አስተባባሪዎች እንደገለጹት ሱቆች፣ ሆቴሎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለሁለተኛ ቀን ተዘግተው ውለዋል።
ከትናንት በበለጠም የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን እንዲከፍቱ ሲያስገድዱ ውለዋል። የገዢው ፓርቲ
ደጋፊ ነጋዴዎች ወይም እየተጠሩ ድርጅቶቻቸውን ካልከፈቱ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተነግሮአቸው ለይስሙላ ከከፈቱት
በስተቀር በአብዛኛው የከተማ ክፍል የስራ ማቆም አድማው በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል።
“ የሥራ ማቆም አድማ ማድረግ ክልክል ነው” የሚል አፋኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከወጣ በሁዋላ፣ አዋጁን ከምንም
ባለመቁጥር በክልሉ የሥራ ማቆም አድማ ሲደረግ ከባህርዳር ከተማ አድማ ቀጥሎ የጎንደሩ አድማ ለሁለተኛ ጊዜ
የተካሄደ ነው። የአሁኑ የስራ መቆም አድማ የባህርዳር ህዝብ በቢሾፍቱ ያለቁ ወገኖችን በማሰብ ያካሄደውን የሥራ
ማቆም አድማ በመደገፍ አጋርነትን ለመግለጽ እንዲሁም አፋኙን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመቃወም ተብሎ የተዘጋጀ መሆኑን
አስተባባሪዎች ተናግረዋል።
ሰኞ እለት የስራ ማቆም አድማውን ተከትሎ የንግድ ድርጅቶችን በጉልበት ለማስከፈት በተደረገ ሙከራ ወታደሮች
በሰዎች ላይ የተኮሱት ጥይት አንድ አህያ ተመትታለች። በርካታ ነጋዴዎችም ተይዘው ታስረዋል። በከተማዋ ዲሽ ለማውረድ
የተንቀሳቀሱ ካድሬዎች በድንጋይ መመታታቸውም ታውቋል።
በባህርዳርም ህዝቡ ዲሽ እንዲያወርድ በቀበሌዎች አሰተዳደር በኩል ሚሊሻዎች አሰሳ እያደረጉ ነው፡፡
ኢሳት
0 comments:
Post a Comment