
Abraha desta
ከተወሰኑ የኢትዮዽያ ፖለቲካ ተንታኞችና ጋዜጠኞች ጋር የመነጋገር ዕድል አጋጥሞኝ ነበር። እነኚህ ሰዎች በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት (ወይም ብዬ አስባለሁ) ከሀገር እንዲወጡ የተደረጉ ናቸው፤ ለምሳሌ መስፍን ነጋሽ (Mesfin Negash)።ከነ መስፍን ጋር የኢትዮዽያ ፖለቲካ በተመለከተ ከጓደኞቼ ጋር ሁነን ሓሳብ ለሓሳብ ተለዋውጠናል። የነሱ የፖለቲካ ሓሳብና ትንታኔ ካዳመጥኩ በኋላ ግራ ገባኝ፤ ልዩነታችን ምን ላይ መሆኑ መለየት አቃተኛ። እነሱ (መስፍንና ሌሎቹ) የሚናገሩት ነገር የኔ ሓሳብ ነው (አብዛኛው የትግራይ ህዝብም የሚጋራው ይመስለኛል)።በኋላ ግን አንድ ነገር ገባኝ፤ የተለያየ ቋንቋ የምንናገር፣ በተለያየ ባህል ያደግን ዜጎች ብንሆንም ሓሳባችንና የፖለቲካ አመለካከታችን ይመሳሰላል።...