Wednesday, 20 July 2016

ኢሕአፓ ለጎንደር ሕዝብ ትግል ሙሉ ድጋፉን ያረጋግጣል

ኢሕአፓ የትግል ታሪክ ውስጥ ጎንደርና የጎንደር ሕዝባ ያላቸው ቦታ ከፍተኛ ነው። የጎንደር ሕዝብ ኢሕአፓንም ሌሎች ሀገር ወዳድ ድርጅቶችንም ደግፎ ከፍተኛ መስዋዕትነትን ከፍሏል። . . . የጎንደር የሰማዕት ታሪክ የኢሕአፓ ታሪክ ማዕክል ሆኖም ቆይቷል። ኢሕአፓ በጎንደር እየተካሄደ ያለውን ጸረ ወያኔ ትግል ሙሉ በሙሉ ይደግፋል። . . . ወቅቱ የመራራና የቆራጥ ትግል ወቅት ነው። ወያኔ ሕዝብን በጅምላ በመፍጀት ትግሉ ለማፈን መጣሩ የሚጠበቅ ነው። በግድ ወደ ትግራይ የተጠቃለለው መሬትና ማንነቱ የተካደውም ሕዝብ ቆርጦ መነሳቱ የሚመሰገን ነው። የአፍራሽና የቅጥረኞች አዞ እንባ ረግጦ ትግልን መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ትግልን ለሚያውቀው የጎንደር ሕዝብ ሊያስተምር የሚቃጣ ሊኖርም አይችልም። ከጎንደር ሕዝብ ጎን በተጨባጭ መቆም ጊዜው አሁን ነው። ሀገርን ማስመለስና ድንበርን ማስከበር፤ ማንነትን ማስረገጥ ለነገ የሚባል ትግል አይደለም። በመሆኑም ኢሕአፓ በአካባቢው ያሉትን አባላትና ደጋፊዎች የትግሉ አካል ሆነው እንዲሰለፉ ጠርቷል። በሰበብ አስባቡም ከወያኔ ጎን ቆመው የነበሩትም በጊዜ ከሕዝብ ጎራ እንዲቀላቀሉም ጥሪ ያደርግላቸዋል። ይህ ጸረ ወያኔ ትግል መጠቃት የለበትምና ሀገር ወዳድ ሀይሎች ሁሉ–በያሉበት–ሊታደጉት፤ ሊረዱት፡ ሊያጠናክሩት መነሳት አለባቸውም ይላል። ሙሉውን መግለጫ ያንብቡ …

0 comments:

Post a Comment