Monday, 31 October 2016

“በቂሊንጦ ማ/ቤት በደረሰው እሳት ቃጠሎ ወቅት 67 ሰዎች ተገድለዋል / ሞተዋል”

(የኢሰመፕ ልዩ ዘገባ)

በኢትዮጵያ የፌደራሉ መንግስት ከሚያስተዳድራቸው ቃሊቲ፣ ዝዋይና ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤቶች በተጨማሪ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙ እስረኞችን የያዘው ‹የቂሊንጦ ጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር› በርካታ ተጠርጣሪዎች (እስረኞች) የሚገኙበት እስር ቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ እስር ቤት 3000 ገደማ እስረኞች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ በሽብር የተከሰሱና ሌሎች የፖለቲካ እስረኛ ናቸው፡፡

ቂሊንጦ እስር ቤት የኦፌኮ ም/ፕሬዚዳንት አቶ በቀለ ገርባ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የቀድሞው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ፣ ጋዜጠኞቹ ካሊድ መሃመድ፣ ጌታቸው ሺፈራውና ዳርሰማ ሶሪ እንዲሁም ሌሎች በርካታ የፖለቲካ አመራሮችና አክቲቪስቶች ታስረው የሚገኙበት ነው፡፡

ይህ እስር ቤት በያዝነው አዲስ አመት ዋዜማ (ነሀሴ 2008) ላይ የእሳት ቃጠሎ ደርሶበት እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህ ቃጠሎ የተነሳ በወቅቱ የተጎዱ ሰዎች ማንነትና መጠን በታሰበው ፍጥነት ቶሎ ሳይገለጽ ቢቆይም የኋላ ኋላ መንግስት በቃጠሎው ወቅት በእሳት ተቃጥለውና ‹ለማምለጥ ሲሞክሩ የተገደሉ› በሚል 23 ሰዎች መሞታቸውን ገልጾ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት ባደረገው ማጣራት በወቅቱ ከተፈጠረው እሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ 67 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ሟቾች ውስጥ በቃጠሎ የሞቱት 22 ሰዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ  45 ሰዎች ‹‹ሊያመልጡ ሞክረዋል›› በሚል በመንግስት ታጣቂዎች (የማ/ቤቱ ጠባቂዎች) የተገደሉ ናቸው፡፡

በወቅቱ ህይወታቸውን ካጡ ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ በጭስ ታፍነው የጤና መታወክ የገጠማቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ለአብነትም በእነ ከድር መሃመድ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦበት በጊዜ ቀጠሮ ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ የመተንፈሻ አካሉ ላይ በገጠመው የጤና መታወክ ህክምና ላይ ይገኛል፡፡

ከቃጠሎው ማግስት

በቂሊንጦ የደረሰውን ቃጠሎ ተከትሎ የእስረኛ ቤተሰብ፣ ዘመድና ጓደኞች ለቀናት የጭንቅ ቀናትን አሳልፈዋል፤ እያሳለፉም ነው፡፡ በወቅቱ በደረሰው ቃጠሎ ወቅት የእስረኞችን በህይወት መኖርና አለመኖር ማረጋገጥ አዳጋች ሆኖ፣ ያለምንም መረጃ ቤተሰብ በየዕለቱ ወደቂሊንጦ ሲንከራተቱ ቆይተዋል፡፡ ይህን በማድረጋቸውም ጭንቅ ላይ የሚገኙ የእስረኛ ቤተሰቦች ላይ ‹ለምን ትጠይቃላችሁ› በሚል ድብደባና እስር ደርሶባቸዋል፡፡

መንግስት በወቅቱ በቂሊንጦ የነበሩ (በህይወት የተረፉትን) እስረኞችን ወደተለያዩ እስር ቤቶች ለማዘዋወር ተገድዷል፡፡ ይህንንም ዘግይቶም ቢሆን ለእስረኛ ቤተሰቦች አሳውቋል፡፡ ሆኖም የእስረኛ ቤተሰቦች ከቃጠሎው ወዲህ የሚደርስባቸው እንግልት አልቆመም፡፡ ከዚህ የከፋው እንግልትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ ያለው ግን በእስረኞች ላይ ነው፡፡

ወደ ዝዋይና ሸዋሮቢት እንዲዘዋወሩ የተደረጉት እስረኞች የተለያዩ የሰብዓዊ ክብርን የሚያዋርድ ተግባር እንደተፈጸመባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዝዋይ የተዘዋወሩት እስረኞች ለአስር ቀናት ያህል ካቴና ከእጃቸው ሳይፈታ በእስር አሳልፈዋል፡፡ እነዚህ እስረኞች ሁለት፣ ሁለት ሆነው በአንድ ካቴና ታስረው መጸዳጃ ቤት ሲሄዱም፣ ሲመገቡና ሲተኙ ሳይቀር በእስር አንድ ላይ ሆነው እንደነበር ተረጋግጧል፡፡

እስረኞቹ ከምግብ ሌላ ማናቸውም ነገሮች እንዳይገቡላቸው ተከልክለው፣ ጠያቂዎቻቸውን ከ3 ደቂቃ በላይ እንዳያነጋግሩ ተደርገው ሰንብተዋል፡፡ በተለይም እየደረሰ ያለውን ግፍ በተመለከተ የተናገረ ሰው አሸዋ ላይ ራቁቱን ሆኖ ግርፋት ይፈጸምበት ነበር፡፡ አሸዋ ላይ የሚገረፈው እስረኛ ውሃ እየተደፋበት ሰውነቱ አሸዋውን እንዲይዘው ተደርጎ፣ ከዚያም ሰውነቱን እንዳይታጠብ ተገድቦ በስቃይ እንዲቆይ ይደረጋል፡፡ በጠባብ ክፍል ውስጥ በርካታ እስረኞችን በማጨቅ ሰው በሰው ላይ ተደራርቦ እንዲተኛ ተገድዶ ነበር(በተለይ ዝዋይ)፡፡

ሸዋሮቢት የተዘዋወሩትም ቢሆን ተመሳሳይ በደል እንደተፈጸመባቸው ነው ማረጋገጥ የተቻለው፡፡ በዚሁ እስር ቤት የቆይ እስረኞች አንዳንዶቹ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ከመፈጸሙ ጋር በተያያዘ ቤተሰብ ሊጠይቃቸው በሄደ ወቅት አንድ ክፍል ውስጥ አስቀምጠው በመስኮት ከወገብ በላይ ብቻ እየታዩ ‹አለሁ› እንዲሉ መገደዳቸውን ከቤተሰቦቻቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

የእስረኞቹ ወደቂሊንጦ መመለስ

ጥቅምት 2009 ዓ.ም መግቢያ ጀምሮ ወደተለያዩ እስር ቤቶች ተበትነው የነበሩ ተጠርጣሪዎች ወደ ቂሊንጦ መመለስ ጀምረዋል፡፡ ሆኖም ግን የቂሊንጦ ማ/ቤት አስተዳደር እስረኞችን ፍ/ቤት እያቀረበ አይደለም፡፡ ይህ ሪፖርት እስከተዘጋጀበት ዕለት ድረስ እስረኞች በፍ/ቤት ቀጠሯቸው መሰረት ፍ/ቤት ሊያቀርቧቸው አልቻሉም፡፡ ለምሳሌ ጥቅምት 9/2009 ዓ.ም ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት ቀጠሮ የነበራቸው እነ ከድር መሃመድ (20 ሰዎች) እና እነ ትንሳኤ በሪሶ (10) ሰዎች ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ተረጋግጧል፡፡

ጥቅምት 14/2009 ዓ.ም ቀጠሮ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬም በተመሳሳይ በቀጠሮው ዕለት ፍ/ቤት አልቀረበም፡፡ ለዚህም ከማ/ቤቱ አስተዳደር ተጠርጣረውን ላለማቅረቡ በቂ ምክንያት ለፍርድ ቤቱ አላቀረበም፡፡

አሁን ላይ ወደ ቂሊንጦ የተመለሱት ታሳሪዎች በአንጻራዊነት የተሻለ ሁኔታ ላይ ናቸው ለማለት ቢቻልም አሁንም ግን የመጠየቂያ ሰዓት ገደብ አለባቸው፡፡ ቢበዛ ለ10 ደቂቃ ብቻ ነው ቤተሰቦቻቸውን እንዲያነጋግሩ የሚፈቀድላቸው፡፡ ከምግብ ሌላ ማናቸውም ነገር እንዲገባላቸው አይፈቀድም፡፡ የጥርስ ሳሙናና ቡርሽ፣ ቫዝሊን፣ በሶ እና የመሳሰሉት አስፈላጊ ነገሮች እንኳ አይገቡላቸውም፡፡

