ፖሊስ ቤተሰብን በወረዳ፣ በብሎክ ብሎም በቤት ደረጃ በማደራጀት እየጠረነፈ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች
ገልፀዋል፡፡ ከአሁን ቀደም በየካ ከፍለ ከተማ በየግቢው የታደሉ ‹‹የቤተሰብ ተጠሪ ፎረም›› የሚሉ ቅፆችን
በማስደገፍ መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በሳሪስ በተመሳሳይ አደረጃጀት ቤተሰቦችን ለመጠርነፍ እየተሰራ መሆኑን
ለማወቅ ተችሏል፡፡
ቅፁ ላይ የቤተሰብ አባላት ‹‹በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ የሚፈጠሩ ያለ መግባባቶችን
በራሳችን ለመፍታትና ብሎም የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲሁም ከፖሊስ ጎን ሆነን በማህበረሰብ አቀፍ
ፖሊስ አገልግሎት የድርሻችን ለመወጣት›› በሚል ከቤተሰብ መካከል ለፖሊስ ተጠሪ እንዲወክሉ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ይህ የቤተሰቡ የፖሊስ ተወካይም ግቢው ውስጥ ተፈጠሩ የሚላቸውን ጉዳዮችና ሌሎችም መረጃዎች ለፖሊስ ማድረስ
ይጠበቅበታል፡፡ ጥርነፋው ከቤተሰብ ተነስቶ፣ ብሎክ፣ ቀጠና እና ወረዳ እያለ እንደሚቀጥልም ለማወቅ ተችሏል፡፡
0 comments:
Post a Comment