አሁን በደረሰን ዜና መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የሆኑት እንጂነር ይልቃል ጌትነት ፣ ብሌን መስፍን ፣ወረታው
ዋሴ ፣ወይንሸት ሞላ እና ሌሎችም ስም ዝርዝራቸው ያልተጠቅቀሱ አባሎች መታሰራቸውን ምንጮቻችን ከአዲስ አበባ ፖሊስ
ኮሚሽን መስሪያቤት ከሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ቅርንጫፍ ገልጸዋል ። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፖሊስ አባላቶች
በሌሎችም ዜጎጅ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ግለሰቦች ላይ እንዲሁም ፣መንግስትን ከሃገርቤት ሆኖ በፌስቡክ
እና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን የሚኮንኑ ጽሁፎችን የሚያወጡ ወጣቶችን አድኖ ለማሰር ደብዳቤ ከክፍተኛ ባለስልጣናቶች
እንደተላከ እና ያንን ተግባራዊ ለማድረግ ከ72 ሰአታት እስከ 315 ሰአታት እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል ።
ይህንን ለማድረግ የእያንዳንዱን የፖለቲካልም ሆነ የሌሎች አባል የሆኑ ዜጎችን የሚሰሩበትን መስሪያቤትም ሆነ
፣ስራዎቻቸውን አጣርተው ቢጨርሱም ፣እነሱን ለማፈን የሚንቀሳቀሱት አባላቶች ግን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የፖሊስ
ኮሚሽን ታማኝ የሆኑ ሰራዊቶች ብቻ ናቸው ሲኡ አትተዋል።
በተለይም በዛሬው እለት የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ምራክል በሃገሪቱ ላይ ጉብኝት እሚያደርጉበት ወቅት እንዲህ
ማድረጋቸው የአምባገነንታቸው ምልክት ነው ሲሉ ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላቶች ገልጸዋል ። በሃገር ውስጥ በመሆን
ብቸኛ የፖለቲካ ትግል የሚያደርገው እና ጠንካራ የፖለቲካ ፓርቲ ተብሎ የተሰየመው እንደዚሁም በወጣት አመራር እና
ወጣት ሃይሎች የተሞላው ይሄው የሰማያዊ ፓርቲ ጥቃት በተቃዋሚዎች እና በገዥው ፓርቲ ዱላ ሲሰነዘርበት የቆየ ጠንካራ
ፓርቲ ነው ሲሉም አክለው እነዚሁ ፖሊስ አባላቶች ገልጸዋል።
ማለዳ ታይምስ
0 comments:
Post a Comment