መንግስት እስረኞችን ተጠያቂ ሊያደርግ ስለመሆኑ

የኢትዮጵያ መንግስት በቂሊንጦ ለደረሰው አደጋ እስረኞችን ተጠያቂ በማድረግ ክስ ሊመሰርት መሆኑ ታውቋል፡፡ መንግስት በቁጥር የበዙ እስረኞችን በተጠርጣሪነት ይዞ ምርምመራ በማድረግ ላይ እንደሆነና ምስክሮችንም እያዘጋጀ እንዳለ የታወቀ ሲሆን፣ ተጠርጣሪዎቹ በቂሊንጦ ለደረሰው አደጋና ይህንንም ተከትሎ ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት ተጠያቂ ናችሁ ሊባሉ እንደሚችሉ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ መንግስት ይህን እያደረገ የሚገኘው የደረሰው ቃጠሎ መንስኤና ቃጠሎውን ተከትሎ የደረሰው ጉዳት በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ባልተገለጸበት ሁኔታ ነው፡፡ መንግስታዊው “የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን” ማጣራት አደርጋለሁ ማለቱና በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ ሪፓርት አቀርባለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

(በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጀክት ተዘጋጀ)

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ለ3ኛ ጊዜ ለብይን ተቀጥሯል

‹ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ግንቦት ሰባት ከተባለው አሸባሪ ቡድን አመራሮች ጋር ግንኙነት አድርገሃል› በሚል የሽብር ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘው የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ለ3ኛ ጊዜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡

ዛሬ ጥቅምት 21/2009 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዳኞች ጉዳዩን በጽ/ቤት የተመለከቱት ሲሆን፣ ዳኞቹ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ ለህዳር 28/2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

በሌሎች መዝገቦች ከዛሬ ቀደም ቀጠሮ የነበራቸውን ተከሳሾች ሳያቀርብ የቆየው የቂሊንጦ ማ/ቤት ዛሬ ጋዜጠኛ ጌታቸውን ጨምሮ ሌሎች በዕለቱ ቀጠሮ ያላቸውን ተከሳሾች ፍ/ቤት አቅርቧል፡፡

ተከሳሹ ጌታቸው ሺፈራው ጉዳዩ ሲታይ የቆየው 14ኛ ወንጀል ችሎት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ ጉዳዩን የሚያየው ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም ቀደም ሲል በነበረው ችሎት በአንድ ዳኛ ይታይ የነበረው የክስ ጉዳዩ በአሁኑ ችሎት በሦስት ዳኞች የሚታይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የቀረበበትን ክስ መከላከል ይገባዋል ወይስ መከላከል ሳያስፈልገው በነጻ ይሰናበት የሚለውን ብይን ለመስማት ፍ/ቤት ቀጠሮ ሲሰጥ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡ ተከሳሹ ላይ አቃቤ ህግ ከሰነድ ማስረጃዎች ሌላ የሰው ምስክር አላቀረበበትም፡፡

ጌታቸው ታህሳስ 15/2008 ዓ.ም ለእስር ከተዳረገበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ጉዳዩን በእስር ቤት ሆኖ እየተከታተለ ይገኛል፡፡

Dr Berhanu Nega Speech for the establishment of Ethiopian National Movement

Four Political organizations have established a movement known as Ethiopian National Movement vowing to fight Woyane(TPLF). The organizations included in the movement are, Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy, Oromo Democratic Front(ODF) Afar people’s Party and Sidama National Democratic People Movement. Formal signing for the establishment of the Movement, in the presence of all the leaders and a video speech by Dr Berhanu Nega, has taken place in Washington DC on 30th October 2016.


Sunday, 30 October 2016

ንቅናቄው ይፋ ሆነ – “ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ መመስረት ጠንክረን እንሠራለን” –ሌንጮ ለታ “ሕዝባችንን እና ሀገራችንን አስቀድመን እንታገላለን” – ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

አራት ድርጅቶች በጋራ የመሰረቱት “የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ” ዛሬ በዋሽንተን ዲሲ የድርጅቶቹ መሪዎች ሌንጮ ለታ እና ምክትላቸው ዲማ ነገዎ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳና አቶ በቀለ ዋዩ በተገኙበት ይፋ ሆነ::

“የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ”ን የመሰረቱት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ የአፋር ሕዝብ ፓርቲና የሲዳማ ሕዝብ ዴሞራሲያዊ ንቅናቄ ሲሆኑ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ንግግር ያደረጉት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር መሪ ኦቦ ሌንጮ ለታ ““ወረቀት መፈራረም ቀላል ነው፤ እዚህ ንግግር ማድረግ ቀላል ነው። ከባዱ ነገር ሀገር ቤት እያለቁ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ጠንክረን መሥራቱ ነው። እጅግ ብዙ ሂደት አልፈን ነው እዚህ የደረስነው። ከፊታችን ብዙ ከባድ ፈተናዎች አሉ።ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገናል። በህዝቦቿ መፈቃቀድ ለምትመሰረት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ጠንክረን እንሠራለን!” ሲሉ ቃል ገብተዋል::

 በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ”ጨቋኙን አገዛዝ ለማስወገድና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ስምምነት ለተፈራረምንበት ለዚህ ታሪካዊ ቀን በመብቃታችሁ ሁላችሁም እንኳን ደስ ያላችሁ! ንቅናቄው በአራት ፓርቲዎች ይመስረት እንጂ ሌሎች ድርጅቶችንም ወደ ህብረቱ ለማምጣት ተግተን የምንሠራበት ነው። ከራሳችንንና ከድርጅታችን ይልቅ ሕዝባችንን እና ሀገራችንን አስቀድመን ልንታገል ቃል ገብተናል።” ብለዋል::


BLOGGER ZELALEM WORKAGEGNEHU MARKS 848 DAYS IN JAIL

Blogger and activist, Zelalem Workagegnehu today marks 847 days since he was jailed by the current Ethiopian regime for merely caring for his country and people.

Since the five year plus two months sentencing last May 2015, Zelalem has been appealing the decision and is now waiting to yet another appeal from the Cessation Court in Addis Abeba.

Zelalem is currently being jailed in the infamous gulag of prisoners’ of conscience in Ethiopia, Kaliti Prison, where journalists like Eskinder Nega, opposition politicians such as Andualem Arage and Okello Aquay are being jailed.

Zelalem was finishing his Masters Degree in Public Administration at the Addis Abeba University, in July 2014 when he was detained together with nine other opposition politicians, netizens, and activists.

The movement he is accused of supporting is known as Ginbot 7 (Arebgenoch Ginbot 7 Movement), a pro-democracy movement founded by Professor Berhanu Nega, an Ethiopian economist, who lectured in Bucknell University, U.S.A. Zelalem was initially accused of being a member and local leader of Ginbot 7 although the charges were later changed to recruiting members to start an Arab Spring styled revolution in Ethiopia and applying for a digital security course.

Saturday, 29 October 2016

የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት እንዲከበር ግፊትን እንዲያደርግ ተጠየቀ

የካናዳ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ልማታዊ ትብብር በመጠቀም በሃገሪቱ ዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት እንዲከበር ግፊትን እንዲያደርግ የካናዳ የፓርላማ አባላት ጠየቁ።

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ካለው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተገናኘ ወደ 1ሺ 600 አካባቢ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ያወሱት የፓርላማ አባላቱ የካናዳ መንግስት ማንኛውንም አማራጭ በመጠቀም እርምጃ እንዲወስድ ፒተር ኪንግ የተባሉ የፓርላማ አባል አሳስበዋል።
ለሃገራቸው መንግስት የጽሁፍ መልዕክትን ያቅረቡት የፓርላማ አባሉ፣ ካናዳ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን ድጋፍ ለዴሞክራሲ መከበር ስትል ተጽዕኖን ለማድረግ በአማራጭነት መመልከት እንደሚገባት ጠይቀዋል።

“ሁሉም ኢትዮጵያ ሰላምና ደህንነቱ ተጠብቆ መኖር ይኖርበታል” ሲሉ በጽሁፋቸው ያመለከቱት ፒተር ኬንት በህግ የበላይነት የሚያምን መንግስት ብቻ ይህንን ስርዓት ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሚችል አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረት አዋጁ የሰብዓዊ መብት ረገጣን ያባብሳል ሲሉ ስጋታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል። አሜሪካ በተለየ መልኩ ዜጎቿ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይጓዙ ማሳሰቢያን የሰጠች ሲሆን፣ የሃገሪቱ ዕርምጃ በሌሎች አለም አቀፍ አካላት ዘንድ ስጋት መፍጠሩ ይነገራል።

