝባዊ አመጹ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል

ትናንት እስከ ምሽቱ አራት ሰአት በተደረገው የተኩስ ልውውጥ በርካታ የህወሃት ታጣቂዎች ተገድለዋል። ጥቃቱን የፈጸሙት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎችን ለመታደግ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ጎንደር ከተማ የገቡ ነዋሪዎች ናቸው። በተኩሱ ልውውጥ መሃል ከወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ አቅራቢዎች መካከል አቶ ሲሳይ ታከለ፣ አቶ ሰጠኝ፣ አቶ አለቃ እስበሶም እና ሌሎች ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎችም ሲገደሉ፣ በፌደራል ፖሊስና በህወሃት ደህንነት አባላት በኩል ደግሞ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶች እንደተገደሉም መረጃዎች እየወጡ ነው። ተቃውሞው ዛሬም የቀጠለ ሲሆን አንድ የህወሃት የንግድ ድርጅትና አንድ የፌደራል ፖሊስ መኪና መቃጠላቸው ታውቋል። በተጣቂዎች...

Monday, 11 July 2016

ዜጎችን ማፈናቀል መግደልና ማሰደድ የህወሃት አይነተኛ መግለጫዎች ናቸው!!! (አርበኞች ግንቦት 7)

ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ አንስቶ በአገራችንና በህዝባችን ላይ ሲፈጽም የቆየውና እየፈጸመ ያለው ግፍና ስቃይ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደልም። አፈና ፣ እስር፣ ግድያና ዜጎችን ማፈናቀል አይነተኛ መግለጫዎቹ የሆነው ይህ የህወሃት አገዛዝ፣ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችንና የከተማ ቦታዎችን በመቸብቸብ ሃብት ለማካበት ባለው ዕቅድ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬና የትውልድ መንደሮቻቸው በግፍ እንዲፈናቀሉ አድርጎአል። አሁንም እያደረገ ነው ። ሰሞኑን በአዲስ አበባ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ቀርሳና ኮንቶማ በተባሉ ቀበሌዎች ከ30 ሺ በላይ የሚገመት ህዝብ ለአመታት ከኖረበት መኖሪያ ቤቶች በሃይል ተገፍትረው በመውጣት ጎዳና ላይ እንዲበተኑ ተደርጎአል።...

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በመከላከያ ምስክርነት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ሰበር ችሎት አዘዘ

በሽብር ድርጊት ወንጀት ተጠርጥረው በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን በተሰጠባቸው በእነ ዘመኑ ካሴ መዝገብ አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁንና አቶ አንሙት የኔዋስ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቀርበው እንዲመሰክሩ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አዘዘ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠውን የመጨረሻ ትዕዛዝ መሠረት በማድረግ፣ ክሱን ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት፣ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ባስተላለፈው ትዕዛዝ፣ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን ሐሙስ ሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ያቅርብ ብሏል፡፡ የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የነበሩት...

Saturday, 9 July 2016

U.S. Senators condemn Ethiopian abuses, urge ‘review’ of security assistance

(REPRIEVE)— A US Senate Committee has given initial approval to a Senate resolution calling on the White House to review American assistance to Ethiopia, amid concerns over the kidnap and detention of activist Andy Tsege and other abuses in the country.UK “stands shoulder to shoulder” with EthiopiaThe resolution, ‘Supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia’, is set for a vote in the full Senate during this...

Thursday, 7 July 2016

An open letter to Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus, Minister of Foreign Affairs

SMNE urges Minister Tedros Adhanom to take swift and comprehensive action in helping Ato Habtamu Ayelaw gets proper treatment abroad and addressing the shameful treatment of the Ethiopians who are forced from their homes, resulting in wide scale displacement, homelessness and desperate life and health conditions. July 6, 2016 Dr. Tedros Adhanom Ghebreyesus Minister of Foreign Affairs Federal Democratic Republic of Ethiopia Addis Ababa, Ethiopia.                                                                       ...

Wednesday, 6 July 2016

የአዲስ አበባ መስተዳድር ዜጎችን የማፈናቀሉን እርምጃ እንዲያቆም የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ጠየቀ

የአዲስ አበባ መስተዳድር ዜጎችን የማፈናቀሉን እርምጃ እንዲያቆም የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) ጠየቀ አብዛሃኞቹ ዜጎች ካርታ ባይኖራቸውም ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸውንና የመብራትና ውሃን የመሳሰሉትን አገልግሎቶችን ሲያገኙ እንደነበር ሰመጉ ገልጿል። “እነዚህ ዜጎች አስቀድሞ ሕጋዊነትን በያዘ መልኩ መኖሪያዎችን እንዲሰሩ መደረግ ነበረበት። ይህ ከሆነ በኋላ ሕገወጥ ናችሁ በማለት አፍራሽ ግብረኃይል አሰማርቶ በክረምት ነዋሪዎች ላይ ቤት ማፍረስ ኢሰብዓዊ ነው” ሲል ሰመጉ ድርጊቱን በጽኑ ኮንኗል። በ አፍራሽ ግብረኃይሉ ቤቶቻቸው በክረምት ወራት የፈረሰባቸው ዜጎች ቁጥራቸው ከአስር ሽህ እንደሚበልጥና ታዳጊ ሕጻናትና አዛውንት ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን...

