(ዋዜማ ሬዲዮ) በሀገሪቱ የተከሰተውን ረሀብ በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ለዓለም ህዝብ ይፋ መሆኑን ተከትሎ መንግስት መረጃዎችን ለማፈንና ለመደበቅ እየሞከረ ነው።
መንግስት ለክልል መንግስታትና በውጪ ሀገራት ላሉ ኤምባሲዎቹ ባስተላለፈው መመሪያ ረሀብ ወደ ተከሰተበት አካባቢ
ጋዜጠኞች እንዳይሄዱ፣ የረድዔት ድርጅት ሰራተኞችም መረጃ እንዳያቀብሉ ብርቱ ጥረት እንዲደረግ አሳስቧል።
“ሁኔታውን ተጠቅመው የልማት ስኬታችንን ለማንኳሰስ ያሰፈሰፉ ፅንፈኛ ተቃዋሚዎችንና ለኢትዮዽያ በጎ አመለካከት የሌላቸውን ግለሰቦችና ተቋማትን መመከት ይገባል” ሲል መክሯል መመሪያው። ሁሉም መንግስታዊ አካላት ኢትዮዽያ የድርቁን አደጋ ለመቋቋም የሚያስችል በቂ አቅም እንዳላትና ጅምር የልማት
ስራዎችን ላለማደናቀፍ አለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ማስፈለጉን አፅንኦት ስጥተው እንዲያብራሩ አሳስቧል መመሪያው።
ከውጪ ሀገር ወደ ኢትዮዽያ ለመግባት በሚጠይቁ ጋዜጠኞች ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ገደብ እንዲደረግና ለኢትዮዽያ በጎ
አመለካከት ያላቸው ብቻ እንዲፈቀድላቸው፣ አስፈላጊው ማብራሪያም እንዲሰጣቸው ትዕዛዝ አስተላልፏል።
wazema radio
0 comments:
Post a Comment