Tuesday 26 July 2016

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ! (የጎንደር ሕብረት መግለጫ)

የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በጎንደር የከፈተዉ የዕብሪት ጦርነት የኢትዮጵያን ሕዝብ በባርነት ለመግዛት ያለመዉ ቅጀት ነዉ
በቅድሚያ፤ የፍርሃት ጨለማን ደፍረዉ የባንዳ አጋዚ አፋኞችን ዘርረዉ መስዋዕትነት ከፍለዉ ክብር ላላበሱን የጎንደር ኢትዮጵያዊ ሰማዕታት ጀግኖችን ስም እንዘክራለን፦

ጀግና አቶ ሲሳይ ታከለ
ጀግና አቶ ሰጠኝ ባብል ከበደ
ጀግና አቶ ደሳለኝ
ጀግና አቶ ጌታዉ ጎዳናዉ አምዴ

ሌሎችም ስማቸዉን ያላገኘናቸው ጀግኖች ሁሉ ስማቸዉ በጎንደር/በኢትዮጵያ የታሪክ የወርቅ መዝገብ እንደሚሰፍር ስንገልጽ ከፍ ባለ ኩራት ነዉ።

የዛሬዉ መግለጫችን የሚያተኩረዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ዘረኛ ቡድን የሚያካሂደዉን በጎንደር ክፍለሃገር የተፈጸመዉን አፈና ለመቋቋም የህብረት ተሳትፎ ጥሪያችን ለማስተላለፍ የታሰበ ነዉ። መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያዉቀዉ፤ የወልቃይት ጠገዴን/ጠለምት ህዝብ የ30 ዓመታት የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ግፍ ተፈጽሞበታል። በተመሳሳይ መልኩ በሌሎችም የኢትዮጵያ ምድር ያሉ ዜጎች ሁሉ የወያኔ እስረኛ ከሆኑ 25 ዓመታት ተቆጥሯል።

በወለጋ፤ በጋምቤላ፤ በአፋር የመሬት ቅርምት ሰለባ የሆኑ ወገኖቻችን፤ በአዲስ አበበባና አካባቢዊ ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ዝናብ እየወረደባቸው የተበተኑና ስደተኛ የሆኑት፤በሃረር ፤በጎንጎፋl በኤሊባቡር በአሪሲ፤ በባሌ፤ በሃረር ፤ በኡጋዴን፤ በትግራይ፤ በጎጃም መተከል በወያኔ አጋዚ የሚገደለዉ፤ የሚታሰረዉ ፤የሚሰደደዉ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊያን የተዋረዱበት ዘመን ቢኖር በወያኔ ዝመን ነው።
[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]


0 comments:

Post a Comment