Saturday 23 July 2016

በጨለማ ቤት የሚገኙ የህሊና እስረኞች በቂሊንጦ እስር ቤት የረሃብ ኣድማ ላይ ናቸው

በቂሊንጦ እስርቤት "እስረኛ እያሳመፃችሁ ነው" ተብለው ከሌሎች እስረኞች ተለይተው በጨለማ ቤት የሚገኙ የህሊና እስረኞች በቀለ ገርባ፣  ፍቅረማርያም አስማማው፣  ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ አበበ ኡርጌሳ ማስረሻ ታፈረ ደጀኔ ጣፋ፣ ጉርሜሳ አያና  እና አዲሱ ቡላላ ካለፈው እሮብ ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ ናቸው።

እነ አቶ በቀለ ገርባ እና እነ ብርሀኑ ተክለያሬድ ሐምሌ 13 የጀመሩት የረኀብ አድማ 4ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን የፖለቲካ እስረኞቹ ሕይወት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን ቤተሰቦቻቸው  ገልጸዋል።

ከ9 በላይ የሆኑት እና በቂሊንጦ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በጨለማ ቤት ሆነው ባለ5 ነጥብ ጥሪ አስተላልፈዋል::
ይህን መስዋዕትነት የሚከፍሉት ለሕዝብ ነውና ሕዝቡ ከጎናቸው እንዲቆም ቤተሰቦቻቸው ጥሪ አቀርበዋል።

0 comments:

Post a Comment