Exiled prominent journalist, activist wrote open letter to Ethiopia’s security chief

Exiled prominent journalist, activist wrote open letter to Ethiopia’s security chief following threats to their family back home by security operatives Exiled journalist Sisay Agena and Tamagn Beyene, an activist and a well-known critic of the Ethiopian government wrote an open letter to the country’s security chief, Getachew Asefa following intimidation against their family back home in order to silence their criticism of the government. ...

Tuesday, 5 July 2016

Security forces detain hundreds protesting home demolition

Security forces have detained over 200 people in the capital Addis Ababa after thousands of homes, deemed illegal by the government, were demolished. Six people, including two police officers, were killed in the confrontation last week and authorities are carrying out mass arrests in connection with the killings of the officers. The residents said the regime was indiscriminately arresting citizens who had nothing to do with the killing of...

ከኦሮሚያ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ዜጎች ቁጥር 50ሺህ እንደሚደርስ ዶ/ር መረራ አስታወቁ

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ከመንፈቅ በላይ የዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ወደ እስር ቤት የተጋዙ ዜጎች ቁጥር ከ40ሺህ እስከ 50ሺህ እንደሚገመት የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ። ወጣቶቹ በስርዓቱ ላይ ተቃውሟቸውን ከሚገልጹባቸው መንገዶች አንዱ ባለስልጣናት ስርዓቱን እንዲያወግዙና መንገድ በድንጋይ እንዲዘጉ ማስገደድ እንደነበርም አመልክተዋል። ኦህዴድ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ መስከረም ወር ላይ ስራ ጀምሮ፣ በህዳር ወር የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ስለምርጫው ውጤት በራሱ የሚናገረው ነገር መኖሩን ያመለከቱት ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ ምዕራብያውያኑ በምርጫው ከ50 እስከ 60 ወንበር ለተቃዋሚዎች ይለቀቃል የሚል ዕምነት እንደነበራቸውም አስታወሰዋል።  ምርጫው በኢህአዴግ...

Sunday, 3 July 2016

Journalist Reeyot Alemu roasted TPLF agent Gebrekiros Abraha

A few weeks ago Ethiopians from all walks of life gathered in Nashville, Tennessee, to support ESAT and discuss issues of concern. Reeyot Alemu known for her courage and unwavering stand against tyranny was a guest of honor. Gross human rights violations was top on the agenda. The inconvenient truth was too uncomfortable for a TPLF spy who sneaked in the meeting hall. The TPLF agent, who even worked at the spying entity called Information Network Security Agency, was full of himself. Gebrekiros Abraha, wanted to lecture and dictate what freedom-loving...

Saturday, 2 July 2016

በናይሮቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የረሀብ አድማ አደረጉ

በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ሀብታሙ አያሌው እገዳው ተነስቶለት የውጪ ህክምና እንዲያግኝ በናይሮቢ-አምነስቲ ቢሮ ፊትለፊት በረሀብ አድማ ጥያቄ ሲያቀርቡ ዋሉ። ሥርዓቱ በፈጠረባቸው ጫና ለስደት የተዳረጉት እነኚህ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች በቀድመው አንድነት ፓርቲ አመራር በሀብታሙ አያሌው ምስል የተሰራ ቲሸርት በመልበስ ፤በቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራር በሀብታሙ አያሌው ላይ የተጣለበት የፍርድ ቤት እግድ እንዲነሳና በውጪ ሀገር ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ የሰብዓዊ መብት ተቋሙ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ሀሳባቸውን በነጻ በመግለጻቸውና ሙያቸውን ተግባራዊ በማድረጋቸው ሳቢያ በአገዛዙ አለስቃይና እንግልት የተዳረጉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችና...

Friday, 1 July 2016

በአወዳይ በተነሳው ተቃውሞ ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 4 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት) በምስራቅ ሃረርጌ በአወዳይ ከተማ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው አስተዳዳሪ በከፈተው ተኩስ  ሁለት ህጻናት እና  አንድ ጎልማሳ ተገድለዋል። ነዋሪዎች ማምሻውን ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የሟቾች ቁጥር 7 ድርሷል። ኢብራሂም ሙሜ የሚባል ባለ ጸጉር ቤት እና አህመድ አልዬ የሚባል ባለሞባይል ቤት አሊ መሰራ ህንጻ እና አዋሽ ባንክ መሃል የሚገኘው ቤታቸው  ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ሌሊት ላይ መቃጠሉን ተከትሎ ህዝቡ ለተጎጂ ቤተሰቦች የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰብ ሲጀምሩ ፖሊሶች ጣልቃ ገብተው ለምን ተሰባሰባችሁ በማለት ተኩስ ከፍተዋል። የአወዳይ 01 ቀበሌ ሊቀመንበር የሆነው አቶ አብዲ እድሪስ በከፈተው ተኩስ ሁለት ህናጻንት ጨምሮ 3 ሰዎች ተገድልዋል።  ፌደራል...