መቀመጫቸውን በካናዳ ያደረጉት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ዕርምጃን መውሰድ ይኖርበታል ሲሉ ዘመቻ ሲያካሂዱ መቆየታቸውን CBC የተሰኘ የሃገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። በኢትዮጵያ ከሽብርተኛ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለእስር ተዳርጎ የሚገኝ አንድ ካናዳዊ ለማስለቀቅ የካናዳ መንግስት ማንኛውንም ጫና ማድረግ እንዳለበት የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማቱ በመጠየቅ ላይ ናቸው።

ባሽር ማክታል የተባለው ካናዳዊ ወደ ሶማሊያ ባቀና ጊዜ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውሎ በሽብርተኛ ወንጀል ክስ የእድሜ ልክ ዕስራት እንደተላለፈበት ለመረዳት ተችሏል። ይሁንና የሃገሪቱ የፓርላማ አባላትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የካናዳ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ ጫናን በማሳደር ግለሰቡ እንዲለቀቅ የሚተየቅ ዘመቻን እያካሄዱ እንደሆነ ታውቋል።

Friday, 28 October 2016

Four major Ethiopian oppositions formed “Ethiopian Movement”

Four political parties announced that they have formed an umbrella organization called the Ethiopian National Movement. The four parties that formed the Movement are the Oromo Democratic Front (ODF), Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy (PG7), the Afar People’s Party and the Sidama People’s Democratic Movement.
 
Leaders of the four parties will sign the document at a public gathering on Sunday in Washington, DC. More political parties are expected to join the National Movement, it was learnt.

It is to be recalled that ODF and PG7 had already formed an alliance early this year.

Ethiopians at home and in the Diaspora have been urging opposition political parties to have cohesion and unity in a bid to do away with a tyrannical regime that is facing uprising in all corners of the country.

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ በአራት ድርጅቶች ተመሰረተ!

አራት የፖለቲካ ድርጅቶች ወያኔን ለመታገል የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ የተሰኘ የጋራ ንቅናቄ መመስረታቸው ይፋ ሆነ፡፡ እነዚህም አርበኞች ግንቦት ሰባት የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ዶሞክራሲያዊ ግንባር፣ የአፋር ህዝብ ፓርቲና የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሲሆኑ ምስረታውን አስመልክቶም በመጪው እሁድ ኦክቶበር 30/2016 መሪዎቹ በሚገኙበት በዋሽንግተን ዲሲ የፊርማ ስነ-ስርአት እንደሚደረግ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄን ምስረታን አስመልክቶም በመጪው በዋሽንግንወ ዲሲ በሚደረገው የፊርማ ስነ-ስርአት ላይ ለመገኘትም የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታና ም/ሊ/መንበር የሆኑት አቶ ዲማ ነገዎ እንዲሁም የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊ/መንበር የሆኑት ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ አሜሪካ መግባታቸው ሲታወቅ የሲዳማ ህዝብ ዲሞክራሲያው ንቅናቄ ሊ/መንበር የሆኑት አቶ በቀለ ዋዩ በቅርቡ አሜሪካ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

የአዲሱን ንቅናቄ ምስረታን በይፋ በሚያበስረውና እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው የመሪዎቹ የፊርማ ስነ-ስርአት ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሊ/መንበር ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ እንደሚገኙ የሚጠበቅ ሲሆን ዜናውን እስከአጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ አሜሪካ መግባታቸው ያለመታወቁን ዜናው ጨምሮ ሲያስረዳ ከፊርማው ስነ-ስርአት በተጨማሪ አራቱም የአራቱም መሪዎች በተገኙበት ህዝባዊ ጉባኤ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Thursday, 27 October 2016

ወጣት ብሌን መስፍን በድጋሜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣት

ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዛ በስቃይ ላይ የምትገኘው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው ወጣት ብሌን መስፍን በአስር ሽህ ብር ዋስትና መብቷ ተፈቅዶላት ውጪ ሆና ጉዳይዋን እንድትከታተል ሲል የሰባራ ባቡሩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወቅቱ ውሳኔ ቢያሳልፍም፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም አቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው የክስ መቃወሚያ ጉዳዩን የሚያየው ኮማንድ ፖስቱ በመሆኑ በእስር ላይ ትቆይ ብሎአል። የብሌን ጠበቃ በበኩላቸው በደንበኛቸው ላይ የቀረበባት ክስ ከህግ አግባብ ውጪ እንደሆነና ብሌን መስፍን የተያዘችበት ቀን መስከረም 25 ቀን 2009 ዓ.ም ሲሆን ይህም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመታወጁ በፊት በመሆኑ፣ የኮማንድ ፖስቱ አዋጅ ጉዳይ አይመለከታትም ሲሉ ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱም በውሳኔው ላይ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Wednesday, 26 October 2016

የቂሊንጦ ተወካይ “አቶ ዮናታን ተስፋዬ የት እንዳለ አላውቅም” አለ

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃለፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ትላንት ፍርድ ቤት ቀጠሮ የነበረው ቢሆንም ሳይቀረብ ቀርቷል፡፡ አቶ ዮናታን ትላንት ቀርቦ የመከላከያ ምስክሮቹን ማሰማት የነበረበት ቢሆንም፣ ታስሮ የሚገኝበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ሳያቀርበው መቅረቱ ተነግሯል፡፡ አቶ ዮናታን ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ጥያቄ የቀረበላቸው የወህኒ ቤቱ ተወካይ፣ ተጠርጣሪው ፍርድ ቤት መቅረቡንም ሆነ አለመቅረቡን አንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ቂሊንጦ ይኑር አይኑርም እንደማያውቁ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡

የተከሳሽ ጠበቃ አቶ ሽብሩ በለጠ በበኩላቸው ወህኒ ቤቱ ከደምበኛቸው ጋር እንዳይገናኙ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል፡፡ ተከሳሹ ለምን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ወህኒ ቤቱ የጽሁፍ ማብራሪያ እንዲያመጣ የጠየቀው ፍርድ ቤቱ፣ ለህዳር 19 ቀን 2009 ተለወጭ ቀጠሮ በመስጠት፣ ወህኒ ቤቱ በዕለቱ ተከሳሹን ችሎት እንዲያቀርበው ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የኦሮሚያ ተቃውሞ እየተጋጋለ በነበረበት ወቅት ማለትም ያለፈው ዓመት አጋማሽ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው አቶ ዮናታን፣ ለክሱ በማስረጃነት ከቀረቡበት ነጥቦች በፌስ ቡክ ገጹ የጻፋቸው ፖለቲካዊ ጽሁፎች እንደሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡ መንግስት ሆን ብሎ ባስነሳው እና ብዙዎችን በጥይት ደብድቦ በገደለበት የቂሊንጦ እሳት አደጋ ወቅት ወደ ሌላ ማቆያ ተወስደው ከነበሩት ተጠርጣሪዎች አንዱ ዮናታን ተስፋዬ ነው፡፡ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ከሚያደርጉ ወጣት ፖለቲኮኞች አንዱ የሆነው አቶ ዮናታን ተስፋዬ በዓቃቤ ህግ የሽብር ወንጀል ክስ እንደተመሰረተበት ይታወቃል፡


Monday, 24 October 2016

በየእለቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመውን ግፍ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሌሎች ወገናዊነትንና አንድነትን የሚያጎለብቱ ተግባራት በመላው አለም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

ያሳለፍነው ቅዳሜ በጀርመንዋ ከተማ ቩርዝቡርግ በርካታ ህዝብ የተሳተፈበትና ዋና ዋና ጎዳናዎችን የሸፈነ ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ ደግሞ በሙኒክ ከተማ በሀገራችን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የሚመክር ህዝባዊ ስብሰባ ይደረጋል። በስዊትዘርላንድ ጄኔቫ ደግሞ በመላ አውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ በመጪው ሳምንት ማክሰኞ ይደረጋል።

በሌላ በኩል በኒዉዚላንድ ኦክላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን “ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በኒዉዚላነድ” ቅዳሜ ኦክቶበር 22፣ 2016 በኢሬቻ በዓል ሥነ ሥርዓት አከባበር ላይ ወጥተዉ በ አጋዚ ጦር ለተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት በማዘጋጀት ዘክረዋል። 


በዚህ የኢሬቻ የሻማ ማብራት ሥርዓት ላይ ወጣቶች ስለ አገራቸዉ ታሪክና አሁን ስላለዉ የኢትዮጵያ ችግር እና ዘርን አስመልክቶ ወያኔ እያደረገ ያለዉን የጥፋት ዘመቻ እና ወያኔን ለመታገል ከተደራጁት ወገን በኩልም መወሰድ ስለሚገባቸዉ እርምጃዎችና ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ አንድነት እና መተሳሰብ እንደሚያስፍልጋቸዉ አብረዉም መስራት እንዳለባቸው አቶ ባቱና አቶ ዘካርያስ በስነስርአቱ ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ ሰጥተዋል።

Saturday, 22 October 2016

Conference on post-conflict Ethiopia underway in Washington, DC

A two day conference kicked off in Washington, DC on Saturday to deliberate on “transition and constitution making in post-conflict Ethiopia.”Conference on post-conflict Ethiopia underway in Washington, DC

Political scientists, activists, representatives of political organizations and religious institutions as well as prominent Ethiopians would be deliberating and exchanging views on prevention, management and resolution of conflicts in a post-TPLF Ethiopia in a bid to prevent and resolve issues that might lead to instability in Ethiopia.

