Monday, 24 October 2016

በየእለቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸመውን ግፍ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች፣ ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሌሎች ወገናዊነትንና አንድነትን የሚያጎለብቱ ተግባራት በመላው አለም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

ያሳለፍነው ቅዳሜ በጀርመንዋ ከተማ ቩርዝቡርግ በርካታ ህዝብ የተሳተፈበትና ዋና ዋና ጎዳናዎችን የሸፈነ ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን የፊታችን ቅዳሜ ደግሞ በሙኒክ ከተማ በሀገራችን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የሚመክር ህዝባዊ ስብሰባ ይደረጋል። በስዊትዘርላንድ ጄኔቫ ደግሞ በመላ አውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሚሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ በመጪው ሳምንት ማክሰኞ ይደረጋል።

በሌላ በኩል በኒዉዚላንድ ኦክላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን “ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በኒዉዚላነድ” ቅዳሜ ኦክቶበር 22፣ 2016 በኢሬቻ በዓል ሥነ ሥርዓት አከባበር ላይ ወጥተዉ በ አጋዚ ጦር ለተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት በማዘጋጀት ዘክረዋል። 


በዚህ የኢሬቻ የሻማ ማብራት ሥርዓት ላይ ወጣቶች ስለ አገራቸዉ ታሪክና አሁን ስላለዉ የኢትዮጵያ ችግር እና ዘርን አስመልክቶ ወያኔ እያደረገ ያለዉን የጥፋት ዘመቻ እና ወያኔን ለመታገል ከተደራጁት ወገን በኩልም መወሰድ ስለሚገባቸዉ እርምጃዎችና ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያዉያን ዛሬ አንድነት እና መተሳሰብ እንደሚያስፍልጋቸዉ አብረዉም መስራት እንዳለባቸው አቶ ባቱና አቶ ዘካርያስ በስነስርአቱ ላይ ሰፋ ያለ ገለፃ ሰጥተዋል።

0 comments:

Post a Comment