Thursday, 1 October 2015

እነ ሃብታሙ አያሌው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አርብ ይቀርባሉ

ሽብርተኛ ናችሁ በሚል ክስ ተከሰው ከአመት በላይ በወህኑ የማቀቁት ታዋቂ የፖለቲክ መሪዎች፣ ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታም የሺዋስ አሰፋና ዳን ኤል ሺበሺ ፍርድ ቤት ሽብርተኛ ስለመሆናቸው የሚያሳይ ምን አይነት መረጃ አልቀረበም በሚል በነጻ እንዲለቀቁ መወሰኑ ይታወቃል።

ፍርድ ቤቶች፣ መረጃ ሳይኖር ዜጎችን ጥፋተኛ ማለት የለመደባቸው፣ ዳኞች ሕግን መርምረው የሚፈርዱ ሳይሆን የፖለቲካ ዉሳኔ የሚያነቡ መሆናቸው ይታወቃል። እነ ሃብታሙ እንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱ ሲወስን፣ ፍርድ ቤቱ እንደዚያ እንዲወስን ታዞ እንደሆነ አያጠያይቅም።

ሆኖም አንዱ ፍርድ ቤት በመመሪያ ታዞ ፣ ዉሳኔ ከሰጠ በኋላ ፣ አቃቢ ሕግ ይግባኝ ማለቱና ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም ጉዳይ እስኪታይ በ እሥር እንዲቆዩ መወሰኑ፣ ወይም አንዱ ባለስልጣን የወሰነዉን ሌላው ባለስልጣን ሰርዞት ፣ አሊያም አገዛዙ እንደውም ለይስሙላ “ፍርድ ቤቶች ነጻ ናቸው፣ አቃቢ ሕግን ያልፈለገውን ወሰኑ” የሚለውን ለማስወራትታስቦ እንደሆነ ብዙዎች ያናገራሉ።

Millions of voices for freedom - UDJ's photo.Millions of voices for freedom - UDJ's photo.Millions of voices for freedom - UDJ's photo.

0 comments:

Post a Comment