Welcoming participants, Prof. of economics at Harper College and President of Vision Ethiopia, Getachew Begashaw of Harper College and President of Vision Ethiopia, the organizer of the conference, spoke of the significance of the theme of the conference considering the current state of affairs in Ethiopia.

Also welcoming conference participants, Abebe Gellaw, Executive Director of ESAT, the co-organizer of the conference said the conference came at a time when “change is knocking at the door in Ethiopia.” He said the topic of the conference was of paramount importance as Ethiopians need to work “to clean up the mess that the demise of the TPLF regime would leave behind.”

A number of papers with particular emphasis on transition as well as managing and resolving conflicts in the post TPLF Ethiopia would be deliberated at the conference which is streaming live on ESAT.

Friday, 21 October 2016

As Protests Rage in Ethiopia, Zone9 Bloggers Return to Court

As protests rage over land rights and ethnic discrimination, bloggers and independent journalists in Ethiopia appear to be losing ground in their struggle to exercise free expression. Alongside other recent arrests, four members of the Zone9 bloggers collective, who spent 18 months in prison on terrorism-related charges from 2014-2015, returned to court on October 21 following an appeal by the public prosecutor. Their case was adjourned yet again, with a new court date scheduled for November 15.

The Addis Ababa-based blogging collective, six of whom are Global Voices contributors, had worked to foster political debate and discussion in the face of a near-monopoly that the state holds over media outlets.

Charged under Ethiopia’s Anti-Terrorism Proclamation with “inciting public disorder via social media” and “receiving support from a foreign government,” the bloggers appeared in court 38 times from July 2014 to October 2015, only to be adjourned each time at the behest of the prosecution, which sought more time to investigate their case. Some members were released without explanation shortly before Barack Obama’s July 2015 visit to the country. The rest were “acquitted” in October of that year, though they were never invited to testify before a jury. And now, a year later, the four members of the group—Abel Wabela, Atnaf Berahane, Natnael Feleke and Befeqadu Hailu—are returning to court once again.

With the country in an official “state of emergency,” social media sites are intermittently blocked or banned from use and mobile Internet connections are periodically cut, the need for independent media reporting from inside the country feels ever-more vital — and increasingly under threat.

Netizen report (Global voices)

 Zone9 bloggers left to right: Abel Wabela, Zelalem Kiberet, Mahlet Fantahun, Atnaf Berahane, Befeqadu Hailu, Natnael Feleke

Thursday, 20 October 2016

Mass incarceration ensues emergency law in Ethiopia

Ethiopian security forces have detained hundreds of people after authorities declared a state of emergency in a nation that saw anti-government protests and crackdowns.

In the country’s Oromo region, where hundreds of youth lost their lives in the hands of regime’s security forces, over a thousand people have been arrested in the last one week alone, a command post setup by the regime to implement the emergency law told the local media on Wednesday.
State run media, quoting the command post, confirmed the detention of 670 people in the central region of Arsi while 110 were arrested in Wollega, west of the country.

Over one thousand people were arrested last week in Sebeta, near the capital Addis Ababa. Authorities suspect the detainees were organizing the youth to defy the emergency law.

In the last two weeks, people in the Oromo region of the country have been protesting the killing of hundreds of festival goers in Debre Zeit/ Bishoftu on October 2, 2016, where a religious ceremony turned deadly as security forces fired shots and threw tear gas canisters, resulting in a massive stampede. At least 700 people, by the estimate of a local political organization, lost their lives.

The protest in the Oromo region which began in November 2015 still continues unabated while in Gondar, Amhara region, a three-day strike concluded on Wednesday. The strike, according to organizers, was aimed at defying the state of emergency and denounce mass killings and human rights violations throughout Ethiopia, including Bishoftu.

Wednesday, 19 October 2016

US Demands the Release of Ethiopian High-Profile Female Prisoner Blen Mesfin

The United States has called on the Ethiopian government to release a high-profile female prisoner and to stop its crackdown on peaceful opposition.

On Monday, the US ambassador to the United Nations (UN) Samantha Power called for the release of Blen Mesfin, a female member of the opposition Blue Party, who was arrested last year.
Power also noted that attempts to stifle opposition voices would backfire on the Ethiopian government.

The Ethiopian government declared a state of emergency on October 8 in response to months of widespread anti-government protests. More than 1,000 people have been incarcerated in Ethiopia since the state of emergency came into effect, BBC reports.

Blen Mesfin is reportedly one of Ethiopia’s most high-profile female political prisoners. She was arrested in April 2015 with two other opposition members at a demonstration against the Islamic State in Libya (ISIL). Mesfin was charged with inciting violence during the protests against the terror group, Human Rights Watch reported.

The call for Mesfin’s release comes as several international organizations including the UN and the Europe Union (EU) have called on Ethiopian authorities to exercise restraint in dealing with protesters.

The protest, which began last year in the Oromia region over a government expansion plan, has since spread to other parts of the country. The demonstrations have turned violent with clashes between protesters and security forces.

Ethiopian authorities say the protest has been high jacked by opposition groups working with foreign governments seeking to destabilize the country.

Tuesday, 18 October 2016

Seven things banned under Ethiopia's state of emergency

Ethiopia's government has declared a six-month state of emergency in the face of an unprecedented wave of violent protests. Activists in the country's Oromia region has been holding demonstrations since last November, and protesters from the Amhara region have also joined in.

Rights groups say that at least 500 people have died during the protests.  The emergency was announced earlier this month but the government has now made clear what this means in practical terms.

Here are some of the things that are restricted:

1. Social media

You cannot use social media, such as Facebook and Twitter, to contact what are called "outside forces". In fact, any attempt to communicate with "terrorist organisations and anti-peace groups designated as terrorist" is banned. Ethiopians who post statuses on Facebook about the country’s growing political unrest could face up to five years in jail.

2. Broadcast media

You cannot watch the TV channels Esat and OMN, which are both based outside the country. The government has described them as "belonging to terrorist organizations".
These broadcasters have become some of the major sources for people wanting to know more about the protests.

3. Protests

You cannot organize a demonstration at your school or university, neither can you be involved in a political campaign that is "likely to cause disturbances, violence, hatred and distrust among the people".
University campuses were among the first places to be hit by the wave of anti-government protests.

4. Gestures

You cannot make a political gesture, such as crossing your arms above your head, or communicate a political message to the public "without permission".
The crossing-arms gesture has been seen widely at the protests in Oromia, and even made it to the Olympics when marathon runner Feyisa Lilesa used it as he crossed the line in second place in Rio in August.

5.Curfew

You cannot visit a factory, farm or governmental institution between 6pm and 6am the next day. If you violate the curfew then "law enforcement bodies have been authorised to take the necessary action".

6. Diplomats

If you are a diplomat you are not allowed to travel more than 40km (25 miles) from the capital, Addis Ababa, without permission.

7. Guns

If you have a gun, you cannot take it within 25km of the country's main roads out of Addis Ababa, and within 50km of the country's borders, even if you have a permit to carry it.

