Saturday, 30 July 2016

በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ጉዳይ ዐቃቤ ህግ ያዘጋጃቸው ምስክሮች እንዳይሰሙ ፍርድ ቤት አዘዘ


                                                                            ዮናታን ተስፋዬ
የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በነበረው በአቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ ዐቃቤ ህግ ያዘጋጃቸው ምስክሮች መሰማት እንደማያስፈልጋቸው ፍርድ ቤቱ ወሰነ። ለብይንም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
አቶ ዮናታን ያቀረበውን አዲስ አቤቱታም በጽሑፍ እንዲያስገባ ፍርድ ቤቱ አዟል።
በቂሊንጦ ማረምያ ቤት ሰብአዊ መብቶቻችን ተጥሰዋል ብለው ባለፉት ዘጠኝ ቀናት በረሃብ አድማ ላይ ከነበሩት ዘጠኝ ሰዎች መካከል አንዱ እና የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በነበረው አቶ ዩናታን ተስፋዬ ላይ ዐቃቤ ሕግ ቀጥሯቸው የነበሩት ሁለት ምስክሮች እንዳይሰሙ ፍርድ ቤቱ በየነ።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
http://amharic.voanews.com/pp/3440622/ppt0.html 

0 comments:

Post a Comment