በጎንደር የሚደረገው የሥራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎአል

አስተባባሪዎች እንደገለጹት  ሱቆች፣ ሆቴሎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለሁለተኛ ቀን ተዘግተው ውለዋል። ከትናንት በበለጠም የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሲያስገድዱ ውለዋል። የገዢው ፓርቲ ደጋፊ ነጋዴዎች ወይም እየተጠሩ ድርጅቶቻቸውን ካልከፈቱ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተነግሮአቸው ለይስሙላ ከከፈቱት በስተቀር በአብዛኛው የከተማ ክፍል የስራ ማቆም አድማው በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።

“ የሥራ ማቆም አድማ ማድረግ ክልክል ነው” የሚል አፋኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከወጣ በሁዋላ፣ አዋጁን ከምንም ባለመቁጥር በክልሉ የሥራ ማቆም አድማ ሲደረግ ከባህርዳር ከተማ አድማ ቀጥሎ የጎንደሩ አድማ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ  ነው። የአሁኑ የስራ መቆም አድማ የባህርዳር ህዝብ በቢሾፍቱ ያለቁ ወገኖችን በማሰብ ያካሄደውን የሥራ ማቆም አድማ በመደገፍ አጋርነትን ለመግለጽ እንዲሁም አፋኙን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቃወም ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑን አስተባባሪዎች ተናግረዋል።

ሰኞ እለት የስራ ማቆም አድማውን ተከትሎ  የንግድ ድርጅቶችን በጉልበት ለማስከፈት በተደረገ ሙከራ ወታደሮች በሰዎች ላይ የተኮሱት ጥይት አንድ አህያ ተመትታለች። በርካታ ነጋዴዎችም ተይዘው ታስረዋል። በከተማዋ ዲሽ ለማውረድ የተንቀሳቀሱ ካድሬዎች በድንጋይ መመታታቸውም ታውቋል።

በባህርዳርም ህዝቡ ዲሽ እንዲያወርድ በቀበሌዎች አሰተዳደር በኩል ሚሊሻዎች አሰሳ  እያደረጉ ነው፡፡

ኢሳት

Monday, 17 October 2016

የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል

ከመግለጫው የተወሰደ

" ከዚህ በኋላ የፍትህና የነፃነት ኃይሎች ዋና ተግባር ያላቸውን አቅም ሁሉ አስተባብረውና ነፃነት የራበውንና የጠማውን ሕዝባቸውን ከጎናቸው አሰልፈው፤ ጊዜውና ሁኔታው የሚፈቅደውን ተለዋዋጭና ተለማጭ የትግል ስልት እየተጠቀሙ ይህ አዋጅ በፍጹም ተግባራዊ እንዳይሆንና እንዳይሳካ ማድረግ ነው። ይህን የባርነት አዋጅ ለማስፈጸም በመሪነትና በዋና አስፈጻሚነት የሚንቀሳቀሱት ኃይሎች፤ ይህ የባርነት አዋጅ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲተገበርና እንዲሳካ ለማድረግ የሚሞክሩ ወይንም ከዚህ ዘራፊ ሥርዓት ጋር በጥቅም ተሳስረው ከዚህ የባርነት አዋጅ ጋር የሚተባበሩ ማናቸውም ኃይሎች ሁሉ ከአሁን ጀምሮ የሕዝባዊ ትግሉ ቀንደኛ ዒላማዎች መሆናቸውን ግልጽ አድርጎ መንቀሳቀስ ይገባል። በዚህ ሕዝባዊ ትግል ላይ የሚሳተፉ የሕዝብ ወገኖችም ሆነ ይህንን ዘራፊ ሥርዓት የሚያግዙ ኃይሎች በደንብ እንዲረዱት የሚያስፈልገው ይህን አዋጅ አከሸፍነው ማለት የወያኔ ሥርዓት አከተመለት ማለት እንደሆነ ነው። ይህ አዋጅ ተሳካ ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላልተወሰነ ጊዜ በባርነት መቀመቅ ውስጥ ሊኖር ተፈረደበት ማለት ነው። ለዚህ ነው አሁን የገባንበት ትግል የመጨረሻው የሞት ሽረት ትግል ነው የምንለው።"

"በዚህ የመጨረሻ የፍልሚያ ወቅት ጥቂቶቻችን ልናልፍ እንችላለን። ለነፃነታችን ስንል ሕይወታችንን ብንሰጥ ፈጣሪያችን በአምሳሉ ሲፈጥረን የሰጠንን የሰውነት ማንነት እውን ለማድረግ በምናደርገው ትግል ነውና የምናልፈው፤ የፈጣሪያችንን ፈቃድ ለማስፈጸም የገበርነው ሕይወታችን ነውና በደስታ የምንጠጣው ጽዋችን ነው። ይልቅስ ፈጣሪያችን ለምንግዜውም ይቅር የማይለን ከሌላው እንሰሳ ለይቶ የሰጠንን ይህን በነፃነት የታጀበ የሰው ልጅነት፤ እንደ እንሰሳ ለሚበላና ለሚጠጣ ቁሳዊ ጥቅም ሸጠን፤ ሰው መሆንን በእንሰሳዊ የባርነት ሕይወት ቀይረን እኛ ባርነትን ተቀብለን ከራሳችን አልፎ ባርነትን ለልጆቻችን ያስተላለፍን እንደሆነ ነው። የዛሬ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የባርነትን ኑሮ ከኛ እንዳያልፍና ወደ ልጆቻችን እንዳይጋባ ማስቆም ታሪክ የጣለብንና በእርግጠኛነት የምንፈጽመው ተግባራችን እንደሆነ ከቶውንም አልጠራጠርም።"

Saturday, 15 October 2016

Ethiopian regime releases details of state of emergency

One week after declaring a six-month state of emergency, Ethiopian authorities released details of the law on Saturday prohibiting exchange of electronic messages and banning public gatherings and demonstrations among others.

The state run media outlets on Saturday published details of the law as presented by the head of the command post secretariat in charge of the state of emergency and minister of defense, Siraj Fergessa.
The emergency law prohibits the exchange of messages and information via the internet, cell phones, social media, television and radio.

Publishing and distributing documents, holding demonstrations, showing protest gestures, importing and exporting published materials were also prohibited by the law.

The law specifically mentioned two independent media outlets abroad and banned the public from watching and listening to television and radio programming by the Ethiopian Satellite Radio and Television (ESAT) and Oromo Media Network. The law gives power to security forces to monitor and block messages transmitted via television, radio and movie theatres.

According to the law, strikes by workers as well as businesses and closing government offices in protest are illegal. The law says protests by students in universities, colleges and higher institutions of learning are also outlawed. The law gives power to security forces to take any action they deemed necessary against students who stage protest rallies.

The emergency law stipulates that diplomats cannot travel beyond 40 kms radius outside the capital without prior authorization and permission from the command post. Members of the police and security forces cannot take leave of absence or resign in the duration of the state of emergency.

A curfew is in effect from 6 p.m. to 6 a.m. local time in areas where there are economic infrastructures, factories, agricultural projects and other investments. The law also authorizes security forces to take whatever measure necessary against people who violate the curfew.

Areas 50 k.m. inside the the country’s border are designated as red zones. The carrying of firearms are banned in the red zone. Other restrictions imposed in the rest of the country are also applicable in the red zone. Carrying firearms within 25 meters of highways connecting the capital Addis Ababa to major towns and destinations are also forbidden.

Security forces are given permission to search and arrest anyone and confiscate possessions without a court warrant, according to the law. The emergency law also give security forces the power to take any action to defend themselves from any threat or attack.

The Ethiopian regime last Sunday declared a state of emergency after a wave of anti-government protests flared up again following the massacre early this month of hundreds of festival goers in Bishoftu, 45 kilometers outside the capital, at a religious festival of the Oromos.

Local political parties estimate close to 700 people were killed in a stampede as security forces shot tear gas to disperse protesters. Witnesses also say security forces shot and killed several people, who used the occasion to express grievances against the tyrannical government.

A year long protest in the Oromo region, which was joined this summer by the people in the Amhara region has left hundreds dead as security forces use lethal force to disperse demonstrators, who demanded an end to a dictatorial rule.

Wednesday, 12 October 2016

UN outraged at mass killings, abuses in Ethiopia

The United Nations Special Rapporteur on freedom of peaceful assembly and of association says it was outraged at reports of mass killings and abuses in Ethiopia. 

“We are outraged at the alarming allegations of mass killings, thousands of injuries, tens of thousands of arrests and hundreds of enforced disappearances,” said the UN Special Rapporteur on freedom of peaceful assembly and of association, Maina Kiai, the Working Group on enforced or involuntary disappearances and Agnes Callamard, on extrajudicial, summary or arbitrary executions.

In its latest press release, the UN Special Rapporteurs called the crackdown a “systematic violence against protesters” and called on the Ethiopian regime to allow an international commission of inquiry to investigate the protests and the violence used against peaceful demonstrators.

“Curtailing assembly and association rights is never the answer when there are disagreements in a society; rather, it is a sign of the State’s inability to deal with such disagreements,” Mr Kiai said. “Suffocating dissent only makes things worse, and is likely to lead to further social and political unrest.”

“We are also extremely concerned by numerous reports that those arrested had faced torture and ill-treatment in military detention centres,” the rapporteurs said.

UN human rights experts renewed their calls for an end to the deadly crackdown against peaceful protesters and for an independent investigation into the killings in Ethiopia by the ruthless regime.
The rapporteurs believed the crackdown on protesters in Ethiopia was a deliberate effort to wipe out any kind of opposition to the regime. “The scale of this violence and the shocking number of deaths make it clear that this is a calculated campaign to eliminate opposition movements and silence dissenting voices,” Kiai added. The experts reiterated the urgent need to investigate and hold accountable those responsible for the violence.

A group of UN experts made a similar call in January 2016, which went unheeded, according to the group.

The UN High Commissioner for Human Rights late last week renewed a request to the Ethiopian government seeking access to the country to conduct an independent assessment of continuing protests.


(UN Special Rapporteur on freedom of peaceful assembly and of association, Maina Kiai)

MEPs denounce worsening human rights situation in Ethiopia

Press release

Deteriorating human rights situation in Ethiopia, killings of Oromos and the country-wide six-month state of emergency declared on Sunday 9 October by the Ethiopian government were amongst the main issues raised by Human Rights subcommittee and Development committee Members in a joint meeting on Wednesday morning.

MEPs expressed their concerns as regards the worsening human rights situation in Ethiopia during a debate with various experts and representatives from the European External Action Service (EEAS), the European Commission, and the Ethiopian Embassy. They are worried by continuous public arrests, waves of violence and by the country-wide six-month state of emergency declared by the Ethiopian authorities on Sunday 9 October after months of anti-government protests.

MEPs were critical against the EU policy vis-à-vis Ethiopia arguing it is "falling a long way behind its own standards regarding human rights". "Maintain the dialogue with Ethiopia" is the priority said representatives of the EEAS adding that the good governance and human rights dialogue will be the first to be activated. See more at...

http://www.europarl.europa.eu/news/en/news-room/20161012IPR46851/meps-denounce-worsening-human-rights-situation-in-ethiopia

Tuesday, 11 October 2016

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት እየታደኑ መታሰር ጀመሩ

አሁን በደረሰን ዜና መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት እንጂነር ይልቃል ጌትነት  ፣ ብሌን መስፍን ፣ወረታው ዋሴ ፣ወይንሸት ሞላ እና ሌሎችም ስም ዝርዝራቸው ያልተጠቅቀሱ አባሎች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መስሪያቤት ከሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ቅርንጫፍ ገልጸዋል ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፖሊስ አባላቶች በሌሎችም ዜጎጅ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ግለሰቦች ላይ እንዲሁም ፣መንግስትን ከሃገርቤት ሆኖ በፌስቡክ እና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚኮንኑ ጽሁፎችን የሚያወጡ ወጣቶችን አድኖ ለማሰር ደብዳቤ ከክፍተኛ ባለስልጣናቶች እንደተላከ እና ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ከ72 ሰአታት እስከ 315 ሰአታት እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል ።
yiliqal
ይህንን ለማድረግ የእያንዳንዱን የፖለቲካልም ሆነ የሌሎች አባል የሆኑ ዜጎችን የሚሰሩበትን መስሪያቤትም ሆነ ፣ስራዎቻቸውን አጣርተው ቢጨርሱም ፣እነሱን ለማፈን የሚንቀሳቀሱት አባላቶች ግን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የፖሊስ ኮሚሽን ታማኝ የሆኑ ሰራዊቶች ብቻ ናቸው ሲኡ አትተዋል።
በተለይም በዛሬው እለት የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ምራክል በሃገሪቱ ላይ ጉብኝት እሚያደርጉበት ወቅት እንዲህ ማድረጋቸው የአምባገነንታቸው ምልክት ነው ሲሉ ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላቶች ገልጸዋል ። በሃገር ውስጥ በመሆን ብቸኛ የፖለቲካ ትግል የሚያደርገው እና ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ ተብሎ የተሰየመው እንደዚሁም በወጣት አመራር እና ወጣት ሃይሎች የተሞላው ይሄው የሰማያዊ ፓርቲ ጥቃት በተቃዋሚዎች እና በገዥው ፓርቲ ዱላ ሲሰነዘርበት የቆየ ጠንካራ ፓርቲ ነው ሲሉም አክለው እነዚሁ ፖሊስ አባላቶች ገልጸዋል።
ማለዳ ታይምስ

አቶ አንዳርጋቸውን ጽጌን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ ሪፕሪቭ የተሰኘው ተቋም ገለጸ

(ኢሳት) በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን ደህንነት አድጋ ውስጥ እንደከተተ አንድ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሰኞ አስታወቀ።

መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው ሪፕሪቭ ተቋም የሃገሪቱ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ጉዳይ ግምት ውስጥ በመክተት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የሚፈቱበትን ሁኔታ እንዲያመቻችና ይፋዊ ጥያቄን እንዲያቀርብ አስቧል። በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት ተቃዋሚ ናቸው ባላቸው አካላት ላይ የሚወደውን እርምጃ ለማጠናከር ያለመ ነው ሲሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሃላፊ ማያ ፎዓ (FOA) ገልጸዋል።

ዜጋውን ለማስፈራት የተለሳለሰ አቋም ይዟል የሚል ትችት የሚቀርብበት የብሪታኒያ መንግስት በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ግምት ውስጥ በመክተት ዜጋውን ለማስለቀቅ አፋጣኝ ጥያቄን ማቅረብ እንደሚገባው ሃላፊዋ አስታውቀዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው ይኸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ወር የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች ለአቶ አንዳርጋቸው መጻፊያ እስክርቢቶና ወረቀት እንዳይገባላቸው እገዳ መጣላቸውን አውስተዋል።


በዚህም የተነሳ አቶ አንዳርጋቸው የህግ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማቅረብ ያልቻሉ ሲሆን፣ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ የብሪታኒያ መንግስት በኩል አቶ አንዳርጋቸው የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። ሁለቱ ሃገራት ባልፈው አመት ሰኔ ወር በጉዳዩ ዙሪያ ስምምነትን ቢያደርጉም የኢትዮጵያ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይግባኝ ለማቅረብ እንደማይችሉ ለብሪታኒያ መንግስት ማሳወቁን ሪፕሪቭ ማግኘት የቻለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።


ጉዳዩ አሳስቦት እንደሚገኝ የገለጸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የብሪታኒያ መንግስት የችግሩ አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በመግባት አፋጣኝ እርምጃን እንዲወስድ አክሎ ጠይቋል።


Monday, 10 October 2016

TPLF regime declares state of emergency in Ethiopia

The TPLF-led government, shaken by widespread protests, declared Sunday a six-month long state of emergency.

The titular Prime Minister Hailemariam Desalegn said in a televised address to the nation that the state of emergence was needed to repulse what he called “the danger posed by anti-peace elements and foreign enemies on the peace, security and stability of the nation.”

The state of emergency was declared by the minorty regime after months of anti-government protests, especially in the Oromo and Amhara regions of the country where security forces killed hundreds of peaceful protesters and tens of thousands detained.

Protests were reignited this week after the death of hundreds of festival goers when  Oromos celebrated Ireecha, an annual thanksgiving and a festival to welcome spring. Security forces were accused of causing the mayhem by shooting into the massive crowd and throwing gas canisters.

The actions taken by security forces triggered a stampede which reportedly caused the death of nearly 700 people. Witnesses and video evidences also show security forces shooting at party goers who also used the occasion to express their grievances against the regime.

The minority regime has been widely accused of committing gross human rights violations since it came to power in 1991.

Sunday, 9 October 2016

Independent Inquiry Needed on Irreecha (HRW)

Scores of People Killed at Festival

The Ethiopian government should allow an independent, international investigation to determine how scores of people were killed at the country’s Irreecha festival on October 2, 2016, Human Rights Watch said in a question-and-answer document about the issue.

Unprecedented, large-scale anti-government protests have been sweeping through Oromia, Ethiopia’s largest region, since November 2015, and the Amhara region since July 2016. On October 2, in Bishoftu, a town 40 kilometers southeast of the capital, Addis Ababa, tensions ignited at the annual Irreecha festival – an important cultural event that draws millions of people each year. Security forces confronted huge crowds with tear gas and fired shots, inducing panic. Scores died during a stampede of people fleeing security forces.

Ethiopian security forces have killed more than 500 people during protests over the course of the last year. These protests have occurred in a context of the near-total closure of political space. Nongovernmental groups and the independent media face harassment, surveillance, and criminal charges.

Ethiopians should be able to criticize their government without fear of arrest, Human Rights Watch said. Security forces should exercise restraint and be held accountable for abuses.

“The world should be carefully watching what is happening in Ethiopia,” said Felix Horne, senior Africa researcher at Human Rights Watch. “As more and more people are killed in protests this year, the government should urgently change course to prevent more bloodshed.”

Friday, 7 October 2016

UN rights commission press briefing on Ethiopia

Spokesperson for the UN High Commissioner for Human Rights: Rupert Colville

(Geneva) — There has been increasing unrest in several towns in the Oromia region, south east of Addis Ababa, since last Sunday when many people died after falling into ditches or into the Arsede lake while apparently fleeing security forces following a protest at a religious festival in the town of Bishoftu. The protests have apparently been fuelled in part by a lack of trust in the authorities’ account of events as well as wildly differing information about the death toll and the conduct of security forces. We call on the protestors to exercise restraint and to renounce the use of violence. 

Security forces must conduct themselves in line with international human rights laws and standards. There is clearly a need for an independent investigation into what exactly transpired last Sunday, and to ensure accountability for this and several other incidents since last November involving protests that have ended violently.

Instead of cutting off access to mobile data services in parts of the country, including in Addis Ababa, we urge the Government to take concrete measures to address the increasing tensions, in particular by allowing independent observers to access the Oromia and Amhara regions to speak to all sides and assess the facts. In August this year, the UN High Commissioner for Human Rights requested access to the regions to enable the Office to provide assistance in line with Ethiopia’s human rights obligations. We again appeal to the Government to grant us access.

We are also concerned that two bloggers, Seyoum Teshoume and Natnael Feleke, the latter from the blogging collective Zone 9, were arrested this week. Feleke and a friend of his were reportedly arrested for loudly discussing the responsibility of the Government for the deaths at last Sunday’s Irrecha festival in Oromia. There have also been worrying reports of mass arrests in the Oromia and Amhara regions. We urge the Government to release those detained for exercising their rights to free expression and opinion. Silencing criticism will only deepen tensions.


Tuesday, 4 October 2016

የእሬቻ ክብረ በዓል ተሣታፊዎችን ፍጅት በተመለከት ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዲግ) እና ከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

የሃያ-አምስት ዓመታት የሕወሐት አገዛዝ ቁም ስቅላችሁን ያሣያችሁና ከመሞት በላይ ከመኖር በታች የሆነ የሰቀቀን ኑሮ የምትገፉ ዉድ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሆይ፡-

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዲግ) እና የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከቡሾፍቱ የተሠራጨዉን የወገኖቻችንን እልቂት የሚገልፅ እጅግ በጣም ዘግናኝ የሆነ ዜና የተከታተልነዉ በቃላት ለመግለፅ በሚያስቸግር የሃዘንና የጭንቀት ስሜት ነዉ፡፡

የፋሺስቱ ወያኔ አጋዚ ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል ቡሾፍቱ በሚገኘዉ ሆረ አርሰዲ የእሬቻን በዓል ለማክበር በተሰበሰቡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የወሰደዉ ጭካኔ የተመላበት እርምጃ ህዝብን አስተዳድራለሁ ብሎ በመንግሥትነት ሥልጣን ላይ በተቀመጠ አካል ዕዉቅናና ትዕዛዝ የተፈፀመ መሆኑ የዚህን ዘረኛ ሥርዓት መሪዎች እንደሰዉ ማሰብ መቻል እንድንጠራጠር አድርጎናል፡፡

የእሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት ታግሎና ተንከባክቦ በመጠበቅ ካቆያቸዉ የማንነቱ መገለጫ ከሆኑት እሴቶቹ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እንደተገለፀዉ በአገራችን ታሪክ እስከዛሬ ታይቶና ተሰምቶም በማይታወቅ ሁኔታ ባህላዊ እምነታቸዉን በሚያከብሩበት ሥፍራ በጣም ብዙ ዜጎቻችን በአጋዚ ነፍሰ ገዳዮች ወደ ገደል ተነድተዉና በጥይትም ተጨፍጭፈዉ አልቀዋል፡፡ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የበዓሉ ተሣታፊዎች ደግሞ ይህ መግለጫ እስከሚዘጋጅበት ጊዜ ድረስ የደረሱበት አለመታወቁን ከሥፍራዉ ከተላለፉልን መረጃዎች ለማወቅ ችለናል፡፡ ይህን የሕወሐት ድርጊት የበለጠ አሣዛኝና እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚያደርገዉ ደግሞ የእነዚህ ዜጎች ወንጀል በሕወሐት አረመኔያዊ አገዛዝ ሥር ታፍነን መማቀቅ በቃን ብለዉ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተቃዉሟቸዉን ለመግለፅ መሞከራቸዉ ብቻ የመሆኑ እዉነታ ነዉ፡፡

ይህ የጭካኔ እርምጃ የሕወሐት/ኢህአዴግ አገዛዝ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ባለዉ ንቀትና ጥላቻ መሠረት በማን አለብኝነት ፍትሃዊ ጥየቄ ባነሱ የአገራችን ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያወጀዉን ጦርነት ወደመተግበር መሸጋገሩን የሚያሣይ ነዉ፡፡ ስለሆነም ይህን በሰላማዊዉ የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተደረገ ለማመን የሚያስቸግር ግድያ በመግለጫ ብቻ ማዉገዝ በቂ እንዳልሆነ ይሰማናል፡፡ ለደረሰዉ የሰዉ ህይወት ጥፋት ብቸኛ ተጠያቂዉ የሕወሐት/ኢህአዴግ መንግሥት በመሆኑ መሪዎቹ ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ልናሰምርበት እንወዳለን፡፡ ይህን ዓይነት ዘግናኝ እልቂት ለማስቀረት የሚቻለዉ የሕወሐት/ኢህአዴግን አገዛዝ በማስወገድ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ ይህን አገዛዝ ለማስወገድ ደግሞ በተቃዉሞዉ ጎራ ያለን ኃይሎች አንድ ላይ ሆነን ለነፃነት የሚደረገዉን ትግል የበለጠ ማፋፋም ብሎም ጠንካራ አማራጭ ኃይል ሆነን በመገኘት በህዝባችን እየተካሄደ ያለዉን ትግል ከግብ ማድረስ ይኖርብናል፡፡ በዚህ ረገድ ኦዲግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በጋራ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጀምረናል፡፡ ይህ አሁን የደረሰዉ ዕልቂት ደግሞ የጀመርነዉን የጋራ ትግል የበለጠ አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያደርገን መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡
የተከበራችሁ ወገኖቻችን ሆይ፡-

የአሁኑ መስዋዕትነታችሁ በሕወሐት የሚመራዉን ሥርዓት በተቀናጀ መልኩ ታግለን ለመጣል የጀመርነዉን የጋራ ትግል በአስቸኳይ ወደ ሰፊ የአንድነት፣ የነፃነት፣ የዲሞክራሲና የፍትህ ታገዮች ህብረት በማሸጋገር ይህን የወንበዴዎች ቡድን በማስወገድ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና ፍትህ የሰፈነበትን ሥርዓት በአገራችን ዕዉን ለማድረግ የበለጠ ተግተን እንድንሠራ ያስገድደናል፡፡ ስለሆነም እስከዛሬ በሕይወትና በአካል የከፈላችሁትና እየከፈላችሁ ያላችሁት መስዋዕትነት ፍሬያማ እንዲሆን ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል፡፡ በዚህም ላይ ተመሥርተን የወያኔ የግፍ ድርጊቶች ገፈት ቀማሽ ለሆናችሁት ሕዝቦቻችንና በአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ ላሉ የኢትዮጵያ የነፃነት፣ የዲሞክራሲና የፍትህ ታጋዮች የሚከተለዉን ጥሪ ስናቀርብ ሁላችሁም የአሁኑ የሕወሐት አረመኔያዊ ድርጊት ከምን ጊዜዉም የተለየ መሆኑንና በሥርዓቱ ቁንጮዎች የታወጀብንን ግልፅ ጦርነት በቀላሉ የማንመለከተዉ መሆኑን ተረድታችሁ የየበኩላችሁን እንደምታደርጉ በመተማመን ነዉ፡፡

1. ለኢትዮጵያ ሕዝቦች በሙሉ፡-

የሕወሐት/ኢህአዴግ መሪዎች ላለፉት ሃያ-አምስት ዓመታት አንተን ከሰዉነት ዉጭ አድርገዉ ለአስከፊ ችግር፣ ለሰቆቃ፣ ለስደትና ለመፈናቀል ዳርገዉህ እነርሱ ግን ያንተኑ አንጡራ ሃብት በተለያየ መንገድ በመዝረፍ ቅንጦት የተመላበት ኑሮ መኖር አልበቃ ብሏቸዉ ዛሬ ደግሞ ያወጁብህን ጦርነት በግልፅ መተግበር ጀምረዋል፡፡ ባለፉት 11 ወራት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በኮንሶ እና በሌሎችም የኢትዮጵያ ክልሎች ያለምንም ጥፋት በግፍ መገደላቸዉ ይታወሳል፡፡ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ዉድ ልጆችህን በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ዉስጥ እንደፋብሪካ አስፋፍተዉ በከፈቷቸዉ የማሰቃያ ማዕከላት ዉስጥ አጉረዉ በታሪክ ከምናዉቀዉ በናዚ ማጎሪያ ቤቶች ይደረግ ከነበረዉ የማሰቃያ መንገድ በከፋ ሁኔታ ከማሰቃየትም አልፈዉ እሥር ቤቶችን በእሳት በማጋየት ሰዉን ያህል ክቡር ፍጡር አቃጥለዉ ሲገድሉ ታዝበናል፡፡ እነርሱ በሕዝብ ላይ ጦርነት ማወጃቸዉ እንዳለ ሆኖ አንተ ያነሣህባቸዉን የአልገዛም ባይነት ሰላማዊ የተቃዉሞ ጥያቄ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠርከዉ በማስመሰል የሕዝብ-ለሕዝብ ፍጅት ለማስነሣት የዉሸት ፕሮፓጋንዳ በሰፊዉ ነዝተዋል፡፡ መስከረም 22 ቀን 2009 ቡሾፍቱ በሚገኘዉ ሆረ አርሰዲ ዓመታዊዉን የእሬቻ በዓል ለማክበር በተሰበሰበዉ የኦሮሞ ሕዝብ ላይ የፈፀሙት የግፍ ጭፍጨፋ ያወጁብህን ጦርነት ወደከፍተኛ ደረጃ እያሸጋገሩት መሆናቸዉን በገሃድ የሚያሣይ ነዉ፡፡ የሕወሐት/ኢህአዴግ መሪዎች ይህን እርምጃ የወሰዱት የአንተ በልበ-ሙሉነት የአልገዘም ባይነት ትግልህን አጠናክረህ መቀጠል ተስፋ አሰቆርጧቸዉ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ ይህ የቡሾፍቱ ጭፍጨፋ በቀላሉ ከታለፈ እነዚህ ተስፋ የቆረጡ የወያኔ መሪዎች ተመሣሣይ ጭፍጨፋዎችን በሌላዉም ሕዝብ ላይ የማይደግሙበትና አንተን ፀጥ ለጥ አድርጎ ለመግዛት የሚያስችላቸዉን እርምጃ አጠናክረዉ የማይቀጥሉበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ስለሆነም የእኔ ነዉ ብለህ የምትቀበለዉን በነፃነት፣ በዲሞክራሲ፣ በፍትህ እና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ መንግሥት እስክታቋቁም ድረስ የጀመርከዉን ሰላማዊ የተቃዉሞ ትግል ለአፍታ እንኳን ሳታቋርጥ እርስ በእርስህ ተባብረህና ተረዳድተህ የበለጠ አጠናክረህ ቀጥል እያልን ጥሪ ስናቀርብልህ ምንጊዜም ከጎንህ መሆናችንን እያረጋገጥን ነዉ፡፡

2. በአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ በመንቀሳቀስ ላይ ለሆናችሁ የወያኔ ተቃዋሚ ኃይሎች በሙሉ፡-

ከመቼዉም ጊዜ በላይ ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የእኛን የተባበረ ኃይልና ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ አብረን መቆም ከሚፈልጉበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያን ሕዝቦች የነፃነት፣ የዲሞክራሲ፣ የእኩልነትና የፍትህ ጥማት ከሁሉም የፖለቲካ አመለካከት ልዩነቶቻችን አስበልጠን ማየት ይኖርብናል፡፡ አገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታና በሕዝባችን ላይ እየተፈፀሙ ያሉት የግፍ ድርጊቶች እልባት ካላገኘንላቸዉ እንታገልለታለን የምንለዉ ሕዝብ ህልዉናም ሆነ ከወያኔ ነፃ እናደርጋታለን የምንላት የጋራ አገራችን እንደ አገር መቀጠል ጥያቄ ዉስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ይህ እንዳይሆን ጥቃቅን ልዩነቶቻችንን ወደጎን በመተዉ ለትልቁ የአገርና የህዝብ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተን የየበኩላችንን ድርሻ መወጣት ጊዜ የማይሰጠዉ ጉዳይ መሆኑን ልናሰምርበት እንወዳለን፡፡ ስለዚህ እንደ የፖለቲካ ኃይሎች ተደራጅተን የምንንቀሳቀስ ወገኖች ሁሉ ሕወሐት የከለለልንን “በአገር ዉስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ” እና “ከአገር ዉጭ ያሉ” ወይም “ህጋዊ የሆኑ እና ያልሆኑ” የሚለዉን የሕወሐት ከፋፋይ ሴራ ወደጎን ትተን ተቀራርበን በመሥራት ይህን ፈታኝ ወቅት ማለፍ የማንችል ከሆነ በታሪክ ፊት ተጠያቂ ከመሆን የማንድን መሆኑን ለአፍታ እንኳን መዘንጋት የለብንም፡፡ ስለሆነም በአንድነት መንፈስ እየተዋደቀ ያለዉ ሕዝባችን ከምንም በላይ የሚፈልገዉንና በተለያዩ መንገዶች እየጠየቀ ያለዉን የተማከለ የፖለቲካ አመራር መስጠት የሚያስችለንን ሰፊ መሠረት ያለዉ ትብብር ለመመሥረት የጀመርነዉን ጉዞ እንድናፋጥንና ወደ የጋራ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንድንገባ ልባዊ ጥሪያችንን በድጋሚ እናቀርብላችኋለን፡፡
ፍትህና ነፃነት ለሁሉም ሕዝቦች!!

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዲግ) እና የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ
መስከረም 2009 ዓ. ም.

Monday, 3 October 2016

OLF Press Release on Irreecha Massacre

Irrecha Massacre of 2016 by TPLF Regime is a day of Infamy for Oromo people

The TPLF has committed genocide against Oromo people by murdering in a broad day light peaceful people who gathered at Bishoftu to Celebrate Irrecha, the Oromo National Thanks Giving Festival celebration on October 2, 2016. The TPLF attacked peaceful people on the ground and from the air by killing hundreds and wounding thousands. At Irrecha, Oromo from all corners of Oromiya dressing their cultural clothes and caring olive branch as sign of peace and prosperity get together to celebrate their national holiday.

The TPLF fascist regime which intoxicated with the blood of innocent Oromo people for the last 25 years, particularly for the last 11 months has ordered its army on the ground and the Helicopter from the air to attack peaceful innocent people who gathered at Hora Arsadi, Bishoftu for national Irrecha Celebration.

The Oromo Liberation Front strongly condemns this callous massacre by the TPLF Regime , and resolute that the TPLF regime will be accountable for the genocide it has committed against Oromo people who came together from all corners of Oromiya to Celebrate and thank their Almighty at Hora Arsadi , Bishoftu, Oromiya.

The murderous regime of TPLF should know that it will not control oromiya and its resources by killing its people. The glorious Oromo people will hunt the TPLF Regime down to make sure that they will pay for all crimes they have committed against Oromo people in particular and Ethiopian peoples in general.

We call upon all Oromo and other political organizations to be united to dismantle The TPLF callous & fascist regime. There remains no moral or legal justification to demand the respect of people’s rights from the regime that used machine guns on the ground and on the air against peace full people. All Ethiopian people should use all means necessary to dismantle the genocidal and murderous TPLF regime and its collaborators.

The OLF will do everything to make sure the TPLF will not get away with all crimes it has been committing against peoples in Ethiopia, and especially the mass murder it has committed against Oromo people at Irrecha National Thanks giving Holiday on October 2, 2016.

Victory to the Oromo People
Oromo Liberation Front
October 2, 2016